“እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።”

 

መገን ሸዋ

ዝንጆሮን የት ዋልሽ ዝንጀሪት ተብላ ስትጠየቅ ምን ያልቧጠጥ ነው ተራራ ያልገፋነው ኮረብታ አለ ?” ብላ መለሰች አሉ

ከእንድ ሰው ጋር ስናወራ ውሎ እንዴት ነበር አልኩት?

ውሏችን እንደ ዝንጀሮዋ ነው አለኝ:: በቀላሉ አማሪኛ ምን ያልተሞከረ ነገር አለ ለማለት ነው!!

አቅመቢሶች እስክንድርን ጥግ ለማሲያዝ በሁለት መንገድ በሰፊው ተጓዙ!!

 አንደኛው መንገድ

“አሳውን ለማያዝ ምንጩን ማድረቅ” በሚል ቢሂል በዚህ አንድ አመት ውስጥ በሰፊው ሄዱበት

ከዚህ የተነሳ የእስክንድር ደጋፊ ናቸው የሚባሉት ሰዎች ቋንቋ ለመደባላለቅ ያልተጠቀሙት መንገድ ያለጠፉት ስም የለም! እኔ ደግሞ ጎበዝ መዝገቡ ነኝ እመዘግባለሁ

የእስክንድር ደጋፊዎችም ቀላል ያልሆነ የቋንቋ መደበላለቅ ግጠማቸው:: ረጅም የዝምታ ጊዜም አሳለፉ በመገፋፋት ጊዜን አባከኑ በዚህ ጊዜ ነበር አቅመቢሱ አቅም ያገኙት::

ለምሳሌ አብዛኞቹ የእስክንድር ደጋፊ ናቸው የሚባሉት አካሎች የሀብታሙ አያሌውን አይነት ሰው ሲታመም ያስታመው ሲከፋው አጽናንተው ሻ ሲለው አዝናንተው! ከዚያም አልፈው

የእውቅና ዝግጅት አዘጋጅተው ካባ ያለበሱት እህትና ወንድሞች ናቸው!!” አለማህ ወንድማችን “ብለው በክብር ቆመው ያጨበጨቡ በተለያዬ መንገድ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካሎች ነበሩ ምን ያደርጋል ቅሉ የእስክንድር ደጋፊ በመሆናቸው ሀብቲሽ የተሰጠውን ተልእኮ ለማስፈጽም ለሁሉም ስም ከመስጠት አልፎ እስክንድርንና የእሱ አይነት አመለካከት ያላቸውን ሰዎች “አንጃ” የሚል ስም በመስጠት እርምጃ እንዲወሰድባቸው አፋብን ጥያቄ ጠየቀ::
ልብ አድረጉ ዋናዎቹን ባላንጣዎች እነ መአዛ መሀመድን:አሳዬ ደርቤንና ‘ፈኖ ቢያሸንፍ የደብረውርቅ አስተዳዳሪ መሆን ያንሰኛል’ ያለውን ይልቃል ጌትነትን ዘንግቼ አይደለም እነሱ ቀድሞም ከእኛ ጋር ባለመሆናቸው ነው::

“እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።”

ሁለተኛው መንገድ

“እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፤”

ዘካርያስ 13:7

እስክንድር የፖለቲካውን አወዳደቅ ያውቅ ስለነበር የተበታተነውን ሀይል ለማሰባሰብ ፍቅርና መተሳሰብ መደጋገፍ ብሎም ይቅርታ ተጠያይቀው በአንድነት ይጓዘ ዘንድ ዳግም መክነያት ሆኖ ብቅ አለ! ::በዚህ ጊዜ ነበር ሀብታሙ አያሌው ሴፉን ከሰገባው አውጥቶ ቀጥተኛ ፍልሚያ ያካሄደው ! በዚህ ጊዜ ነበር የአፋብን መሪ ነን ባዮቹ አይናቸው የቀላው :: ቀድሞውኑ በእስክንድር ላይ አሉባልታ ሲያሶሩ የነበሩ ቡድኖች በፊት ለፊት ተገልጠው ህግ እያጣቀሱ ዙሪውን መክበብ የጀመሩት :: እረኛው ከተመታ በጎቹ ይበተናሉ ብለው አስበው ዙሪውን እንደ አሞራ የሚዞሩት የዞሩት:: በዚህ ጊዜ ነበር በህውሃት አቅጣጫ ሰጪነት በተፈራ እና በዘመነ ካሴ ቀጪን ትእዛዝ መሳይ የተላለፈው :: እስክንድር ከተመታ እረፍት እናገኛለን መንጋው ይበተናል ብለው ያሰቡት !! እንግዲህ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነውና ነገሩ!! ከእስክንድር ይልቅ ደብረጺዮን ወይም ጃል ማሮ ይሻላል ብለህ ካሰብህ ምርጫው የአንተ ነው እኔ ግን

“ከአማራ ይልቅ ሱዳን ይሻለኛል” ያለኝን ደብረጺዮን ከድል በኃላ ስለ ህገ መንግስት መቀዬርና ስለ ግዛት እና ማንነት እንግባባለን ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል:: ” ከድል በኃላ ሻይ እየጠጣን የወልቃይቲን ጉዳይ እንፈተዋለን ” የሚል የሞኞች ተረት ልቀበል አልችልም!!

“ደግሞ የሰላሜ ሰው የታመንሁበት እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።” — Psalms 41:9

እስክንድር ሆይ ኢየሱስን የሸጠው ሰው ከአስራ ሁለቱ አንዱ ነበር አብሮ አንጀራን የቆረሰ የበላ “ከአንተ በፊት የእኔን ሞት ያድርገው” ያለ ሐዋሪያው ነበር :: ወንድምዬው አንተን እየመከርሁ አይደለም ግን በብዙ መከራ ውስጥ በመሆንህ ቃሉን እንዳትረሳ እያስታወስኩህ ነው እንጂ::

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.