ከሎጂክ፣ ከአመክኒዮ፣ ከእውነት፣ ከመርህና ከአቋም ጋር ፈጽሞ የማይተዋወቀውና ገንዘብና ክፍያ ባለበት እና ለከፈለው ሁሉ አብዝቶ በመጮህ የሚታወቀው ጆቶኒው ሀብታሙ አያሌው የሴኩቱሬ ቦታ ለመተካት መጋጋጥ
(ክፍል -፩)
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
ጆቶኒው ሀብታሙ አያሌው – በእርግጥ ጆቶኒ ብቻ አይደለም እልምና ሙልጭ ያለ የሀሳብ፣ የመረጃ፣ የገንዘብና የዝና ሌባም ጭምር ነው – ሰሞኑን ጽምዶን የነካ ውጉዝ ከመአሪዮስ ነው፣ ጽምዶን ያልተቀበለ ኦህዴድ መራሹን ብልጽግናን የመረጠ ነው እያለ ማቀርሸት ከጀመረ ሰነባብታል።
እውነትን፣ ፋክትን በተመለከተ ሁለት ማስረጃዎችን ልጠቀም። ወያኔ የአማራ ሕዝብ በተለይም የሸዋ አማራ ጠላት ናትብሎ የተናገረውንና በአፋህድ ውስጥ ሰርጎ የገባውን አምስተኛ ረድፈኛን በተመለከተ።
1ኛ- ሀብታሙ አያሌው ህወሃት የአማራ ሕዝብ ጠላት ናት፣ በተለይም የሸዋ አማራ ጠላት ናት የሚለውን መረጃ እኔ ነኝ የገለጽኩላችሁ፣ የተነተንኩላችሁ፣ እናም ዛሬ እኔ በነገርካችሁ መረጃ ተመሰርታችሁ ወያኔ የአማራ ጠላት ናት፣ በተለይም የሸዋ አማራ ጠላት ናት እያላችሁ አትናገሩ፣ ዝም ብላችሁ ወደ ጽምዶ ተደመሩ እያለ ነው።
ይህ እልም ያለ አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው።
ይህንን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደረግነው እኛ የኢትዮጲያ ነጻ ፕረስ ሚዲያዎች ነን።
ታሪኩ እንዲህ ነው። በ1989 EU C የ CIAው ፕሮፌሰር ፖል ሄንዝ መለስ ዜናዊ ጫካ ውስጥ እያለ Interrogate አድርጎት ነበር። ቃለ ምልልስ ሳይሆን የምርመራ ጥያቄ አድርጎለት ነበር። ህወሃት ማን ነው?? እናንተ የአልባኒያ ኮምኒስት ናችሁ? ደርግን ብትጥሉ ምን አይነት መንግስት ትመሰርታላችሁ እና ወዘተ አይነት ከአሜሪካን ኢንተረስት ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ጥያቄዎችን ጠይቆት ነበር። የጥያቄውም አላማ አሜሪካ ኢሕአዴግን እና የኤርትራስን ሻእቢያ ደርግን ለመጣል ለመደበቺው 100 ሚሊዮን ዶላር (ለህወሃት 50 ሚሊዮን ለሻእቢያ 50 ሚሊዮን የተሰጠ ) በጀት ለመልቀቅ ያለመ ነበር።
ታዲያ በዚህ ጥያቄና መልስ ውስጥ ፕ/ር ፖል ሄንዝ ለመለስ ዜናዊ አማራ ጠላታችን ነው እያላችሁ ነው። አማራ ጠላታችሁ ከሆነ ከፊት ለፊታችሁ ያሉትን እንደ ወሎ፣ ጎንደር ክፍለሀገራትን እንዴት አድርጋችሁ አልፋችሁ ነው አዲስ አበባ የምትደርሱት ብሎ ጠየቀው። መለስም ይህንን ጥያቄ ሲመልስ “እኛ አማራ ጠላታችን ነው የምንለው የሸዋውን አማራ እንጂ እነዚህ ጎንደር፣ ወሎ ያልካቸውማ እንደ እኛው ጭቁኖች ናቸው ” በማለት መለሰለት።
ይህንን መረጃ እኛ የኢትዮጲያ ነጻ ፕረሶች በ1980ዎቹ መጨረሻና በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ በተለያዩ መጽሄቶችና ጋዜጦች ላይ – በተለይም በወንጭፍ፣ በምንሊክ፣በሳተናው ( የእስክንድር ናቸው) እና በሌሎችም እየተረጎምን አትመነዋል። ምናልባትም ሀብታሙ አያሌው በዚያን ግዜ ብሄረጽጌ ውስጥ የሚዝናኑትን በማሳደድ ላይ የተጠመደ የመንደር አውደልዳይ ነበር እንጂ ፖለቲካውንም የሚያውቅ አይደለም። ምክንያቱም በ1997 ግዜ እኔ ስለፖለቲካ አላውቅም እያለ ሲናገር ሰምታችሁታልና ነው።
ታሪኩ ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬ አይን አውጣው፣ ፈጣጣው ሀብታሙ አያሌው ይህንን መረጃ የነገርካችሁ እኔ ነኝ በማለት ያለእፍንዳች ሀፍረት ሲናገር ሰማነው። የመረጃ ሌባ ማለት ይህ ነው።
2ኛ- በአፋሕድ ውስጥ ስለነበረው ሰርጎ ገቦችን የማጋለጥ ሁኔታን በተመለከተም ሀብታሙ አያሌው As if እሱ እነዚህን ሰርጎ ገቦችን ያጋለጠና የታገለ አድርጎ የገለጸበት ቅጥፈት ሌላኛው የማሳያ ማስረጃዬ ነው።
በአፋሕድ ውስጥ ሰርጎ የገቡትን አምስተኛ ረድፈኞችን ያጋለጠውም ሆነ አምስተኛ ረድፈኛ ብሎ የፈረጀው ሀብታሙ አያሌው አይደለም። ይህም እልም ያለ ቅጥፈት ነው።
ይህን ጸሀፊ ጨምሮ የአፋሕድ የውጭ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆንን እነ ዶ/ር አምሳሉ አስናቀ፣ ወንድም ኡመር ሻፊ፣ ወንድም ኤርሚያስ ሺበሺ እና መሰል እና ዛሬ አንድነይ በሚል ድርጅት ስም የሚንቀሳቀሱ 11ዱ የአፋህድ የውጭ ድጋፍ አስተባባሪ አባላት ናቸው ስያሜውን ያወጡት።
የሰርጎ ገቡን የብአዴን ኤጀንት በማጋለጥ የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ውይይት በመጥራት ይፋ ያደረገውም ይህ ጸሀፊ ነው (ጋሻ ሚዲያ) እንጂ ፈጽሞ ሀብታሙ የሚባል ነጋዴ አይደለም።
ዛሬ ግን ይህንን ሂደት ደጋግሞ ደጋግሞ በመግለጽ እራሱን ልክ እንደ አንድ እነዚህን ሰርጎ ገቦችን እንዳጋለጠ፣ ስማቸውንም እንደፈረጀና እንደታገለ አደርጎ ሲገልጽ መስማት እጅግ ይቀፋል። የሚቀፈው ለእኛ ነው እንጂ ቆሻሻን ጌጡ ላደረገው ሀብታሙ አያሌው አይደለም።
እናም ይህም Just ለማሳየነት ያህል ቀንጭቤ ያቀረብኩት እንጂ ሀብታሙ አያሌው የሚባለው ግለሰብ ገንዘብ አለ በተባለበት መድረክ ሁሉ ድምጽና አቋሙን እየሸቀጠ ለሚኖረው ሰው Daily Basis የሚገልጻቸውን በቅጥፈት፣ በስርቆት፣ በክህደትና እርሰበርስ በመጣረስ የተሞላ ታሪኩን ለማቅረብ ጊዜና ስፍራ አይበቃኝም።
In short Summarize ለማድረግ- ሀብታሙ አያሌው ማለት ጥሩ ክፍያ እስከተከፈለው ድረስ ሚስቱን አሳልፎ የሚሸጥ በአፍቅሮተ ንዋይ ምህዋር ላይ የሚሽከረከር ነፍስ ያለው ሰው ነው።
ደጋግሞ ሲገልጽ የምትሰማቸውን ፋክትስ፣ መርህ፣ አቋም፣እውነትና ታማኝነትና እምነትን በተመለከተ ግለሰቡ በቃላት ደረጃ የሚታወቁና ለግል ስብእና ግንባታነት ጡብ ብድግ እያደረገ የሚጠቀምባቸው እንጂ ፈጽሞ የማይኖራቸው፣ የማያውቃቸውና መተግበር የማይቻለው ሰዋዊ እሴቶች ናቸው።
ለአብነት ያህል በትናንትናው እለት ” በአርበኛ እስክንድር ነጋ ሁኔታ የያዝነው ተጨባጭ ሁኔታ….” በሚል የተለመደ የአድማጭን እይታ መሳቢያ አርእስት ለጥፎ ከአርባ ደቂቃ በላይ ሲዘበዝብ ስለአርበኛው አንዳችም አዲስ ነገር ሳይናገር ግን የታወቁ outdated የሆኑ እና አሁናዊ ያልሆኑ ያለፉ ክስተቶችን ለእሱ በሚመች መልክ እየጨፈላለቀ በመግለጽ የአድማጭን ትእግስት የሚፈታተን ፕሮግራም አቀረበ።
የአድማጭን ትእግስት የሚፈታተን የተባለበት ምክንያት ስለአርበኛው የምናውቀው ተጨባጭ መረጃ ብሎ ለጥፎ ሲያወራ የተደመጠው ግን ቅንጣትም ታህል አዲስ ነገር ያለማቅረቡ ምክንያት ነው።
ታሪኩ እንዲህ ነው። ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ሰኞ እለት ከጀርመን ድምጽ ራዲዮ DW ጋር ባደረገው አጭር ቃለ ምልልስ የሴኩቱሬን ቦታ እተካለሁ በማለት እየተጋጋጠ ያለው ሀብታሙ ነርቩን የነካ ነጥቦች ስለተነገሩ ነው።
አርበኛው በቃለ ምልልሱ ተደጋግሞ ከተቃጣበት የግድያ ሙከራ በእግዜር ቸርነት መትረፉን፣ በጽምዶ ጉዳይ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰራዊት የማያውቀው መሆኑን፣የአፋብን አመራሮች ከትግራዪ ህወሃትና ከኦሮሞው ኦነግ OLA እና መሰል ጸረ አማራ ከሆኑ ኃይሎች ጋር ከመጣመሩ በፊት ጉዳዩን በፖለት ቢሮ አብላጫ ድምጽ ማስወሰን፣ በማዝከላዊ ኮሚቴ ማስወሰን፣ በጠቅላላ ጉባኤ ማስወሰንና በሰራዊቱ ታውቆ ማስወሰን እንዳለባቸው እና ይህንን ሂደት ሳይከተሉ በጥቂት አመራሮች ውሳኔ ብቻ ጥምረቱን ለመፍጠር ድርጅታዊ ስልጣን እንደሌላቸው ገልጻል። ይህ የአፋብን አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የተመረጠ አመራር ሳይሆን ንቅናቄው የአፋሕድ እና የአፋብኃ ውህደት ውጤት እንደመሆኑ እንደመሆኑ መጠን ጊዜያዊ የሽግግር አመራር በምደባ እንደተቀመጠ በመግለጽ ይህ አመራር የህልውናውን ትግል አቅጣጫ የሚያስለውጥ መሰረታዊ የፖለቲካ ውሳኔን በተናጥል የመወሰን ስልጣኑ የለውም ብሎ በመግለጹ የህወሃቱ አሽከር የሆነው ሀብታሙ አያሌው እና መሰል የጽምዶ ካምፕ ያሉ የዘመናችን ሴኩቱሬዎች እጅግ ሲንጫጩ፣ በንዴት ሲንጨረጨሩ ታይታል።
በአጭር አገላለጽ የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ግንቦት 20 ቀን 2023 የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን በመመስረት ችቦ የለኮሰው ታላቁ አርበኛ አፋብን ከአማራ ጠላቶች ጋር ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ሊያደርግ የሚያስበውን ጥምረት ሊያደረገው አይገባም፣ የሚል አቋም በማንጸባረቁ ቀፎው እንደተነካበት ንብ የህወሃቱ ጎራ ሊናደፍ አፉን አሹሎ፣ ወደ ሚዲያ እየተግተለተለ ብቅ አለ።
እናም ጥሩ ክፍያ እስከተከፈለው ድረስ ሚስቱንም ከማከራየትና ብሎም ከመሸጥ ወደ ኃላ የማይለው ሀብታሙ አያሌው አለቆቹን ሊያስደስት እንዴት ወያኔ ተነካችብኝ ብሎ በአርበኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ በእጃችን ያለ ተጨባጭ ማስረጃ… በሚል ማጭበርበሪያ አርእስት ፕሮግራም ከፍቶ እንደ የቁጭራ ሰፈር ሴተኛ አዳሪ ሲሳደብ፣ ሲዛለፍ፣ እና ሲውረገረግ አመሸ።
ለመሆኑ ሀብታሙ አያሌው ለምን እንዲህ ተንጨረጨረ??? የአማራ ፋኖ ከህወሃትና ከOLA ጋር የሚሰራበት ሁኔታ ገና አልተፈጠረም፣ አልተመቻቸም፣አሁን ባለንበት ሁኔታ አይቻልም ብሎ መግለጽ ለምንና እንዴት ሆኖ ነው ሀብታሙ አያሌው Personal የሆነ ያህል እንዲህ ሊያንገበግበው የቻለው ???
ከወያኔና ከ OLA ጋር መስራት አይቻልም ያለውን አርበኛ ላይ outdated የሆነ ታሪክ አምጥቶ ከማመንዠክ ለምንድነው እነዚህ የጽምዶ በቀቀኖች የአማራ ፋኖ ከትግራዪ ህወሃት እና ከኦሮሞው ኦነግ ጋር መስራት የሚችሉባቸው መንገዶች እነዚህ ናቸው እያሉ አይቻልምን በይቻላል ለመተካት ሲጥሩ ከማየት ይልቅ አንዳንዶቹ እስክንድር ከህወሃት ብልጽግናን መረጠ፣ አንዳንዶቹ እስክንድር ህወሃትን መበቀል ስለፈለገ ወዘተ እያሉ ሲናገሩ የምንሰማው???
ምክንያቱም በአማራ ፋኖ እና በህወሃትና በኦነግ መካከል ሊያሰራ የሚያስችል አንዳችም አይነት የፖለቲካ መደላደሎች ስላልተሰሩ ብቻ ነው።
ፋኖን እና ህወሃትን፣ ፋኖን እና ኦነግን አብሮ የሚያጣምሩ የፖለቲካ ስራዎች ሳይሰሩ ዝም ብሎ በጨበጣ ጽምዶ/ጥምረት እያሉ በመጮህ ፋኖን ህወሃት ጉያ ለመወሸቅ ደላሎቹ እነ ሀብታሙ የአእምሮ ማጠቡን ስራ እንዲሰሩ አቅጣጫ ስለተቀመጠላቸው ነው።
ለመሆኑ እንዴት ሆኖ ነው አንድ ሰው ሲቃወመው የነበረን ድርጅት ተመልሶ መደገፍ የሚችለው??።
ለምሳሌ አንድ የህወሃት/የኦነግ ተቃዋሚ የሆነ ግለሰብ እንዴት ሆኖ ነው የህወሃት እና የኦነግ ደጋፊ መሆን የሚቻለው?.?
መልሱ ግልጽ ነው። ህወሃትን ለመቃወም ምክንያት የሆነብህን ጉዳይ ህወሃት ከለወጠች የህወሃት ደጋፊ መሆን ትችላለህ።
ህወሃትን በምታራምደው የፖለቲካ ፖሊሲ ሲቃወምና ሲታገል የነበረ ሰው ህወሃት ያንን ፖለቲካና ፖሊሲዋን ስትለውጥ ህወሃትን መደገፍ ይችላል፣ መደገፍም ይጀምራል። ህወሃት በምትከፍለው የክፍያ ዋጋ ህወሃትን ሲቃወም የነበረ ሰው ህወሃት የክፍያ መጠኑ አሳድጋ ስታሻሽል የህወሃት ደጋፊና አገልጋይ ይሆናል። ህወሃት በምታራምደው ጸረ አማራ ፖሊሲ፣ አማራ ጠላቴ ነው ትርክት ህወሃትን ሲቃወምና ሲታገል የኖረ አንድ አማራ ህወሃት ፖሊሲዋን ስትለውጥ፣ ህወሃት አማራ ጠላቴ ነው ያለችውን ፍረጃ ስህተተኛና ጥፋተኛነታን አምና ስታነሳና ይቅርታ ስትጠይቅ ይህ ሰውም በህወሃት ላይ ያለውን አቋም ለመለወጥ ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ነገር ሳይለወጥና ሳይፈጸም ህወሃትን ሲቃወም እና ሲታገል የነበረ ሰው ብድግ ብሎ Over night Pro- TPLF አፍቃሬ ህወሃት ሊሆን ከቶም አይችልም።
ወደ ፖለቲካው አለም በህወሃት ካድሬነት ስለገባው ወደ ሀብታሙ ጉዳይ ስመጣ – ከኢሕአዴግ አባል ካድሬነት ወደ ኢሕአዴግ ተቃዋሚነት ተሸጋገርኩ ያለው ኢሕአዴግ በሚያራምደው የፖለቲካ ፖሊሲ አንጻር ሳይሆን በሚከፈለው ክፍያና ጥቅማጥቅም እንደ ትግሬዎቹ ሊከፈለኝ ስላልቻለ ብሎ ነው ወደ ተቃውሞ ጎራ የተቀላቀለው። ክፍያና ጥቅማጥቅም አነሰብኝ ብሎ ህወሃትን መቃወም የጀመረ ህወሃት የምትሰጠውን ክፍያና ጥቅማጥቅም ስትጨምርለት ተመልሶ አገልጋይ እንደሚሆነው ሁሉ ሀብታሙ አያሌው ከህወሃት ጋር ትንሽ የተቃቃረውና የተራራቀው በክፍያ ጉዳይ ስለነበረ ዛሬ ህወሃት ያንን የተጣሉበትን ክፍያ ስታስተካክልለት ተመልሶ ለህወሃት አደግድጎ አሸርጋጅና ተላላኪ ለመሆን ቻለ እንጂ ሀብታሙ ከህወሃት ጋር የተራራቀው በምታራምደው ፖሊሲና ፖለቲካዋ ምክንያት ቢሆን ኖሮ አንዳችም የፖለቲካና የፖሊሲ ለውጥ ያላደረገቺውን ህወሃትን መልሶ የሚያገለግልበት ሁኔታና ለህወሃት ብሎ በእውነተኛ አማሮች ላይ ህወሃትን ስላልተቀበሉ ብቻ እስከ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስራ ውስጥ ባልገባ ነበር።
አዎን – ክፍያ ባለበት ሁሉ አነፍንፎ የሚገኘው ህሊናቢሱ ፣ እምነተቢሱና እውነትየለሹ ሀብታሙ አያሌው ህይወት መሽከርከሪያ ኦርቢት ገንዘብና ገንዘብ ብቻ ነው። Nothing more, Nothing Less. . ጠርቀምቀም ያለ ክፍያ ካገኘ ሚስቱንም እስከማከራየትና መሸጥ ደረጃ የሚያደርስ በአፍውሮተ ቁስ ያበደና በዚህ ፍላጎቱም ምክንያት ህይወቱ በክህደት የተሞላ ሰው ነው። እንዴት፣የት? በማን? መቼ የሚሉትን መልሶች በክፍል ሁለት መጣጥፌ ይዤ እቀርባለሁ። አበቃሁ።





















