>
11:11 pm - Sunday August 7, 2022

ደሴ ..! ለታፈኑ ልጆቿ ብሶቷን አሰማች..! ..(ታደለ ጥበቡ)

ደሴ ..! ለታፈኑ ልጆቿ ብሶቷን አሰማች..!

 

ታደለ ጥበቡ
በአገራችን ኢትዮጵያ በ1960ዎቹ ሲደረግ በነበረው ጸረ ፊውዳል ትግል በግንባር ቀደምትነት የሚታወቀው የደሴው የወሮ/ስህን ት/ቤት ተማሪዎች ትግል ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ መፈክሮችን በማሰማት የመስዋዕትነት ተምሳሌቷን እናውሳለን:- ከመሬት ላራሹ እስከ አሁን ድረስ እስካ’ልተመለሰው “ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም” ድረስ መፈክር ይዘው የታገሉባት የጀግኖች አገር.,! ዛሬም በነበረው ወኔና ሰብአዊ የርህራሄ ስሜት ውስጥ ሆና ለታፈኑ ልጆቿ ብሶቷን አሰምታለች ..! ለመንግስትም ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክቷን አስተላልፋለች።

በሰልፉ ላይ ከታዩት መፈክሮች፦

1.እህቶቻችን የውሸት ትርክት ማወራረጃ አይሆኑም!!
2.ከእንግዲህ አማራ ሰላማዊ ሠልፍን ለደስታ እንጂ ሙሾ ለመደርደር አይወጣም! ዋ!
  3.የአማራ ጠላቱ ሆዳሙ ብአዴን/አዴፓ ነው!!
 4.ጠ/ሚ ሆይ በ7 ዓመተዎ ንጉስ እንደሚሆኑ ራዕይ ያዩለዎት እናትዎ እኮ ሴት ናት! ነው ሴትን ለስልጣን መውጫ ሿሿ ነው!
 5.እነ ጁሀር መሀመድ ሀይማኖትን ለፖለቲካ አጀንዳ እያዋሉት መሆኑ የማይረዳ ግለሰብም ሆነ ህዝብ ካለ ወደ ቀልቡ ይመለስ!!
6.የአማራ ህዝብ ለቅሶ ይብቃ!! በአማራነታቸው ብቻ የታፈኑት ልጆቻችን ልቀቁ!
7.አማራነት ወንጀል አይደለም!! መግደል፣ማሰር፣ማፈናቀል እና ማፈን ይቁም!!
8.የአማራን ህዝብ የካደው አዴፓ ከህዝባችን ጫንቃ ይውረድ….እህ! ፍትህ በተረኞች ለታገቱ እህቶቻችን!
9.የአርሶአደር ልጆችን በማገት አማራነት አይሸነፍም!
10.የዘረኞች ነብስ አገር አንቀጥቅጥ ሀሳብ ሲሆን የአማራው ነፍስ ዋጋው ስንት ነው!?
11.ሀይማኖታዊ ሀሳብ እና ኢትዮጵያዊነት ሀሳብ ፍፁም የተለያዩ ናቸው!!
12.አማራው ተራራው ተገፍቶ ማይወድቀው
      ለፀሎት እና ተኩስ ነው ሚንበረከከው
13.ከህወሓት የማምከን ስትራቴጂ የተረፉ ሴት እህቶቻችን በተረኛው ኦነግ ዳግም ሰለባ እየሆኑ ነው!!
14.stop OLF terrorism!
15.ንጉሱ ጥላሁን እኳን ዋሽተህ እውነት ብትናገርን አትታመንም አድባርባይና ሆዳምና ከሃዲ ስለሆንክ!!
*የዩቲብ ቻናላችን suscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!
Filed in: Amharic