“ትብብሩን የሚቃወሙ የብልፅግና ደጋፊዎች ናቸው” አንዳርጋቸው ፅጌ

 

– ትብብሩ ኮምፓስ የሌለው መርከበኛ ነው

እኔ አዳባይ

የትብብሩን አልፋ ኦሜጋነት ደጋግሞ እየነገረን ያለው የአብይ አህመድ የቅርብ አማካሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ትናንት ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ቀንደኛው ፀረ አማራ አንከር ሚዲያ ላይ ቀርቦ የሰጠውን እረጅም ቃለ ምልልስ በትዕግሥት አዳመጥኩት።

በዚህ ቃለ መጠይቅ አንዳርጋቸው ሁለት ችግሮች እንዳጋጠሙት ንግግሮቹ ያሳብቁበታል።

አንደኛው የአማራ ህዝብ ትብብሩን አለመቀበሉን

ሁለተኛው በባለፈው ቃለ ምልልስ :-

ህወሓትን ተሸንፋለች ብሎ የገለፀበት መንገድ ቁንጥጫ እንዳስከተለበት ።
አንዳርጋቸው በዚህ መድረክ ትብብሩ አስፈላጊውን ሥራ ጨርሶ አብይ አህመድን ሊነቅል መቃረቡን በድፍረት ከገለፀ በኋላ ይህንን የሚቃወሙት የብልፅግና ደጋፊዎች ናቸው ሲል የአማራ ህዝብን በሙሉ ፈርጇል።ለዚህም ያቀረባቸው የማሳመኛ ነጥቦች:-

1.የቀደሙ በደሎችን ቁጭ ብሎ በመወያየት ለመፍታት አይቻልም ።ገዳይም ሟችም ተስማምተው አብይን ብቻ ይጣሉልን
2.የህልውና ትግል አለብኝ ያለ ህዝብ በሆነ አካባቢ ባለ መሬት (ወልቃይትና ራያን) መጠየቅ አያስፈልግም
3.ደብረጽዮን ፋኖንና ኤርትራን እንውጋቸው ብሎ አብይ ሃላላ ኬላ ስብሰባ ላይ ጠይቆት አልተቀበለውም (ደብረፅዮን በፋኖ ፍቅር ወድቋል አይነት )
4.ተቃውሞአቸውን የሚያሰሙ አካላት ምክንያታዊነት (RATIONALITY ) ይጎድላቸዋል በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
እኔ ደግሞ ለአንዳርጋቸው የሚከተሉትን ነጥቦች አንስቼ መሞገት እፈልጋለሁ።
ሀ.የትብብሩ አካላት አላማ አብይ አህመድን ማስወገድ ብቻ ከሆነ የሽግግር ስልጣኑን ማን ይመራል ?በምን መስፈርት?እኔ እኔ በሚል ውዝግብ የእርስ በእርስ ውጊያ ቢከሰትና ወደ ለየለት የህዝብ እልቂት ቢያመራስ? ህወሓትና ኦነግ(OLA) ወደ ተነሱበት የመገንጠል ጥያቄ ቢያመሩስ በምን ሁኔታ ይስተናገዳሉ?
ለ.የአማራን የህልውና ጥያቄዎችን ከተገንጣዮች ጥያቄ ጋር ሚዛን ላይ አስቀምጦ ማነፃፀር ፓለቲካዊ ምክንያታዊነት አለውን ?
ሐ.ትብብሩ ሀገር ለማዳን ከሆነ ህወሓት የራያን ህዝብ ለምን ይገድላል :ያፈናቅላል ይደፍራል :በአማርኛ አትናገሩ አታምልኩ ብሎ ለምን አማራን ያሰቃያል ?ወልቃይትን ለመውረር በአምስት አቅጣጫ ለምን ጦር ለማዝመት ይዘጋጃል ?
መ.በወለጋ በአሩሲ በአምቦና በሌሎችም አካባቢዎች የአማራ ህዝብ ተለይቶ ሲጨፈጨፍ ሲፈናቀልና መንደሮቹ በሙሉ በእሳት ሲጋዩ የትብብሩ አካል የሆነው የኦነግ ክፋይ(የጃል መሮ ጦር) የአማራን ህዝብ ለምን ከጥቃት አይከላከልም?
ሠ.ትብብሩን የሚቃወሙ በሙሉ የብልፅግና ደጋፊዎች ናቸው የሚለው ፍረጃና የአንዳርጋቸው ምክናያታዊነት(Rationality ) ፅንሰ ሃሳብ አይጋጭምን?
መቼም ምክንያታዊነት ትርጉሙ በአንዳርጋቸው ካልተቀየረ በስተቀር Rationality አመክንዮ :ግልፅ ማስረጃዎች እና ከስሜታዊነት የፀዳ ሃሳብን የሚያጠቃልል እስከሆነ ድረስ ሶስት አመት ሙሉ የአብይ አህመድን ጨፍጫፊ ስርዓት ያንበረከከ የአማራ ህዝብና ፋኖ እንዴት የብልጽግና ደጋፊ ሊሆን ይችላል ?? ብዬ እጠይቃለሁ ።
ለማንኛውም አንዳርጋቸው ፅጌ በዚህ የአማራ ህልውና ትግል ውስጥ አበረከትኩት ከሚለው አስተዋጽኦ በላይ ራሱን ለመሸጥ የሚሯሯጥበት መንገድ አስገራሚ ነው ።ሰውዬው ትናንት እንደምናውቀው ዛሬም ሰኞ የሆነ ነገር ተናግሮ ረቡዕ ማስተባባሉ በእኔ ምልከታ IRRATIONALITY ነው።
ዝኒ ከማሁ
ከአዳባይ
ነሐሴ 28/2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.