>

ትራንስ ማንነት በኢትዮጵያ (ብሩክ ደሳለኝ)

ትራንስ ማንነት በኢትዮጵያ

ብሩክ ደሳለኝ

ጽንሰ ሃሳብ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡ በጠላት የተጠፈጠፈን ጽንሰ ሃሳብ መነሻ አድርጎ መጯጯህ ጊዜንና ሀብትን ከማባከኑም በላይ ሌሎች ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እንዲዘነጉ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጠላት አጀንዳና ጽንሰ ሃሳቦች ዙሪያ ማተኮርና አስተሳሰቡን ማራቆት ያስፈልጋል፡፡ የብሔሮች ጉዳይን ባብዛኛው ከሶቭየት ህብረት ጋር ብቻ ለማያያዝ ቢሞከርም የብሔሮች ጉዳይ በዋናነት መነሻው አውሮፓ የፈረንሳይ አብዮት ነው፡፡ ብሔረሰብ የሚባለው በአሁኑ ዘመን ትርጉም የሌለው ቃል ግን ከሶቭየቶች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ኢትጵያን ካጥለቀለቋት ዘባተሎ የጠላት ጽንሰሃሳቦች አንዱ ብሔረሰብ፣ ህዝቦች የሚባል በኢትዮጵያ ውስጥ እጅ እግር ያጣ ሃሳብ ነው፡፡  

ብሔረሰብ ማለት ደግሞ  ‹‹ በይበልጥ የባሪያ አሳዳሪና የፊውዳል ሥርዓት ዓይነተኛ ገጽታ የሆነ የሰዎች ታሪካዊ ማህበረሰብ ነው›› ይላል የደርግ የማርክሲዝም ሌኒኒዚም መዝገበ ቃላት፡፡ እንግዲህ ይህንን ገጽታ ነው የብሄር-ብሔረሰብ ድርጅት ነን ባዮቹ ለዛሬው 21ኛ ክፍለዘመን ኢትዮጵያውያን ይዘውልን የቀረቡት፡፡ የብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች አስተሳሰብ መነሻ ደግሞ ወያኔ ያረቀቀው ሕገመንግስት ነው፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ማነው ብሔር ማነው ብሔረሰብ ማነው ሕዝብ? አስኪ ከሰማንያው ቋንቋ ካለው ህዝብ  ስንቱ ነው ብሔር? ስንቱ ነው ብሔረሰብ? ስንቱ ነው ህዝቦች የሚባለው ቅርጫት ውስጥ የሚገባው? የብሔር መብት ምንድነው? የብሔረሰብስ? የህዝቦችስ? ማንም ሲተነትነው አላየንም ከጉንጭ አልፋ ቃላቶቹን የመደጋገም በቀቀናዊነት በቀር፡፡

ወያኔያዊው ሕገ መንግሰት ‹‹ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ማለት፡

 

  • ሰፋ ያለ የጋራ ጸባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ 
  • ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣
  • የጋራ ወይም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣
  • የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና፣

 

  1. በአብዛኛው በተያያዘ መልክኣ ምድር የሚኖሩ ናቸው ›› ይላል፡፡

የደርግ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ደግሞ ስለ ብሔር ትርጉም እንዲህ ይላል፤ 

  1. ‹‹ በአንድ መልክአ ምድራዊ ክልል ውስጥ መኖር፣ (5.)
  2. በኤኮኖሚያዊ ግንኙነት መተሳሰር፣ (?)
  3. በአንድ ቋንቋ መጠቀም፣ (2.)
  4. በጋራ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የወል (3.)
  5. ሥነ ልቡናዊ ገጽታዎችና (4.)
  6. ባህላዊ አመለካከቶች (1.) መከሰት የብሔር መከሰት መሠረቶች ናቸው፡፡

ከላይ በንጽጽር እንደተቀመጠው ከዕውቀት ነጻ የሆነው ወያኔ ህገ መንግስቱ ላይ ያሰፈረው የደርግ ማርክሲስቶች ለብሔር የሰጡጥን ትርጉም ትንሽ አቀማመጣቸውን በማለዋወጥ ነው፡፡ ወያኔማ እንኳን ማርክሲስቶችን ተራ ምሁራንንም ጠል የሆነ ድርጅት ስለሆነ ከመኮረጅ ውጪ በራሱ ማውጣት ቀርቶ በቅጡ ሌሎች የጻፉትንም መረዳት የማይችሉ አስተሳሰበ ድኩማን ስብስብ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በግሎባላይዜሽን ዘመን “በኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መተሳሰር” የሚለውን እንኳ ዘሎታል፡፡

 እንግዲህ በሕገመንግስቱ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት የሆኑት ብሔር፣ ብሔረሰብና፣ ሕዝቦች በሙሉ የማርክሲስት ሌኒኒስት የብሔር ትርጉምን ይጋራሉ፡፡ ይህም ሁለቱን ብሔረሰብና፣ ሕዝቦች የሚባሉትን መካተት አላስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ባጭሩ ብሔሮች ቢባል ይበቃ ነበር፡፡ ሕዝቦች ብሎ ነገር በኢትዮጵያ መዝገበ ቃላት ጨርሶ የለም፡፡ ጸያፍ ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ከተለመደ ችግር የለውም ይላል፡፡ በህግ ደረጃ ያውም ሕገ መንግሰት የቋንቋውን አገባብ በሚገባ መጠበቅ አለበት፡፡ አለበለዚያ መግባባት ላኖር ነው፡፡ ለዚህ ነው ብሔረሰብ፣ ሕዝቦች የሚባለው አስተሳሰብ እጅ እግር የሌለው የተባለው፡፡

ሲጀመር ኢትዮጵያን በአውሮፓውያን የብሔሮች የራስን በራስ የመወሰን ጠባብ ከረጢት ውስጥ ለመክተት መሞከሩ ራሱ ሙልጭ ያለ የዕውቀት ድህነት ነው፡፡ ኢትዮጵያን የምታክል በሺዎች የሚቆጠር ታሪክ ያላት ታላቅ ሀገር ያውም ዋናውን መንፈሳዊነቷን ወደ ጎን አድርጎ ከ16ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በተነሱ መናኛ የሰውኛ አስተሳሰብ ብቻ ልለካት ማለት የተራራን ከፍታ በስንዝር እንደመለካት ይቆጠራል፡፡

ብሔር በኢትዮጵያችን የነበረ መሬት የረገጠ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ማርክሲስት ሌኒኒስት ነን ብለው አብዮተኞቹ ከሶቭየቶቹ ገልብጠው አመጡብን እንጂ ብሔር በተሰማ ሀብተ ሚካኤል መዝገበ ቃላት ትርጉሙ፤ 

‹‹በአውራጃዎቹ ውስጥ በስምና በቅፈፍ፣ በድንበር፣ ተከፋፍሎ የሚጠራ፣ መስፍኑና አበጋዙ፣ ደጃዝማቾቹም፣ ህዝቡም በአገዛዝ፣ በስልጣን የተለየ  በዚያውም ውስጥ ብዙ ቀበሌዎችና መንደሮች፣ ልዩ ልዩ ባላባትና፣ ባለጉልት ትልቅ ባለርስትም ያሉበት ብሔር(ወረዳ) ይባላል፡፡›› ይላል፡፡

ይህ ትርጉም ከአገሪቱ ተጫባጭ ሁኔታ ተነስቶ የተሰጠ ትርጉምና ለማንም በወቅቱ ለነበረ ተራ ሰው የሚገባ ትርጉም ሲሆን፣ የማርክሲስት ሌኒኒስት የብሔር ትርጉም ግን ለተራው ሰው የማይገባ ባዕድ ትርጉም ስለነበር ከደርግ እስከ ኢሕአዴግ ሲተገበር የነበረው ለማርክሲስት ሌኒኒስቱ ጽንሰ ሃሰብ ሲባል በኢትዮጵያ የነበረውን አተረማምሶ ገለባብጦና አጡዞ ለትርጉሙ የምትመች አገር በማድረግ አዲስ ‹‹ደጃዝማች›› የመሆን አጀንዳ ነው፡

ኢትዮጵያን ከማጥቂያ ግልጽና ድብቅ አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነውን የብሔረሰብ አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ያለን ሰዎች የምንገዳደርበት ጽንሰ ሃሳብ እስከአሁን በተደረሰበት የፖለቲካ ርኩቻ ጥርት ብሎ ባለመውጣቱ ከዚህ በሚከተለው የትራንስ ኢትዮጵያዊነት  ጽንሰ ሃሳብ እንድንመክተው ጽንሰ ሀሳቡ እንደሚከተለው በአጭርና ግልጽ ቋንቋ ቀርቧል፡፡ 

ዘመኑ ኮርጆ የመለጠፍ ዘመን በመሆኑ ብዙ ሳንደክም በኢትዮጵያ ለተካሄደው የሰላሳ ዓመት የማንነት መወናበድ መገለጫ ትራንስ የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እናገኛለን፡፡ ትራንስ የባዕድ ቃል ሲሆን የማንነት ክህደትም በኢትዮጵያ በተለይ ኤርትራና ትግራይ በተፈለፈሉ እናት ሃገራቸውን የካዱ ሰዎች የተፈጠረ ከዚህ ቀደም በአገሪቷ ታሪክ ከነበረው ለጠላት የማደርና ባንዳነት የተለየ ባዕድ ማንነት በመሆኑ በባዕድ ቋንቋ መገለጡ ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም የትራንስ ማንነት በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ከወያኔ መፈጠር በፊት የሌለ ህዝቡም የማያውቀው ክስተት ነበርና፡፡ ባንዳነት የነበረ ቢሆንም ባንዳ አገሩን ይከዳል እንጂ ራሱን አይክድም፡፡ ትራንስ የሆነ ሰው ግን የሚክደው አገሩን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ማንነቱንም ነው፡፡ በአሁኗ ኢትዮጵያ ትራንስ ማለት እንደሚከተለው ከተመሳሳዩ የእንግሊዝኛ ጽንሰ ሃሳብ ተቀድቶ እንደሚከተለው ተተርጉሟል፤

Trans is an umbrella term to describe people whose IDENTITY is not the same as or DOES NOT SIT COMFORTABLY with, the ETHIOPIAN NATIONALITY they were assigned at birth.

ትራንስ የምንላቸው ሰዎች ሲወለዱ የነበራቸው ኢትዮጵያዊነት አልተመቸንም ወይም ማንነታችን ከኢትዮጵያዊነት ጋር ተመሳሳይ አይደለም ብለው የሚሉ ሰዎችን ነው፡፡ ወደ ፈረንጆቹ ዝባዝንኬ ጉዳይ ውስጥ ሳንገባ ወያኔ የወንድ ብልቱን አሰልቦ የሴት ብልት ተኩልኝ እንደሚለው ትራንስ ግለሰብ ኢትዮጵያዊነቱን በገዛ እጁ ሰልቦ ፌክ የትግሬነት ስብዕና ለጥፎ ሲለፋደድ የነበረ የዘቀጠ የትራንስ ግለሰቦች ስብብ ነበር፡፡ እዚያ ውስጥ ይህን ጉድ ሳያውቁ በፕሮፓጋንዳና በግምገማ ማደንዘዣነት ኢትዮጵያዊነታቸውን ተሰልበው ፌክ የትግሬነት ስብዕና የተተከለባቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ወያኔ የወያኔ አማራውንና የወያኔ ኦሮሞውን ኢሕአዴግ በሚባል የትራንሶች ድርጅት አማካይነት በመመልመል ብአዴንና ኦፒዲኦ በሚባሉ ትራንስ ድርጅቶች አማካይነት ይህን የትራንስ ኤትኒክ በሽታውን በመላው አገሪቱ በማስፋፈት በአሁኑ ሰዓት አገሪቱ በትራንሶች ተጥለቅልቃ ትገኛለች፡፡ ኢህአዴግ (ብልጽግና) የትራንሶች ድርጅትና የትራነሶች ጸረ ኢትዮጵያ “ሆርሞን” መውጊያ ሆስፒታል ነበር (ነው)፡፡

የኢህአዴግ (ብልጽግና) አባል ሲኮን ዋናው መለኪያ ኢትዮጵያዊነትን ከስብዕናው በፈቃዱ ተሰልቦ አዲስ ፌክ ትራንስ ማንነት ማለትም ትራንስ የአማራነትና ትራንስ የኦሮሞነት ስብዕና ማስተካት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካ መድረኩ ላይ የሚምነሸነሸው ይህ ትራንስ ኦሮሞና አማራ ነው – ትራንስ ትግሬው ተደምስሷል፡፡ ከታሪክ ዕውቀት ነጻ የሆነው ወያኔያዊው ኢህአዴግና ተረፈ ኢህአዴጉ ብልጽግና ስለኢትዮጵያዊነት ያላቸው ድኩም አስተሳሰብ ቢያንስ በሶስት ሺህ አመታት የተረጋገጠ የነገስታት ታሪካችንን ሙልጭ አድርጎ ክዶ እንቶ ፈንቶውን ይደረድራል፡፡ ዛሬ በወያኔ ድኩም አስተሳሰብ የተበከለው ትራንስ ትውልድ ጭራሽ በረቀቀው ኢትዮጵያዊ ማንነት አድዋን ድል ያደረጉትን አባቶቻችንን ወያኔ ባቀበለው ጨምላቃ አስተሳሰብ እየመዘነ ምኒሊክ አማራ ነው ጣይቱ አማራ ናት ሀብተጊዮርጊስ ኦሮሞ ነው ገበየሁ አማራ ነው እያለ መቀበጣጠር ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ትረንስ ፖለቲከኛ በራሱ በዘቀጠ የወያኔ አስተሳሰብ ተዘፍቆ በኢትዮጵያዊነት ስለኢትዮጵያ ሲወጡ፣ ሲወርዱ፣ ሲሰው የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን የትራንስ ማንነት ታራጋ ሊለጥፍላቸውና የራሱ መዝቀጥ ሳይበቃ ጀግኖቹን ኢትዮጵያውያን ከመቃብር ቀስቅሶ ታሪካቸውን ሊያዘቅጥ ሲቀበጣጥር ይገኛል፡፡ 

የየአካባቢው ታሪካዊ ድርሻ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በዓድዋ ለኢትዮጵያ የሞተ አማራ ለኢትዮጵያ የሞተ ትግሬ፣ ለኢትዮጵያ የሞተ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ወዘተ የለም፡፡ በዓድዋ የተዋጋው፣ የሞተው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፣ አማራ አይደለም፣ትግሬም ኦሮሞም ሌላም አይደለም – ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ 

ለማጠቃለል ኢትዮጵያዊው ኃይል ወያኔ ኢህአዴግና ተረፈ ኢህአዴጉ ብልጽግና በብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስም የሚነግዱበትን ፖለቲካ ትራንስ  ኢትዮጵያዊነት በሚል ጽንስ ሃሳብ ለመመከት ይህች ትራንስ የተባለች ነጠላ ዜማ ተለቃለች፡፡

Filed in: Amharic