በልደቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ የህልውና ጥያቄ አይስተናገድም

ፅምዶ፡ የቀጠለው የልደቱ 30 ዓመት የአማራን ህልውና ትግል ታጋይ ድርጅቶችን የማፍረስ ሴራ እና ተልዕኮ ነው

በልደቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ የህልውና ጥያቄ አይስተናገድም። በልደቱ ኢትዮጵያ የአማራን የህልውና ጥያቄ ማንሳት ጽንፈኝነት፣ የአማራን የህልውና ትግል መካድ ደግሞ የፖለቲካ አዋቂነት ተደርጎ ይቆጠራል።

ልብ በሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካ አንድ ብቻ ነው። እሱም አማራን ለማጥፋት የተደራጁ ኃይሎች እና አማራን ለማዳን የሚታገሉ ኃይሎች መካከል ያለው ፖለቲካ ነው። ከዚህ ውጪ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ምንም አይነት ፖለቲካ የለም።

በዚህ አሳብ መሰረት የአማራን ሕዝብ ለማዳን፣ ህልውናችንን ለማስጠበቅ የሚታገለው አንድ እና ብቸኛ ኃይል ፋኖ ብቻ ነው።

ከዚህ ቀደም እነሀይሉ ሻወል የተባሉ ግለሰቦች የአማራ ሕዝብ ህልውናን ለማስጠበቅ በሚል ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመሰረቱትን የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት /መአህድ/ በማፍረስ ወደ መኢአድ በመለወጥ፣ የአማራ ሕዝብ ያለ ተከላካይ ድርጅት ለ30 ዓመት እንዲጨፈጨፍ አድርገውታል።

ዛሬም በልደቱ አያሌው፣ መሳይ መኮንን፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ መዓዛ መሀመድ እና ሌሎች የጽምዶ ትብብር ደጋፊዎች በተደጋጋሚ “ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ኃይል ብቻ ነው ያለው፣ እኛ የፈጠርነው ጽምዶ እና የፋሺስት አብይ አህመድ አሊ የብልጽግና ጽምዶ” እያሉ ይደሰኩራሉ። ይህ በድንገት የመጣ አባባል አይደለም። ዋነኛ ዓላማቸው መአሕድ ባፈረሱበት መንገድ አማራን ለማዳን የሚታገለውን ኃይል ፋኖን ሁለት ቦታ ሰንጥቆ መቀራመት እና ማጥፋት ነው።

ልክ መአህድ ወደ መኢአድ በመለወጥ የአማራን ሕዝብ እርቃኑን እንዳስቀሩት፣ ዛሬም ጽምዶ ትብብር በሚል የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስጠበቅ የሚታገል ምንም ዓይነት ኃይል እንዳይኖር ለማድረግ ታቅዶ የተፈጠረ የሴራ ጥምረት ነው።
የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስጠበቅ የሚታገለው የፋኖ ኃይል እየጠነከረ፣ ሕዝባዊ ተቀባይነቱም እየጨመረ ስለመጣ፣ “ይህንን ኃይል ለኛ ፍላጎት በሚመች መልኩ እንዴት እንቀራመተው?” በሚል ስውር ሀሳብ ያመጡት አሳብ ነው ጽምዶ የተባለው። ለዚህም ነው ጽምዶን ስትቃወም በቀጥታ “አብይ ይቀጥል” ወደ ፍረጃ፣ ወደ ዘለፋ እና ስም ማጥፋት የሚሄዱት።

ጽምዶ አስመልክቶ ልደቱ የአርበኛ እስክንድር ነጋ ስም የጠቀሰው ለምንድነው?

ልደቱ መርዙን ለመርጨት መድረክ ይፈልጋል። በአሁን ሰዓት ፀረ-እስክንድር ነጋ አቋም መያዝ በብዙ ሚዲያዎች የመጋበዝ መድረክን ይፈጥርለታል። ለዛ ነው እንጂ ከወያኔ ጋር የሚደረግን ትብብር የሚቃወሙ ብዙ ታዋቂ ምሁራን አሉ። አቻምየለህ ታምሩ፣ ዶ/ር ደብሩ ነጋሽ፣ ዶ/ር ተስፋዬ ደመላሽ፣ ዶ/ር አበባ ፍቃደ እና ሌሎችም አሉ። ነገር ግን ልደቱ የአርበኛ እስክንድር ነጋን ስም በመጥቀሱ ብቻ ፀረ-እስክንድር የሆኑት ሚዲያዎች – መሳይ መኮንን፣ ሀብታሙ አያሌው፣ መዓዛ መሀመድ፣ ኢትዮ ፎረም እና ሌሎች – መድረክ እንደሚከፍቱለት ስለሚያውቅ ነው።

እስክንድር፣ ሻለቃ ዳዊት፣ አቻምየለህ ታምሩ፣ ዶ/ር ደብሩ ነጋሽ፣ ዶ/ር ተስፋዬ ደመላሽ እና ሌሎችም ጽምዶን በተመለከተ ያነሱት መሠረታዊ ጥያቄ ትክክል ነው። ድርጅታዊ አሰራርን እና የወያኔን የኋላ ታሪክ ማንሳት ትክክል ነው። እንኳን የህልውና ትግል ይቅርና ስራ እንኳን ለመቀጠር የኋላ ታሪክ ይጠናል። ልደቱ “የህውሃት የድሮ ታሪክ ማንሳት ነው ይለናል” ፤ የድሮ የሚለው ወያኔ ከሦስት ዓመት በፊት ነው ማይካድራ ፣ ጭና ፣ በቆቦ ላይ አማራን የጨፈጨፈው። ለልደቱ በፋኖ እና በዘር አጥፊዎቹ በወያኔ፣ ኦነግ፣ ኦህዴድ መካከል ምንም ልዩነት የለውም።

ወያኔ የተመሰረተው አማራን ለማጥፋት ነው። “ጨቆኝ-ተጨቆኝ” የሚል ትርክት ፈጥሮ፣ የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ፣ ሌላውን ደግሞ እንደ ተጨቆኚ አድርጎ ነው የተደራጀው። ወያኔ በባህሪው በትብብር፣ በውይይት ችግሩን ፈትቶ አያውቅም። ያየህሰው ሽመልስ እና ስብሃት ነጋን ያደረጉትን ቃለ-መጠይቅ ማድመጥ በቂ ነው። ስብሃት “የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርን ለምን ደመሰሳችሁት?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ “ድርጅቱ ፀረ-አማራ በዳቦ ስም፣

ፀረ-ንጉሳዊ ስርዓት አልሆንም ስላለን ነው። የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ስላለን ጥምረት እንፍጠር ብለን ጠርተን በተኙበት ደመሰስናቸው” ይላል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ፣ ጀዋር መሐመድ፣ ጃል መሮ፣ ብልጽግና፣ ኦህዴድ እና ኦነግ በተመሳሳይ “አማራ ጨቋኝ፣ እነሱ ተጨቆኚ” በሚለው አስተሳሰብ የተመሰረቱ ናቸው። እነዚህ ኃይሎች እርስ በእርሳቸው ትግል ቢያደርጉም፣ ስልጣኑ ከኦሮምማ መውጣት እንደሌለበት ይስማማሉ። በዋነኛነት የሚስማሙበት ደግሞ አማራን እንደ ሕዝብ በጠላትነት ማየት ነው።

ከእነዚህ ፀረ-አማራ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ትብብር፣ የተቀደሰውን የፋኖን ትግል፣ ልዕልና ያለውን የህልውና ትግል፣ የህሊና መንገዱን፣ የሞራል የበላይነቱን በሕዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እና የተነሳበትን ዋና ዓላማ – ህልውናውን በመሸጥ፣ የስልጣን ትግል የሚያደርግ ዳግማዊ ሀይሉ ሻወል፣ ዳግማዊ መኢአድ በመፍጠር የአማራ ሕዝብ ህልውና የሚከላከል ድርጅት ወይም ኃይል እንዳይኖር የሚያደርግ መንገድ ነው።

ልደቱ ሀሳብ ሲሰጥ መነሻው ከአማራ ህልውና ትግል ተነስቶ አይደለም። ልደቱ የአማራን ህልውና ትግል ግድ ብሎተ‍ም ፣ ተቀብሎትም አያውቅም። መአህድን ባፈረሱበት መንገድ አሁንም ለአማራ ሕዝብ ህልውና የሚታገለውን ብቸኛውን ኃይል ፋኖን “ብቻህን ይህንን ፀረ-አማራ አገዛዝ አታሸንፍም” በሚል የስነ-ልቦና ጦርነት በፋኖ ላይ በመክፈት፣ የተሰጠውን ስውር ተልዕኮ ለማስፈጸም የመጣ ነው።

አማራ በሕዝብ ቁጥር ከሁሉም የሚበልጥ ነው። 50 ሚሊዮን በላይ የሆነው የአማራ ሕዝብ ብቻውን ይህንን ፀረ-አማራ ስርዓት ከስሩ መንቅሎ መጣል ይችላል። ጥቂት የደርግ ወታደሮች የ3,000 ዓመት በላይ የቆየውን የንጉሳዊ ስርዓት ማፍረስ ችለዋል። 5 ሚሊዮን የማይሞሉት ወያኔዎች 17 ዓመት የቆየውን የደርግ ስርዓት ጥለውታል። 50 ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ ፀረ-አማራ የሆነውን ስርዓት እስከ ፋሺስቱ አብይ አህመድ አሊ የሚመራው ዘር አጥፊ ብልጽግና ድረስ መገርሰስ ይችላል። ይህን ሊያሳካው የሚችለው የአማራን ሕዝብ በዘላቂነት ህልውና ሊያረጋግጥ የሚችለው ብቸኛው ኃይል ፋኖ ነው። ከፋኖ ውጪ ወደ ውጪ።

ድል ለዐማራ ህዝብ!

ሥርዓትነቀልለውጥ
– ስርነቀልለውጥ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.