እንደ ፔንዱለም ወዲህና ወዲያ የሚወዛወዘው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በአስራ አምስት ቀን ውስጥ ሁለት እርሰበርሱ የሚጣረስና የሚደባደብ ስትራቴጂክ የፖለቲካ አቋም በማንጸባረቅ የፖለቲካ ህልውናውን አጨለመ!
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የሀረር ጦር አካዳሚ ምርቁ የሆነው ወታደሩ ሻላቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ83 አመት እድሜው ከአንድ ወታደር በማይጠበቅ ሁኔታ በአስራ አምስት ቀን እድሜ ውስጥ ሁለት እርሰበርሱ የሚቃረንና እርሰበርሱ የሚደባደብ ስትራቴጂክ አቋም በመያዝ የፖለቲካ ህይወቱን በጭቃ ለውሶ ተገኘ።
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ከጸረ አማራዎቹ ህወሃት እና OLA ጋር ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጥምረት ማድረግ አለበት የለበትም በሚለው እጅግ ወሳኝ ስትራቴጂክ ጥያቄ ላይ ሻለቅ ዳዊት ከሁለት ሳምንት የአማራ ሕዝብ በብዛቱ፣ በተዋጊነቱ፣ ባለው ያልተነካ እምቅ ሀብቱና ኃይሉ በኢትዮጲያ ውስጥ ያሉትን የጸረ ብልጽግናን ኃይሎች አሰባሳቢ መሆን ይገበዋል እንጂ እጅግ አወዛጋቢ ከሆኑት ጸረ ኢትዮጲያ ኃይሎች ህወሃትና OLA ጋር ጥምረት መፍጠር የለበትም ብሎ ነበር።
ሻለቃው የመልእክቱን ይዘት ትንሽ ሰፋ በማድረግም የአማራ ፋኖ የጋምቤላ ሕዝብ ንቅናቄን ጨምሮ ከ58በላይ የደቡብ ብሄርብሄረሰቦችን ያቀፈ ጥምረት በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን እራሱን ክአወዛጋቢዎቹ ህወሃትና OLA ጥምረት ማራቅ አለበት በማለት ማንም ሳይጠይቀውና ማንም ሳይጎተጉተው በራስ ተነሳሽነት ጽፎ አሰራጭቶ እንደነበረ አይዘነጋም።
ሻለቃው ይህንን ስትራቴጂክ የሆነውን አቋም በነሀሴ 15 ቀን 2026 ያሰራጨ ሲሆን ከአስራ እምስት ቀን በኃላ በመስከረም 5 ቀን 2026 ባስተላለፈው መልእክት ቀኝ ኃላ ዞሮ የአፋብን አመራሮች ህወሃትን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጲያ ኃይሎች ጋር የሚያደርጉትን ጥምረት ጥቅም አሁን ስለተረዳሁ ድጋፋችን እንዳይለያቸው እላለሁ በማለት በራሱ ላይ የጭቃ ጅራፉን አሳርፋል።
ለመሆኑ አንድ ወታደር፣ በተለይም እድሜው ከ83 በላይ የሆነ አዛውንት ይህንን አይነት ስትራቴጂክ ውሳኔዎችን በየአስራ አምስት ቀኑ እየለዋወጠ ሕዝብን ለማሳሳት መጣር ከሞራል፣ከኃላፊነት፣ ከእድሜና ብሎም ከኃይማኖትስ አንጻር ተገቢ ነውን ???ስለምንድነው ከ 15 ቀን በፊት የአፋብን አመራሮች ከጸረ እማራ ኃይሎች ህወሃትና OLAጋር መጣመርን እደግፋለሁ ብሎ መግለጽ ያልቻለው???
በነሀሴ 15 እና በመስከረም 5 መካከል ባሉት ሀያ ቀናት ውስጥ ምን የተለወጠ ነገር አለ?? ህወሃት አቋማን ለውጣ ነው ?? በአፋብን አመራሮች እና በህወሃት መካከል የተስማሙበት የመስማሚያ ሰነድ ይፋ ስለሆነ ነው?? በአጠቃላይ የጽምዶ ድርጅታዊ ህልውና ተበስሮ ጥምረቱ የተደራጁበትን ሀገራዊ ርእይ፣ አላማ፣ መነሻና መድረሻ፣ በሀገረ ኢትዮጲያ ሉአላዊ ግዛትና አንድነት ላይ ያላቸውን ድርጅታዊን አቋም ይፋ አድርገው ነውና ዛሬ ከሀያ ቀን በኃላ ቀኝ ኃላ ዞሮ እራሱን በራሱ ሊቃወም የቻለው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር ኖሮ አይደለም ግን የአንድ ወሳኝ አርበኛ ድምጽ ስለተሰማ ብቻ ነው የሚል መልስ ነው የምናገኘው።
ከነሀሴ 15 ቀን 2026 እስከ መስከረም 05 ቀን 2026 መካከል ባሉት 20 ቀናት ውስጥ የተከሰተ አዲስ ክስተት ቢኖር የታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ በDW አጭር ቃለ ምልልስ መስጠት ሲሆን በግል ኢጎ የታጠረውና በ83 አመቱ እንደፈለገ ቃሉን መብላት የማይከብደው ሻለቃ ዳዊት ወምደጊዮርጊስ ከሁለት ሳምንት በፊት የሰጠውን አቃም በመቃረን አዲስ አቃም ሊያሳይ የቻለው ከታላቁ አርበኛ ድምጽ መሰማት ተክትሎ መሆኑን ነው መረዳት የቻልነው።
ባሌን ጎዳሁ ብላ በእንትና ላይ ፍልጥ እንደሰካችው አላዋቂ ገልቱ ሴት የ83 አመት አዛውንቱ ወታደርም ገና ለገና ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋን የተቃወምኩ ነኝ በሚል ስሌት እጅግ ወሳኝ በሆነ ሀገራዊ ስትራቴጂክ ጉዳይ ላይ በአስራ አምስት ቀን የተለወጠ እና እርበርሱ የተደባደበ አቋም በማራመድ እራሱን ሊያዋርድ እንደቻለ ስንረዳ በግለሰቡ በሀገር፣ በሕዝብ አጀንዳና በግለሰብ መካከል ያለን ልዩነት መረዳት ያለመፈለግን አቅመ ደካማነት ወይም ሴረኝነትን ልናውቅ ችለናል። ይህ ከአንድ እድሜው ከ 83 አመት በላይ ከሆነና በውትድርናው ዘርፍ እስከ ሻለቃ ደረጃ ከደረሰ እድሜ ጠገብ አዛውንት ፈጽሞ የማይጠበቅና እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው።
በነገሬ ላይ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ አፋሕድና አፋብኃ ፈርሰው አፋብን በመመስረት ደረጃ ከተሳተፉት ሰባት “ሽማግሌዎች” መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ባለፈው ሰኔ 24 ቀን 2026 ለአፋብን ፖሊት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ የድርጅቱ ጥቂት አመራሮች ከድርጅቱ ሕግና ደንብ ባፈነገጠ ሁኔታ በግልና በተናጥል ከህወሃትና ከOLA ጋር ጥምረት ለመፍጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የድርጅቱን መተዳደሪያ ሕግና ደንብ አንቀጽ ጠቅሶ ጽፎላቸው ነበር።
ይህ ማለት ሻለቃው ቀደም ብሎ የአፋብን እመራሮች ከጸረ አማራ ኃይሎች ህወሃት እና OLA ጋር ጥምረት ለመፍጠጠ የሚያደርጉት ግላዊና ቡድናዊ እንቅስቃሴ ተገቢ አይደለም በማለት ሲቃወምና ሲተች የቆየ ሰው ሲሆን ከሳምንት በፊት በDW የተሰማው የታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ አጭር ቃለ ምልልስ መደመጥ ተከትሎ ሻለቃው ቀኝ ኃላ ዞሮ ከራሱ ጋር በመጣላት እራሱን ሲቃወም ማየት መቻል እጅግ አሳፋሪ ተግባር ሆኖ ነው ያየነው።
ምን አለበት እንደዚህ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ቢያንስ ቢሳሳቱ እንኳን በአንድ አቋም መጽናትን ለወጣቱ ትውልድ ቢያስተምሩ፣ በየአስራ አምስት ቀኑ የሚለዋወጥ ስትራቴጂክ ውሳኔዎችን እየወሰኑ እራሳቸውን ከሚያረክሱ?? አበቃሁ።






















