>
5:13 pm - Sunday April 19, 1322

አሽሊ ግርሀም ወንድ ልጅ ወለደች! ስሙንም "ምኒልክ!" አለችው!!! (አለማየሁ ማ/ወርቅ)

አሽሊ ግርሀም ወንድ ልጅ ወለደች! ስሙንም “ምኒልክ!” አለችው!!!

 

አለማየሁ ማ/ወርቅ
አጤ ሚኒሊክ የጥቁር ህዝቦች ነጻነት ተምሳሌት!!! 
ትዕቢት ማንአለብኝነት ያንጠራራውን ጣሊያንን ድል ነስተው በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ ምክንያት  ለሆኑት መሪ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ እና ጀግና አርበኞቻችን ክብር ይሁንና በወያኔ ኢህአዴግ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ጥላቻንና የበታችነት ስሜት በስርአተ ትምህርት ተቀርጾለት ሲጋት ያደገ የቁቤ ትውልድ  ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ሚኒልክን ባልሰሩት ሀጢአት ሲረግምና ሲሳደብ ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን ሁሉ በአሳፋሪ ሁኔታ የምኒልክ ሰፋሪ (ወራሪ) ይውጣልን እያለ ዘቅዝቆ ሲሰቅል፣ አገት ሲያርድ ፣ ጡት ሲቆርጥና ሲያፈናቅል ቢኖርም ያንን የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት የሆነ ገናና ስም ሊያጠፋው ቀርቶ ሊያደበዝዘው አልተቻለውም! አይቻለውምም!!!
ለማንኛውም ቁርጣችሁን እወቁት ይህን የአፍሪካ ኩራት አማራ ጉያ ውስጥ ለመወሸቅ ያለአቅማችሁ ብትውተረተሩም ስመ ገናናው ምኒልክ ከመቶ አመት በኋላ ዛሬም ከክዋክብቱ በላይ ደምቆ በመላው አለም ስሙ እየናኘ ነው። እነሆ አይናችሁ እያየ ጆሮአችሁም እየሰማ አለም አቀፋዊቷ ሱፐር ሞዴል አሽሊ ግራሃም ልጄ “ምኒልክ!” እንጂ ሌላ ማንም አይባልም ብላለች !!!
አሜሪካዊቷ ሱፐር ሞዴል የበህር ልጇን ስም “ምኒልክ” ማለቷ ለምን እና እንዴት እንደሆነ ተጠይቃ “ታሪኩን በቅርብ ነው የሰማሁትና በጣም መስጦኛል!” ስትል ተናግራለች፡፡
አይደለም ከመቶ አመት ከአስር አመት በኋላ የሚነሳ ስም የሌለው የምድር ትቢያ ሁሉ በጫት በደነዘ አእምሮ፣  በጣላቻ ስብከት በታወረ ህሊና እድሜ ዘመኑን “ነፍጠኛ፣ ወራሪ፣ አስገባሪ፣ ፋሽስት….” እያለ የተጫነውን ሲዘረግፍ ቢኖርም እርሱ እያነሰ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ምኒልክ ከፍ… ከፍ…ከፍ እያለ ስሙ ገና የመጭው ትውልድ የነጻነት፣ የኩራት፣ የአልበገር ባይነትና የክብር መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል። ይህው ነው ወዳጄ!!!
Filed in: Amharic