>
1:29 am - Saturday December 10, 2022

"ትገደላላችሁ!!!" ንጉሱ ጥላሁን

“ትገደላላችሁ!!!”

ንጉሱ ጥላሁን
 
በቃል አላምረው
በተለያዩ ጊዚያትከስራ ያፈናቀለኝ ንጉሱ ጥላሁን ነው እያልሁ በየመድረኩ እከስ ነበር፡፡ ተቀራርባችሁ ብታወሩ የሚሉም በዙ፡፡ እኔ አልፈለግሁም! ግን ንጉሱ ይፈልግሐል ተባልሁ፡፡ ስልክህን እንስጠው አሉኝ፡፡ ከምትሰጡት ይሔው እኔ ልደውል ብዬ ደወልኩ፡፡ አያነሳም፡፡ በሌላ ቀን ደወለ እና እናውራ እፈልግሐለሁ አለኝ!
ጥቅምት 262012 ዓም ደወለ ፡፡ አሁን ስምንት ሰዓት ና አለኝ፡፡ አልችልም ስራ አለኝ  አስራ አንድ ሰዓት ይሁን አልሁት፡፡ እሺ አለ፡፡ በመሐል ደወለ እና 10 ሰዓት ና አለኝ፡፡ ሔድኩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፅፈት ቤት እራሱ ቢሮ ገባሁ፡፡ ተገናኘን፡፡ “እንዴ በአካል ሲያዩህ ጎስቋላ ነህ በቲቪ ሲያዩህ ቀይ ነህ” አለኝ! የገባኝ  ገባኝ… አይ እንዲህ ነኝ አልኩት! ስለ ኢኤን ኤን ጠየቀኝ፡፡ የማውቀውን ነገርሁት፡፡  በቃ የህወሓት ነበር በረከት ስምኦን ያግዛችሁ ነበር አለኝ፡፡
አማራን ለመጉዳትም ሆነ ህወሓትን ለማሰቀጠልእንዳልሰራን ነገርኩት፡፡  እየቀፈፈው ሰማኝ፡፡
አሁን ስራህን በህወሓት እየታገዝህ ነው የምትሰራው አለኝ፡፡ አይደለም አልኩት፡፡ 10 ሚሊዮን ብር እኮ ተሰጥቶሃል አለ፡፡ ውሸት ነው አልሁት፡፡ ለአንሙትም ለያየሰውም ተሰጥቷቸዋል አለኝ፡፡ ውሸት ነው አልሁት፡፡ ለጃዋር አንድ ሚሊዮን ዶላር ተሰጥቶታል አለኝ፡፡ ውሸት ይሆናል… ለእኔም ተሰጥቶሓል አልኸኝ እኮ አልሁት! ብዙ ተከራከርን!
እንዴት አቦይን ቃለመጠይቅ ታደርጋለህ ተከፍሎህ ነው አለኝ! አይደለም ወደ መቀሌ ሔጄ ቃለ መጠይቅ ያደረግሁት ለአሸንዳ ጊዜ በግሌ ሄጄ እንጅ ተከፍሎኝ አይደለም አልሁት! አውሎ ሚዲያ በእኛ ስር ይሁን እና እኛ እናግዝህ አለኝ፡፡ አልችልም፡፡ ሚዲያውም የእኔ አይደለም ተቀጣሪ ነኝ አልሁት፡፡ አግዘን አለኝ፡፡ በምን አልሁት..?  ቢያንስ ስታሰረጭ ቀድመህ ይዘቱን አሳውቀን አለኝ፡፡  ሀገር የሚጎዳ ነገር እኔ አለቅም! የማሳወቅ ግዴታም የለብኝም ሙያየ አይፈቅድም አልሁት! ከቻል ቃለመጠይቅ ስጠኝ፤ እኔ ፖለቲካዊ ፍላጎት የለኝም፤ ብሔርተኝነትም አይመቸኝም ፤ በአማራነቴ ከፈለግኸኝ አለሁ፤ በሙያየ ግን ነፃ መሆን እፈልጋሐሁ አልሁት! – የሰጠኝን ግማሽ ሌትር ውሓ ጨረስሗት፡፡
አንተም (በቃል አላምረው)አንሙትም ያየሰውም አንዳች ነገር ቢመጣ Shoot ትደረጋላችሁ አለኝ!! ትገደላላትችሁ ማለተቱ ነው፡፡
 አንሙትን ለምን አልሁት..? የአማራ ብሔርተኛ ሆኗል..! ከህወሓት መረጃ ያገኛል አለኝ!  አስፈራራኝ! ትገደላላችሁ አለኝ!
መረጃው፤ ባንኩ መድፉ፤ ኢንሳ፡ ሁሉ በእናንተ እጅ እኔ ከህወሓት እንደተከፈለኝእና እንዳልተከፈለኝ ለምን አታጣሩም አልኩት! አጣርተው እንደወሰኑ ነገረኝ፡፡ በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ እንደተወያዩበት ጠቅሶ አስፈራራኝ!
ከቀኑ 10:00 የጀመረው ውይይታችን12:30 አበቃ፡፡ ደግመን እንጠራሐለን እናወራለን አለኝ!  ይሔው Shoot መደረግን እያሰብሁ እየተከዝኩ አለሁ!
ተው ግን ተው! ሽመልስ ከማል አይታወስም፤ በረከት ስምና አይታሰብም፤ ነገሪ ሌንጮ አናስበው፤ ስዩም መስፍን አሁን አንደበታችን ላይ የለም! … ተው ባለጊዜ አትሁኑ! ተው እንድምትረሱ አስቡ…ተው ጊዜ ይለወጣል!
Filed in: Amharic