– እስክንድር ነጋ ስለ አፋብን እና ከጠላት ሃይሎች ጋር ስላለው ጥምረት – በፖሊት ቢሮው ለገባው ደብዳቤ ውስጥ ያሉት 7 ነጥቦች:-
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ሰሞኑን ለፖሊት ቢሮአችን ደብዳቤ ገብቷል።
1. መረጃ የለም፡ የአፋብን አባላት ከላይ ወደታች የተሰጠን ይፋዊ መረጃ የለም። እየሰማን ያለነው ከመገናኛ ብዙሃን ነው።
2. ጉዳዩ እንዴት አደገ? ይህ ጉዳይ ለወራት በአሉባልታ ደረጃ ነበር። በተለይ ህወሃትን የሚመለከት ጉዳይ አፋብን ከመመስረቱ በፊትም አየር ላይ ነበር። አሁን ግን ባለፉት 2 ሳምንት በድርጅቱ ጥቂት ከፍተኛ አመራሮች “አልቆሏል” እያሉ ነው።
3. ቀይ መስመራችን ምን ነበር? አፋብኃ እና አፋሕድ ተዋህደው አፋብን ሲመሰርቱ ርዕዮተ ዓለም
(ideology) ብዙ ልዩነት ነበረን። “የድርጅቱ ርዕዮት የአማራ ብሔርተኝነት ይሁን” vs “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለውን እንኳን ለአንድነት ብለን አሳልፈን ሰጥተናል።
አንድ ነገር ላይ ግን በቀይ መስመር ተስማምተናል – ከህወሃትና ህወሃትን መሰል ሃይሎች ጋር ያለው ግንኙነት ምን መሆን አለበት? የሚለው ላይ። በዚህ ላይ የአፋብን አቋም ተቀባይነት አግኝቷል።
4. የፓሊት ቢሮ የመነጋገር መብት አለው ፣ ማጽደቅ ግን አይችልም፡ ማንኛውም ስራ አስፈጻሚ ከማንኛውም ሃይል ጋር ጥምረት ለማድረግ ማሰብ፣ ማጥናት፣ መነጋገር ይችላል። ደብዳቤው “ለምን ተነጋገራችሁ” የሚል አይደለም።
ቁልፍ ነጥቡ ግን – ሄዶ መነጋገር፣ ማመቻቸት፣ እስከ የመግባቢያ ስምምነት (MoU ) መድረስ ይችላል። ይህ ግን ባይንዲንግ አይደለም። የድርጅቱ ይፋዊ አቋም አይደለም።
5. የደም ጉዳይ ነው – ውሳኔው የሰራዊቱ ነው፡ አሁን በሰላማዊ ትግል ውስጥ አይደለንም፣ በትጥቅ ትግል ውስጥ ነን። በሁለቱም በኩል የኢትዮጵያውያን ደም እየፈሰሰ ነው። እንደዚህ ያለ መሰረታዊ ጉዳይ በቀጥታ ለአባላት ቀርቦ በድምጽ መወሰን አለበት። ይህ በአለም አቀፍ የትጥቅ ትግሎች ተቀባይነት ያለው አሰራር ነው።
6. አመራሩ ጊዜያዊ ነው፡ አሁን ያለው የአፋብን አመራር ከ7 ወር በፊት በምርጫ ሳይሆን በምደባ የፋኖን አንድነት ለማሳለጥ የተዋቀረ የሽግግር አመራር ነው። ድርጅታዊ ጉባኤ አልተደረገም። ስለዚህ የትግሉን ይዘትና አቅጣጫ የሚቀይር እንደዚህ ያለ ውሳኔ ብቻውን ሊወስን ህጋዊና ዲሞክራሲያዊ ቁመና የለውም። ህጋዊ አመራር ቢሆን እንኳን ከክብደቱ የተነሳ ብቻውን ሊወስነው አይችልም።
7. ለታሪክ ግልጽ ይሁን፡ እኛ እንደ አባላት ህጋዊ ጥያቄ አቅርበናል። በዚህ ጊዜያዊ አመራር ውሳኔ ብቻ ከጥላ ስር ካሉ ሃይሎች ጋር ጥምረት ቢደረግ – ብዙሃኑ የአፋብን አባላት ምንም የማናውቀውና በውሳኔው ያልተሳተፍን መሆናችን ለህዝብና ለታሪክ ግልጽ መሆን አለበት። ውጤቱ ከፋ ቢሆን ተጠያቂው አመራሩ ነው።
–ሥርዓት ነቀል ለውጥ
– ስርነቀል ለውጥ
– AmharaResistance
– AmharaGenocide




















