የአማራ ትግል የመጠለፍ አደጋ፣
የአማራ ህዝብ ለህልውናው እና ለፍትህ እያደረገ ያለው መራራ ትግል በአሁኑ ወቅት በታሪኩ አደገኛ በሆነ የውስጥና የውጭ ሴራዎች መረብ ውስጥ ወድቋል። በቅርቡ ከውስጥ ምንጮች የወጡ አነጋጋሪ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ የትግሉን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ በማሳት የአማራን ህዝብ መስዋዕትነት ለሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች መጠቀሚያ ለማድረግ የተዘረጋው ሴራ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
በእስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈው የመቀሌ ትዕዛዝ እና የሸዋ ፋኖ አቋም፦
ህውሃት ታላቁን አርበኛ እና የነፃነት ታጋይ እስክንድር ነጋን “ተላልፎ መቀሌ እንዲሰጥ” የሚል ትዕዛዝ በፅሁፍ በይፋ አስተላልፏል። ይህ ትዕዛዝ በቀጥታ ለዘመነ ካሴ እና ለጀነራል ተፈራ ማሞ የተላከ ቢሆንም፣ የሸዋ ፋኖ አመራሮች ይህንን አደገኛ እና አዋራጅ ጥያቄ በድጋሜ ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ ታሪካዊና አገራዊ አቋማቸውን አስመዝግበዋል። ህውሃት እስክንድር ነጋን ማስወገድ የሚፈልግበት ዋናው ምክንያት፣ ታጋዩ በኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ላይ ያለው ፅኑ እምነት የህውሃትን አደገኛ የጠለፋ መስመር ሙሉ በሙሉ የሚያበላሽበት ስለሆነ ነው።
የህውሃት የጦር ሰራዊት ውህደት እና የመቀሌው የፅምዶ ስብሰባ፦
ህውሃት “በፅምዶ” ሽፋን የህውሃት (TDF) እና የፋኖ ሰራዊት እንዲጣመርና የህውሃት ጀነራሎች ትግሉን እንዲመሩት ለማድረግ ባቀደው መሰረት፦
- የምሬ ወዳጆን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል።
– በጎጃም በኩል የተወሰነ ኃይል የተቀላቀለ ሲሆን፣ በጎንደርና በሸዋ በኩል ግን አብዛኛው ኃይል ባለመቀበሉ ምክንያት ሙሉ መግባባት ላይ አልተደረሰም።
– በሻቢያ መሪነት መቀሌ ላይ በተካሄደው የፅምዶ ስብሰባ ጦርነቱን በይፋ ለመጀመር ውይይት ተደርጓል። ሻቢያ በወልቃይት በኩል ጦርነቱ እንዳይጀመር በመፈለጉ፣ በራያ በኩል ለመክፈት ስምምነት ላይ ተደርሷል። ለዚህም ብዙ ምክንያት እንዳለ ቢገመትም ለጊዜው ሻቢያ የህውሃትን ወደ ወልቃይት የሚያደርገውን ስግብግብ ጉዞ አልተቀበለውም። ምናልባትም ወልቃይትን እንደያዙ ከአብይ ውድቀት በፊት de facto state መስርተው የመገንጠል አዋጅ እንዳያውጁ ሊሆን ይችላል። ራያ ግን እነ ምሬ ወዳጆ አሳልፈው ስለሰጡትና በዘሩ አማራ የሆነ በስጋት አካባቢውን ለቆ እየወጣ ስለሆነ ይመስላል።
የሀገር መበታተን ሴራ እና የሪፈረንደም አጀንዳ፦
በስብሰባው ላይ ከአብይ አህመድ ውድቀት በኋላ “በትግራይ ህዝብ ላይ ጄኖሳይድ ስለተፈፀመበት ከኢትዮጵያ ጋር የመቀጠልና አለመቀጠል ሪፈረንደም ይደረጋል” የሚል ውሳኔ ተላልፏል። ይህም “እንገንጠላለን” የሚለውን አቋማቸውን በይፋ ላለመናገር የተጠቀሙበት የነጻነት ሽፋን አነጋገር ነው።
በስብሰባው ላይ ከአፋር፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ እና አማራ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከድል በኋላ ከ2018 በፊት ባለው ህገ-መንግስት በመጠቀም ሌሎች ብሔሮችም የመገንጠል ወይም የአብሮነት መስመራቸውን እንዲወስኑ ይደረጋል ተብሏል። በሚያሳፍር ሁኔታ ስለአማራ የወደፊት ሁኔታ አንድም ፋኖ አልጠየቀም። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የወልቃይት ተፈናቃዮች አሉን እያሉ ሲያወሩ አንድም የሞገተ የለም—አልፎ አልፎ የአማራን ጉዳይ (cause) የሻቢያ ተወካዮች ሲያነሱት ከመስማት ውጭ። ሁኔታው የአማራ ተወካይ በሌለበት የተደረገውን የቀደመ የህገ-መንግስት ውይይት ይመስል ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ የአፋርና የኦሮሞ ተወካዮች ከአቋማቸው የመንሸራተት አዝማሚያ ያሳዩ ሲሆን በስብሰባውም አልተገኙም፤ ከሱዳን፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ የተገኙ ያልታወቁ አካላትም በቀጠናው ጉዳይ ላይ መክረዋል።
ለሕዝባችን የቀረበ የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ!
አማራ ሆይ! ትግልህ በህውሃት እና በግብፅ ተላላኪዎች እጅ እየተጠለፈ ነው። ያ ሁሉ ወጣት መስዋዕትነት የከፈለበት፣ ደምና አጥንት የፈሰሰበት የተቀደሰ ትግል በዘመነ ካሴ በሚባል አካል ለጠላት ተሸጧል!
ስለሆነም፦
🛑 ይህንን የተጠለፈ አደረጃጀት በፍጥነት ማፍረስ አለብህ!
🛑 ፀረ-ፅምዶ እንቅስቃሴው በየአቅጣጫው ይፋፋም!
🛑 ከታሪካዊ ጠላታችን ከህውሃት ጋር የሚደረግ ማንኛውንም አይነት እኩይ ህብረትና ጥምረት በፅኑ ተቃወም!
🛑 አብይ አህመድን በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ የህውሃት እርዳታ ወይም ከባንዳዎች ጋር መጣመር አያስፈልግም!
ሀገርህን አድን!
እኛ የእነዚያ ታሪክ ሰሪዎች፣ የሀገር መስራችና የጀግኖች አባቶች ልጆች ነን! ኢትዮጵያን በደማችን ያፀናን ስልጡን ህዝቦች ነን። ከባንዳ፣ ከሀገር አፍራሽ እና ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር የሚደረግ ማንኛውም አይነት ጥምረት በአስቸኳይ ይቁም!
@FL






















