ከወያኔ ጋር የሚደረገው ጽምዶ፤ ለአርበኛ እስክንድር የተሰጡ ምላሽ እና የግድያ ዛቻዎች

የማይጠይቅ ትውልድ፤

 

መዓዛ መሀመድ፣ ሀብታሙ አያሌው እና አሳዬ ደርቤ አርበኛ እስክንድር ነጋን መሳደብ ብቻ ሳይሆን፣ በሌላ ተሳዳቢ አሳልፈው የማሰደብ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል።

ለምሳሌ ድምጸ ሻቢያው ዮናስ የተባለው ጋዜጠኛ እንዳለው “እስክንድር ነጋን ይሄን ሰውዬ መሸኘት ነው የሚያዋጣቸው” የሚለው ዛሬ በተግባር እየታየ ነው።

“ማይጠይቅ ትውልድ” ትውልዱ መጠየቅ አለበት ተብሎ ነበር። ድርጅት የሚገነባው ተገቢውን ጥያቄ በመጠየቅ፣ የጎደለውን እንዲሞላ በውስጥ ትግል እየተደረገ እንጂ፣ ዝም ብሎ ሆይ ሆይ በማለት ብቻ አይደለም። ለማስታወስ ያህል፣ ከዚህ ቀደም አፋብኃ በተሰኘው ድርጅት ተገቢውን ጥያቄ የሚጠይቅ ትውልድ ባለመኖሩ አንድ መሪ መምረጥ አቅቶ 13 መሪ ያለው ድርጅት ነበር።

አርበኛ እስክንድር ነጋ ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትብብር አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ የደረሰበት የስድብ ውርጅብኝ፣ የስብዕና ገደላ እና የግድያ ዛቻ እንደሚከተለው ቀርቧል።

1. የሀብታሙ አያሌው አደገኛ ምላሽ

ድምጸ ወያኔዋ ሰገነት፣ ሀብታሙ አያሌው ለአርበኛ እስክንድር ነጋ የሰጠው ምላሽ እጅግ አደገኛ እና ዘግናኝ ነው። ከስብዕና ጥቃት አልፎ፣ መሬት ላይ ያሉትን ፋኖዎች ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እንዲወስዱ የሚገፋፋ የጥላቻ ንግግር ነው።

እስክንድር ነጋ ተገደለ” የሚለውን የሀሰት መረጃ መጀመሪያ ይዘው የመጡት የአገዛዙ ካድሬዎች፣ እነ አቤ ቶክቻው የተባሉት እና ሌሎች የአገዛዙ ደጋፊ የፌስቡክ ገጾች ናቸው። ሀብታሙ ግን ይህንን ሀሰት አጣመመው፣ “የአርበኛ እስክንድር ነጋ ደጋፊዎች ናቸው፣ እሱ ነው በጀርባ ያዘዛቸው” በሚል የፈጠራ ትርክት፣ በአርበኛ እስክንድር እና በአፋብን መካከል ሽብልቅ ለመፍጠር ሞክሯል። በተለይ አርበኛ እስክንድር ነጋ የሚገኝበት ሸዋ ቀጠና ከሚንቀሳቀሱትን ፋኖዎች ከነአርበኛ መከታው ማሞ ጋር ለማጣላት የተቀነባበረ ሴራ ነው።

2. ወልቃይት ላይ ያለው ልዩነት

ድምጸ ወያኔ ቴዲ ርዕዮት ለወያኔ ሲሟገት ወልቃይት እና ራያን “በእርግጠኝነት የትግራይ ነው” እያለ ነው። ሌሎቹ እነ ሀብታሙ አያሌው፣ መዓዛ መሀመድ እና አሳዬ ደርቤ ግን “የቁራጭ መሬት ጉዳይ ነው፣ ድህረ-አብይ ውሳኔ ይሰጥበታል” እንጂ “በእርግጠኝነት የአማራ ነው” ብለው በአቋም አስርግጠው አይናገሩም። ለዚህ ነው ይህ ትብብር ሳይሆን ጥገኝነት ነው የምንለው።

3. የሮሃ መዓዛ መርዛማ ንግግር

አሁን ደግሞ ድምጸ ወያኔ ሮሃ መዓዛ የምትባለዋ “አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ አፋብን እርምጃ እስኪወስድ እየጠበቅን ነው” ብላለች። ይህ ማለት “አርበኛ እስክንድር ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትብብር መጠየቅ አይችልም” እያሉ ነው።

ይህ አሳፋሪ ውርደት ነው። አርበኛ እስክንድር ነጋ ከትግል ሜዳ፣ ከጫካ ውስጥ ሆኖ ደም እየከፈለ በቀጥታ በአባልነት ባለበት ድርጅት ውስጥ እንኳን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩት መዓዛ፣ ሀብታሙ፣ አሳዬ እና ከወያኔ ያነሰ ተሰሚነት እንዳለው ማድረግ፣ በአፋብን ድርጅት ውስጥ ጌታ እና ሎሌ ተፈጥሯል ማለት ነው። አርበኛ እስክንድር ነጋ ከሌላው የድርጅት አባል ጋር እኩል ድምጽ እንዳይኖረው ተደርጓል። እንዲያውም የድርጅቱ አባል ያልሆኑት የድምጸ ወያኔ ሚዲያ አካላት ከድርጅቱ አባል በላይ ተሰሚነት አላቸው ማለት ነው።

4. መሰዋዕትን አለማክበር የወደፊቱን ፋኖ ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ

የአማራ የህልውና ትግል የሚከፈለውን መሰዋዕትነት ማክበር እና ማስከበር አለበት።
አርበኛ እስክንድር ነጋ ድስቴን ማቄኑን ሳይል፣ ምቾቱን ትቶ ወደ ጫካ የገባው የሚደነቅ እና ሊበረታታ የሚገባው ጀግንነት ነው። ምክንያቱም ተተኪ ፋኖ የሚፈራው በዚህ መንገድ ነውና።
ሌሎችም ፋኖዎች ለህዝባቸው ሞተው ህዝባቸውን ነጻ ለማውጣት እየታገሉ ነው። እነሱን ማበረታት፣ የሚከፍሉትን መሰዋዕትነት ዋጋ መስጠት የሁላችንም የትግሉ ደጋፊዎች ግዴታ ነው። ነገር ግን አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ፣ የሚከፍለውን ዋጋ ማንኮሰስ እና የስብዕና ገደላ በሱ ላይ ብቻ የሚቆም አይደለም።

አጠቃላይ ፋኖን፣ የወደፊት ፋኖ የሚሆነውን ትውልድ ከእሴቱ ሊያርቅ የሚችል፣ ህብረተሰቡን ወደ ኋላ የሚጎትት አደገኛ ተግባር ነው።

5. አፋብን ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት አደጋ!

እነዚህ ሚዲያዎች እያደረጉ ያለው ነገር ቀላል አይደለም። ፋኖን በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጠላ፣ በከባድ ወንጀለኛነት ሊያስፈርጅ ወደሚችል አደገኛ ተግባር እየመሩት መሆኑን አፋብን አውቆ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።
አንድ ጀግና ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መጥራት፣ “መሸኘት” የሚባል የግድያ ቋንቋን ማስተጋባት፣ ነገ ፋኖን በሙሉ “የጦር ወንጀለኛ” በሚል ዓለም አቀፍ institution ሊያስመዘግብ ይችላል። ይህ ለጠላት የሚሰጥ ትልቅ መሳሪያ ነው።

ስለዚህ አፋብን ከእነዚህ ድምጸ ወያኔ ሚዲያዎች ጋር ያለውን ርቀት ጠብቆ፣ ትግሉን ከጥላቻ ንግግር እና ከግለሰብ ጥቃት ነጻ ማድረግ አለበት።

– ሥርዓትነቀልለውጥ
– ስርነቀልለውጥ
– AmharaResistance
– AmharaGenocide

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.