ሰላሳዎቹ አማራዊያን የፖለቲካ እስረኞች…..
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
ሲታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሆነው ነው። ሁሉም ከሶስት አመት በላይ ታስረዋል። ሁሉም የተያዙት በመጋቢት፣ ሚያዚያና ግንቦት ወር 2015 (2023) ሲሆን የአማራ ክልል በታላቅ ሕዝባዊ አመጽና ተቃውሞ እየተናጠ የነበረበት ወቅት ነበር። አገዛዙ Anticipated ያደረገውን ሕዝባዊ ትግል እንዳይፈነዳ እነዚህን አመራሮችን እያደነ ማሰር ነበረበትና እያደነ አሰራቸው። ግን አላማውን ፈጽሞ አላሳካም። ከአገዛዙ አፈና እና አፈሳ ያመለጠው ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ በግንቦት 12 ቀን 2015 ህልውናውን ባወጀው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር አማራ ከአገዛዙ ጋር በነፍጥ መፋለም ጀመረ። እናም የአገዛዙ ፖለቲከኞችን አስሬ ትግሉ እንዳይፈነዳ አደርጋለሁ ስሌት ሳይሰራ ቀረና ከሸፈ።
ወደ እስረኞቻችን ልመለስ። ሲታሰሩ በመቶ የሚቆጠሩ ነበሩ። ከሶስት አመት የግፍ እስራት በኃላ 300 ያህሉ ያልፈጸሙትን ወንጀል እንደፈጸሙ ተናዘውና ዳግም በጸረ መንግስት መስመር ላይ ላለመሰለፍ ቃል ገብተውና ፈርመው በአዲሱ 2019 ዋዜማ ላይ መፈታት የቻሉ ሲሆን 30ዎቹ ግን ፈጽሞ አናደርገውም በማለት በእስር ቤት ለመቅረት ቻሉ።
ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 300 ያህል አማራዊያን የፖለቲካ እስረኞች ፈጽሜያለሁ ብለው በመፈረም የተፈቱበት የኑዛዜ ሰነድ እና 30ዎቹ ደግሞ አንፈርምም በማለት በእስር ለመቆየት የተገደዱበት የይቅርታ መጠየቂያ ሰነድ እና የእነዚህ 30ዎቹ ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል⇓
“በአማራ ክልል ፅንፈኛው ቡድን በሚያደርገው ትግል ላይ መሳተፌ ስህተት መሆኑን በማመን መንግሥትንና ሕዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ። በክልሉ ለጠፋው ሕይወት (በአሀዝ ተጠቅሷል) እና ለወደመው ንብረት (በአሀዝ ተጠቅሷል) ኃላፊነት እወስዳለሁ። ሁለተኛ በእንዲህ ያለ ፀረ-ሰላም ተግባር እንደማልሳተፍ ቃል እየገባሁ፤ ይህንን አድርጌ ብገኝ መንግሥት ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስድብኝ በፈቃዴ እፈርማለሁ!”
ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው እና አቶ ዮሀንስ ቧያለውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ይህንን ሰነድ ‘አንፈርምም’ በማለት መለየታቸው ተረጋግጧል። አንፈርምም ያሉ የ30 እስረኞች ሙሉ ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. መስከረም አበራ
5. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
6. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማሪያም
7. መሰረት ቀለመወርቅ
8. አለልኝ ምህረት
9. አባይ ዘውዱ
10. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
11. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
12. መንበር አለሙ
13. ማይክ መላከ
14. እስክንድር ሸፈራው
15. ሲሳይ መልካሙ
16. በላይ ሲሳይ
17. አሳምነው ታደሰ
18. መሰለ ቸሩ
19. አሱባለው በለሰ
20. ዶ/ር ዘሪሁን ባሕሪው
21. ኢ/ር ፍቅዱ ታፈረ
22. ሃሊማ መሐመድ
23. ሕይወት አለማየሁ
24. ጫኔ ዘየደ
25. ያሬድ ግርማ
26. ማረው ስለሺ
27. ታደሰ ወዳይነው
28. ሰለሞን ተፈሪ
29. ሙሉቀን ተስፋዬ
30. ደሳለኝ እጅጉ
ከይቅርታው በፊት የሦስት ወይም የሁለት ቀን ሥልጠና ለመስጠትና ‘አይደገምም’ የሚል ጽሑፍ ያለበት ቲሸርት ለማዘጋጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጻል።






















