>

የኦሮሙማ መራሹ መንግስት በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶችን እያሰሰ ማፍረሱን መበልጸግ አድርጎታል....¡¡¡ (ይድነቃቸው ከበደ)

የኦሮሙማ መራሹ መንግስት በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶችን እያሰሰ ማፍረሱን መበልጸግ አድርጎታል….¡¡¡
ይድነቃቸው ከበደ

 የኦሮሚያ ብልፅግና #የወታደር ካምፕ አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረና በቅርስነት የተመዘገበውን የራስ  ኃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት ማፍረሱን የከተማው ባህል ፣ ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ሃላፊ ተናግረዋል፡፡
~  ሆን ተብሎ ፣ ታቅዶበት በተደጋጋሚ ፤ በተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች የሚገኙ እድሜ ጠገብ ታሪካዊ ቅርሶች
በማን አለብኝነት እብሪት እንዲፈርሱ እየተደረጉ ነው !
~ የተቀሩት ቅርሶች ደግሞ ፤ ለመፍረስ እና ለመውደም እንዲሁም  በአዲስ “ማንነት” ለመተካት አፍራሾች አድብተዋል !
~ ይህ ሁሉ ሲሆን ፤ የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን፣ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም  የሚመለከታቸው የመንግስት ሹመኞች ፤ ” ጉዳዩ አሳስቦናል ፤ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው ፣ ወደ ፍርድ ቤት እንሄዳለን ” በማለት ምላሽ ቢሰጡም ፤ መንግስታዊ መዋቅር ያለው ቅርስ ጠል የኦሮሚያ ብልጽግና መራሹ ታሪክ ከመደምሰስ ወደኋላ አላለም ።
~ ከትላንት የቀጠለው ቅርስ የማጥፋት ተግባር ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው በቅርስነት የተመዘገበው የራስ  ኃይሉ ተክለሃይማኖት መኖሪያ ቤት መፍረሱን የከተማው ባህል ፣ ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ሃላፊ ተናግረዋል፡፡
~ ምን ይሄ ብቻ በርካቶችን ያፈራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት ወይም ኮሜርስ ለማፈረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ስለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው
• ከወራቶቹ በፊት በቅርስነት ተመዝግቦ በርካታ አመታትን ያስቆጠረው የደጃዝማች አስፋው ከበደ መኖሪያ ቤት “የኦሮሚያ ብልፅግና የወታደር ካምፕ ልገነባ ነው”  በማለት ቅርሱን አፍርሶ ጊቢውን ተቆጣጥሮት ነበር።
በወቅቱ ፤ አቶ አበባው አያሌው የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ድርጊቱን በማውገዝ ፍርድ ቤት ድረስ እንደሚሄዱ ገለጸው ነበር ።
ይሁን እንጂ በሃይል እና በወረራ የተያዘው የደጃዝማች አስፋው ከበደ መኖሪያ ቤት ፤ ወራሪው ሃይል መደላደል ፈጥሮ ተፈላስፉበት ይገኛል ¡¡
ይህ ቅርስ ጠል አካሄደ ማብቂያው የቱ ጋር ነው ?! ተጠያቂው ማነው ? ምን ቢደረግ የተሻለ ነው ?!
Filed in: Amharic