እንቁራሪት ጉድጓዷ ውስጥ ሆና ከምታየው ሰማይ ውጪ ሌላ ሰማይ ያለ አይመስላትም

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

 

ስንታየሁ ቸኮል – ‘’ እስክንድር ከህወሃት ብልጽግና ይሻለኛል’’ አለ ብለህ ስትጽፍ ምን ያህል አእምሮህ ሰውነትህን ማንቀሳቀስ ከመቻሉ በስተቀር የሚሰቢያ ሴሎቹ ድምጥማጣቸው የጠፋበት ሰው መሆንህን ነው ያሳየህው እንጂ እስክንድር ጸረ-አማራዋን ህወሃትን ሲቃወም አቢይ መራሹ ብልጽግና ይሻለኛል ብሎ እንዳልሆነ በእድሜ ከአንተ እጅግ የሚያንሱት የ10 አመት ልጆች የሚያውቁት ሀቅ ነው።

የአንተ ጭንቅላት ውቅር mind set ግን ብልጽግናን የመረጠ ወያኔን ይቃወማል፣ ወያኔን የመረጠ ብልጽግናን ይቃወማል በሚሉ ሁለት ጠባብ አማራጮች የተዋቀር shallow mind set ስለሆነ አንተ ወያኔን አዝለህ ብልጽግናን የታቀወምክ ስትመስል ሌላው ወያኔን የተቃወመ ሁሉ ልክ እንዳንተው ብልጽግናን የተሸከመ ይመስልሀል።

ይህ ከአእምሮ መቀንጨር (እድሜ ሳይሆን ማሰቢያህ አእምሮ መቀንጨር የሚመነጭ ) የሚመነጭ ሸውራራ እይታ ነው።

For your information አንተ፣ ስንታየሁ ቸኮል ከስምንት አመት በፊት ሰኔ 20 ቀን 2018 (2010) አዲስ አበባ ላይ አቢይን እንቀበለው ብለህ ሰልፍ በምታዘጋጅበትና የኢትዮጲያ ሕዝብ አቢይ እያለ ባበደበት ወቅት እንካን እስክንድር ነጋ ” የሽግግር መንግስት ያስፈልገናል፣ እነዚህን የህወሃት ስሪቶችን አናምናቸውም..” ብሎ እራሱን ከመንጋው ጩህት ያራቀ ሰው ነው። አይደለም ዛሬ ስምንት አመት የፈጀ ጭፍጨፋን ከፈጸመ በኃላ ይቅርና ያኔ በአፍላ ዘመን አንተና አንተን መሰል መንጋዎች አቢይ አቢይ በምትሉበት ወቅት እንካን እስክንድር አቢይን እንደ አማራጭ ጊዜያዊ መሪ አይቶት አያውቅም።

አንድ ነገር ልንገርህ- እሱም አእምሮህ የሚሰራ ከሆነ ብቻ ነው መቀበልና መረዳት የምትችለው።

አንተ አይደለም ጸረ አማራዋን ህወሃትን ይቅርና ጸረ ፈጣሪ ነው የሚባለውን ሎሲፈር ማፍቀር፣ መከተልና ማምለክ መብትህ የተጠበቀ ነው። ህወሃትን አፍቅረህ በእንቀልባ አዝለህ መዞር መብትህ ነው። ማንም አይጋፋህም።

አንተ ያዘልከውን ግም ያልተሸከመን ሰው ግን ብልጽግናን ወዶ ነው ብሎ መደምደም ፍጹም መሀይማዊ ድንቁርናን መግለጽ ነው።

ከእሱ ይልቅ ጭንቅላት ካለህ እስክንድር ወያኔን የተጠየፈው ለምንድነው ??

በድሮዋ ወያኔ እና በዘንድሮዋ ወያኔ መካከል ይህንን ያህል ልዩነት እያለ፣ ( ወያኔ አዲስ ስብእና፣ አዲስ አይዲኦሎጂ፣ አዲስ ፖሊሲ ይዛ ከቀረበች ማለት ነው) ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ ያላትን ፖሊሲ ለውጣ፣ ወንጀሎቻን ተናዛና ይቅርታ ጠይቃ ሳለ ለምንድነው እስክንድር የተጠየፋት የሚል argumentative ሙግት ብታቀርብ መልካም ይሆን ነበር።

እስቲ ማን ይሙት የ 7 አመት ህጻን ልጅ የሚረዳውን እውነታ ወያኔን ያልተቀበለ አቢይን የመረጠ ነው ብሎ መግለጽን የመሰለ የድንቁርና ጥግ አለ ???

በነገሬ ላይ ይህ አንተን ብቻ አይመለከትም። የዘመናችን ሴኩቱሬ ካሞፕ ያላችሁን በሙሉ የሚገልጽ ድንቁርና ነው።

እስክንድርን እርሳውና – ሁለቱንም የማይቀበል ሚሊዮን ሕዝብ አለ። ወያኔንም ብልጽግናንም የሚይቀበል ሚሊዮን ሕዝብ አለ። ይህንን ሕዝብ ምን ልትሉት ይሆን?? ወያኔን የማይቀበለው ብልጽግናን ስለመረጠ፣ ስለፈለገ ነው ብለህ የምትደመድመው???

የማሰቢያ ጭንቅላትህ ሴሎች ፍጹም Dormant መሆን እዚህጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የሰው ልጅ ምርጫ ዘርፈ ብዙ ነው። በሀገራችን የፖለቲካ ኮንቴክስት በሁለት ፈረሶች ብልጽግና እና ህወሃት መካከል ብቻ የሚደረግ ምርጫ አይደለም።

የሁለት ፈረሶች ፖለቲካን በማራመድ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠሩት እነ አሜሪካ እንካን ሁለት Dominant ፈረሶች ( ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን) ብቻ አሉ በሚባልበት ሀገር እንካን አንድ ሰው ከሁለቱም ፈረሶች ሌላ ፈርስ እፈልጋለሁ በማለት ከሁለቱም ፓርቲዎች አንዱንም የማይመርጥ አለ።

በኢትዮጲያ ግን በጣም ይለያክ። ሲጀመር የፖለቲካ አውዱ በህወሃት እና በብልጽግና መካከል ብቻ የተሰደረ አውድ አይደለም።

በርካታ የፖለቲክ ኃይሎች አሉ። በርካታ የፖለቲካ አይዲኦሎጂ አለ።

. ፌዴራሊስት
. ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊስት
. አሀዳዊ
. ሕገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ አቋም
. ሕገ መንግስቱን በመቃወም የተመሰረተ የፖለቲካ አቋም — ወዘተ….. አይነት የፖለቲካ ክፍፍል አውድ ውስጥ ባለንበት ሁኔታና አጠቃላይ የፖለቲካ አውዱ በሁለት ፈርሶች ( ልክ እንደ አሜሪካ) ባልተሰደረበት ሁኔታ ጸረ አማራዋን ህወሃት አላዝልም ብሎ መግለጽ የህወሃትን ልጅና ወራሽ ብልጽግናን ከመምረጥ ነው ብሎ ማሰብና መግለጽ ያለህበትን የድንቁርናን ጥግ አስተሳሰብ ከማሳየት የዘለለ – ህወሃትን ያልተቀበለ ሁሉ ኦህዴድን የተቀበሉ ናቸው የሚለውን ሀሳብ ገዢ ሀሳብ እንዱሆን ማድረግ አይቻልም።

ዘመናችን ሴኩቱሬዎች ለመሆን የምትጋጋጡት ሀሰበ ድኩማን ግስጋሶች አንተን ጨምሮ ሀብታሙ አያሌው፣ አሳዬ ደርቤ፣ አንሙት አብርሃ፣ ትንግርቱ ገብረጻዲቅ፣ መአዛ መሀመድ፣ መሳይ፣ ሙሉጌታ ወዘተ… ግሳግሶች ከሎጂክና ከፋክት ጋር የምትተዋወቁ ፣ ስሜት፣ ምኞትና ፍላጎት መር አስተሳሰብ ይዛችሁ አየር ላይ የምትንሳፈፉ – ጽምዶን ያልተቀበለ ሁሉ ኦህዴድ ብልጽግናን የተቀበለ ነው እያላችሁ ስታቀረሹ እየሳቅንባችሁ ነው የምንሰማው እንጂ እያፈርንባችሁም ሆነ እያዘንባችሁ አይደለም የምንሰማው።

እናም እስቲ እንደምንም በልና ወይም እንደምንም ተማማቱና ጸረ አማራዋን ወያኔን ያልተሸከመ፣ እንደ እኛ ለወያኔ መገረድ ያልፈለገ ኦህዴድ መራሹን ብልጽግና መርጦ ለማዳን ነው ከሚለው የህጻን ልጅ ምርጫ ውጡና እናንተ ወያኔን ለማዘል የቻላችሁበትን የወያኔን በጎ በጎ ስራ፣ አላማ፣ ፖሊሲ፣ አይዲኦሎጂን በመግለጽ ለማሳየት ሞክሩ።

ወያኔን ለማዘል የተጠየፍነው እኛ ለምን ወያኔን ማዘል እንደማይቻለን እስኪበቃችሁ እየገለጽን ነው። እስቲ እናንተ ወያኔን አዝላችሁ ያገኛችሁትንና የምትገኙትን ( የግለሰብ ቅንጥብጣቢ ጥቅም እያልኩ አይደለም) እንደ አማራ ህዝብ ትግል ምን እንዳገኛችሁ፣ ምንስ እንደምታገኙ በመግለጽ ወያኔን አዝሎ መጋዝ ለህልውና ትግሉ ያዋጣል የምትሉትን እየዘረዘራችሁ መግለጽ ተማሩ። እሱንም ከቻላችሁ ነው።

በተረፈ ግም ለግም አብረህ አዝግም እንደሚባለው ወያኔ በአንቀልባ አዝላችሁ መዞር መብታችሁ ነው ስንል – ለምትቃርሙት ግላዊ ቅንጥብጣቢ ጥቅም ብላችሁ ሎሲፈርንም የምታመልኩ መሆናችሁን በመግለጽ የእናንተን ሎሲፈር ያላመለከን፣ የእናንተን ወያኔን እሽኮኮ ብሎ ያላዘለን ብልጽግናን መርጦ ነው ብላችሁ ብትላዝኑ የእይታ አድማሳችሁን ጥበት፣ ጉድጋዷ ውስጥ ያለች እንቁራሪት ጉድጓዷ ውስጥ ሆና ከምታየው ሰማይ በስተቀር ሌላ ሰማይ የለም እንደምትለዋ እንስሳ እናንተም በኢትዮጲያ ፖለቲካ አውድ ውስጥ ከህወሃትና ከብልጽግና (Although ሁለቱም በአላማ፣ በአይዲኦሎጂ፣ በፖሊሲ የአንድ ሳንቲም ፍንካች ቢሆኑም) ውጪ ሌላ አማራጭ ኃይል፣ አማራጭ የፖለቲካ ርእይ፣ አማራጭ የፖለቲካ አይዲኦሎጂ የለም የምትሉ አማርኛ ተናጋሪ ጓጒንቸሮች መሆናችሁን ነው እያሳያችሁን ያለው።

የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ከሁለቱ ጸረ አማራ ኃይሎች ህወሃትና ብልጽግና ጥገኝነት ፍጹም በራቀና በተለየ ሁኔታ በራሱ በሁለት እግሩ ቆሞ ታግሎ በሚያታግል አደረጃጀትና አመራር የሚመራ ትግል ነው። አበቃሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.