የአማራን ትግል የመጥለፍ ሴራ፣
በነፃነት ታጋይ ታላቁ እስክንድር ነጋ ላይ የተቃጣው አደጋ እና የሸዋ ፋኖዎች ታሪካዊ ውሳኔ
የአማራ ህዝብ የህልውና እና የስርዓት ለውጥ ትግል በከፍተኛ የውስጥ እና የውጭ ተደራራቢ ሴራዎች ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የትግሉን አቅጣጫ ለማስቀየር እና መስመሩን ለማሳት የሚደረጉ እኩይ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
በቅርቡ ከውስጥ የሚሰሙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ የህውሃትን ድብቅ አጀንዳ በማስፈጸም ላይ የሚገኘው እና በህውሃት የተጠለፈው የአፋብን አመራር፣ በታዋቂው የነፃነት ታጋይ እስክንድር ነጋ ላይ “እንዲገደል፣ ካልተቻለ ደግሞ እንዲታሰር” የሚል ግልጽ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ይህ በነፃነት ታጋዩ እስክንድር ነጋ ላይ የተስተላለፈው አደገኛ ትዕዛዝ በቀጥታ ከህውሃት የሴራ ክፍል የመጣ እንደሆነ በጽኑ ይጠረጠራል። ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት፦
1. የህውሃትን ድብቅ ሴራ ማክሸፍ፦ ህውሃት “ፅምዶ” እና ሌሎች የተቀናጁ የፖለቲካ ማታለያዎችን በመጠቀም የፋኖን ትግል ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል እና የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን ለማስቀየስ ያቀደውን ድብቅ ሴራ እስክንድር ነጋ መስመሩን ጠብቆ በመታገሉ ምክንያት እንዳይሳካ አድርጎባቸዋል።
2. የትግሉን መስመር ማስጠበቅ፦ እስክንድር ነጋ የአማራ ህዝብ ትግል በጊዜያዊ ጥቅሞች ወይም በጠላቶች የተጭበረበረ ጥምረት ሳይጠለፍ፣ ለህዝቡ ሙሉ ህልውና እና ለስር-ነቀል የስርዓት ለውጥ ብቻ እንዲቆም ያደረገው ጽኑ አቋም ለህውሃት እና ለተጠላፊዎቹ ትልቅ ስጋት ሆኖባቸዋል።
3. ተላላኪዎችን የማጋለጥ አቅም፦ የፋኖ ትግል በህውሃት እና በውጭ ኃይሎች እጅ እንዳይወድቅ ወጥ አቋም መያዙ፣ በትግሉ ስም የሚነግዱትን እና የህውሃትን አጀንዳ የሚያስፈጽሙትን ወገኖች ጭንብል ገፎ በማውጣቱ እርምጃ እንዲወስዱበት አፋጥኗቸዋል።
በዚህ አጋጣሚ ጀግኖቹ የሚኒሊክ ልጆች የሆናችሁ የሸዋ ፋኖ አመራሮች የታላቁን የነፃነት ታጋይ የእስክንድር ነጋን ግድያ እና የእስር ትዕዛዝ ፈፅመ አንቀበልም በማለት ውድቅ ማድረጋችሁ ታሪካችሁን በደማቅ ቀለም ፅፋችኋል!
የህውሃቱ ዋና መሐንዲስ ስብሃት ነጋ በግልጽ እንደተናገረው፦ “አማራ ጠላታችን ነው፤ በተለይ የሸዋ አማራ። ድል አድርገን ስንገባ ምን እናድርጋቸው ብለን ተወያየን፣ እናጥፋቸው ተባባለን… አጠፋናቸውም!” በማለት በሸዋ አማራ ላይ ህውሃት የታቀደ የዘር ማጥፋት መፈፀሙን በገሃድ አምኗል።
ስለሆነም፣ ይህን ህዝባችንን ሲያጠፋና ሲያሳርድ በነበረ ገዳይ ህውሃት ሴራ ተጠልፎ የአማራን የነፃነት ታጋይ የእስክንድር ነጋን ግድያ አስፈፃሚ መሆን አባቶችን፣ ታሪክን እና የአማራን ህዝብ በግልጽ መካድ ነው። የነገስታቱ ምድር የሆነችውን ሸዋን ማዋረድ ከቶውኑ አይገባም!
በመሆኑም መላው የአማራ ህዝብ፣ የፋኖ አበጋዞች እና ደጋፊዎች በህውሃት የተጠለፉትንና ትግሉን ለመበተን የሚሰሩትን አፋብን መሰል አካላት ሴራ በንቃት በመከታተል፣ ታጋዮቻቸውን እና የእውነተኛውን ትግል መስመር ከውስጥ አራጆች የመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።






















