የጽምዶን ጎራ ያተራመሰው የታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ከጀርመን ድምጽ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ

ሴኩቱሬዎች እና ሕወሓቶች በጋራ በንዴት ጨሰው፣ ጦፈው አብደዋል

አማራን የጸረ አማራዋ ህወሃት መጠቀሚያ ለማድረግ እና መጠቀሚያ ላለማድረግ እየተካሄደ ያለ የሀሳብ ፍልሚያ

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

የጽምዶ ጎራ ትርምስምስ ውስጥ ገብታል። Just ከሳምንት በፊት ብልጽግና መስከረምን አያያትም እያሉ ሲፋልሉ የነበሩት እነስታሊን በሳምንት እድሜ ውስጥ አቢይ መጪውን መስከረም እያይም ከማለት በፍጥነት ወደ የጽምዶን ስብስብ ህልውና አልተፈረካከሰም ወደሚል Damage Control ለመግባት ተገደዋል።

ከአህያ ቆዳ የተሰራ ከበሮ የጅብ ጩህት ሲሰማ ሳይበኩት ይጮሀል እንደሚባለው ከአራት ኪሎ በስተቀር አንድም የሚያግባባ አጀንዳ፣ አላማ፣ አይዱኦሎጂና የትግል መነሻና መድረሻ የሌላቸው ስብስቦች በ 19 ደቂቃ ቃለ ምልልስ ብትንትናቸው ወጥቶ የንዴት ሰይፋቸውን ለመምዘዝ ሲገደዱ እያየን ያለንበት ሁኔታ ላይ ነን ያለነው። የንዴቱ ሰይፍ ግን የቃላት ሰይፍ ባይሆን እና መሰየፍ ቢችሉ ስንቱ እውነተኛ አማራ ልጅ በዚህ ሳምንት ብቻ በተሰየፈ ነበር።

የታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ 19 ደቁቃ የፈጀው ቃለ ምልልስ Just summarize ለማድረግ

1ኛ- ተደጋጋሚ ጊዜ ከተቃጣበት የግድያ ሙከራ በአምላክ እግዚአብሔር ቸርነትና ጥበቃ መትረፍ የቻለ መሆኑን….

2ኛ- ጽምዶ የሚባለው ስብስብ የጸረ አማራና የጸረ ኢትዮጲያ ኃይሎች ስብስብ መሆኑን…..

3ኛ- በጽምዶ ውስጥ አለሁ እያለ ያለው የአፋብን አመራር ውሳኔ በፖሊት ቢሮው ያልጸደቀ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያላለፈና ሰራዊቱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ….

4ኛ- የአሁኑ የአፋብን አመራር የህልውና ትግሉን ትራጄክተሪ የሚለውጥና በህልውና ትግሉ አላማ ላይ የፓራዳይም ሺፍት የሚያመጣን ከጸረ አማራና ከጸረ የኢትዮጲያ ኃይሎች ጋር ጥምረት ለማድረግ የሚያስችል ውስኔን በተናጥል ለማሳለፍ ማንዴቱና ስልጣኑ የሌለው፣ በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠ አመራር ሳይሆን በጊዜያዊነት የሽግግር አመራር ተብሎ በምድባ የተቀመጠ አመራር በመሆኑ ይህን መሰል ከባድ ውሳኔን በተናጥል መወሰንና ማስፈጸም የማይችል መሆኑን…

5ኛ- የአመራሩ የቅድሚያ ቅድሚያ አጀንዳዎች ውስጣዊ አንድነትን በማሳለጥ ድርጅታዊ ተቋም መገንባትና ማጠንከር ያለበት መሆኑን እና ወዘተ መሰል የሆኑ ነጥቦችን ነው ያስተላለፈው።

እነዚህ ሀሳቦች ህወሃታዊያኑ ከርእዮቱ ቴውድሮስ ጸጋዬ፣ ስታሊን ገብረስላሴ ጀምሮ እስከ የዘመናችን ሴኩቱሬዎች እነ ጆተኒው ሀብታሙ አያሌው፣ የሮሃ ሚዲያዋ መአዛ መሀመድ፣ እና በዩጋንዳ የተሰገሰጉ ግሳግሶች በጋራ፣ በተናበበ መልኩ እየተቀባበሉ ሁሉም ተንጫጩበት። የርእዮቱ ቴውድሮስ ጸጋዬ እስክንድር ጥምረቱ በታሪክ ከአማራ ጠላቶች ጋር የሚደረግ ስለሆነ አይሆንም ያለው ፍጹም ትክልል አይደለም እያለ እሪታውን አቀለጠው። ምክንያት ብሎ የተናገረው እስክንድር በታሪክ ውስጥ ተዘፍቀን እርሰበርስ እየተበቃቀልን እንድንኖር ስለፈለገ ነው በማለት እሪሪሪ አለ። ከንዴቱ የተነሳም እስክንድር በትግራይ ላይ ጄኖሳይድ ያወጀ እኮ ነው ሲል መቼ? የት ? እንዴት የሚሉትን ጥያቄዎች ሳይመልስ ዝም ብሎ በደፈናው እስክንድርም በትግራይ ላይ ጄኖሳይድ እንዲፈጸም ያወጀ ስለሆነ እና ህወሃትም በአማራ ላይ ጄኖሳይድ እንዲፈጸም ያወጀች ከሆነ እኩል ስለሆንን አሁን አብረው መስራት አለባቸው አይነት አመክኒዮ ለማቅረብ ሲጥር ታየ።

የርእዮቱ ቴዲ በታሪክ ብሎ የጠቀሰው የአማራን የትግራሩ፣ ወይም የአማራና የትግራዩን ህወሃት አሁናዊ ሁኔታን የማይገልጽ ስለመሆኑ እንካን ያ አስተዋዩ ቴውድሮስ ጸጋዬ ማስተዋል ሲሳነው ማየትና መስማት ይገርማል።

የአማራ ሕዝብ እና የትግራዩ ህወሃት መክከል ያለው የጠላትነት Enmity ሁኔታ ቴውድሮስ ጸጋዬ እንደገለጸው የታሪክ ጉዳይ አይደለም። በሁለታችን መካከል ያለው በጠላትነት የመፈላለግና የመፋጠጥ ሁኔታ አልፎ ታሪክ አልሆነም። ታሪክ የሚባለው ያለፈ ክስተት ነው። የእኛ ጉዳይ ማለትም በአማራና በትግራዪ ህወሃት መካከል ያለው በጠላትነት የመፈላለግ ሁኔታ አሁን ዛሬ Actively ያለ ፍጥጫና ትንቅንቅ ነው።

እንዴት ለምትሉ በአጭሩ ላስረዳ።

1ኛ- ህወሃት በ1967 በደደቢት በረሃ አማራ የምታገለው ጠላቴ ነው ብላይ በማንፌስቶዋ ላይ የጻፈቺው አቋም ዛሬ ድረስ አብራት ያረጀና ያለ አቋም ነው። ይህ አቋም በስህተት የተያዘ አቋም ነው በሚል በግልጽና በይፋ ተናዛና ይቅርታ ጠይቃ የአቋም ለውጥ ማድረጋን እስከዚህች ሰከንድ ድረስ የገለጸቺው ነገር የለም። ስለሆነም Practically ዛሬም አማራው ለህወሃት የምትታገለው ጠላታ ነው። ፋይሉ ክፍት እንዳለ ነው ያለው እንጂ ፋይሉ አልተዘጋም። ያልተዘጋ ፋይል ታሪክ ሳይሆን የእለት ተእለት ጉዳይ መፈጸሚያ አጀንዳ ነው የሚባለው።

2ኛ- በእኛ እና በህወሃት መካከል ያላለቀ የመሬት ይገበኛል ጥያቄን የወለደ ውዝግንና ፍጥጫ ዛሬም Actively እንዳለ ነው። ህወሃት የአማራ የሆኑ ግዛቶችን ወልቃይት ጠገዴና ራያን ዛሬም ጭምር ከአማራው እጅ ተነጥቀው ለእኔ መመለስ ያለባቸው በወረራ የተያዙብኝ ግዛቶቼ ናቸው ባይ ነች። ይህም በመካከላችን ያለ ሁለተኛው ያልተዘጋ ፋይል ነው።

3ኛ- ሶስተኛው ያልተዘጋና አሁንም Active የሆነው የጠላትነት ፋይል የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ ምንጭ የሆነው ሕገ መንግስት ነው። ለእኛ ለአማራዊያን ይህ ህወሃት ሰራሹ ሕገ መንግስት የመገደያችን፣ የመጨፍጨፊያችን፣ የመጨቆኛችን ምንጭ ሆኖ ሕዝባችንን እያስፈጀ ያለ ሕገ መንግስት ነው። ለህወሃት ደግሞ ሕገ መንግስቱ እንከን የለሽ፣ የማይሻር፣ የማይለወጥ የመጽሀፍ ቅዱስ ያህል የሆነ “ቅዱስ” ሕገ መንግስት ነው። ይህም ያልተዘጋው ሶስተኛ ፋይል ነው።

4ኛ- ከአራት አመት በፊት በማይካድራ ከ1600 በላይ አማራዊያንን የጨፈጨፈችበት እና በምስራቅ በኩል ከቆቦ እስከ ደብረ ሲና ድረስ ባሉት ከተሞችና መንደሮች ላይ የፈጸመቻቸው አሰቃቂ ወንጀሎች ተጠያቂው ለፍርድ ቀርቦበትና ተቀጥቶበት፣ እና ለወደመው ሀብትና ንብረት ካሳ ተከፍሎ በእርቅ የተዘጋ ፋይል ሳይሆን ዛሬም ጭምር Active የሆነ ፋይል ነው።

እንግዲህ የርእዮቱ ቴውድሮስ ጸጋዬ እነዚህን ወሳኝ የሆኑ አራት አሁናዊ ነጥቦችን አሁን ዛሬ ያሉ ፋይሎች መሆናቸውን ባለመቀበልና ወይንም ሆን ብሎ በመጋረድ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ በታሪክ ላይ ተቸንክረን እርሰበርስ እየተበቃቀልን እንድንኖር ይፈልጋል በማለት በብስጭት ሲናገር የተሰማው።

ቴዲ ይህንን መረዳትና ማስተዋል ተስኖት የተናደደ አይመስለኝም። በአጭሩ ለጥይት ማብረጃነት የተፈለገው የአማራ ፋኖ ሰራዊት ከእጁ ያመለጡ ሆኖ የማየቱ ጉዳይ ክፉኛ እንዳበሳጨው ነው መገመት የምችለው።

ምክንያቱም ይህ ሁሉ የጽምዶ/ጽምዶ/ጥምረት ጋጋታና ግርግርታ ዋና አላማ በአራት ክፍለ ሀገር ተንጣሎ ያለውን ከ40 ሚሊዮን በላይ የአማራን ሕዝብ ጉልበቱን፣ ህይወቱን፣ ገንዘብና ሀብቱን በገፍ ተጠቅሞ ከተቻለ አራት ኪሎ ቂብ ለማለት ካልተቻለ ደግሞ As a king maker ምስለኔያቸውን ዘመነን አራት ኪሎ አስቀምጠው ልክ እንደ ታምራት ላይኔ እያዘዙ ጉዳያቸውን ለማስጨረስ የያዙትን እቅድና ፕላን የታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ አቋም ከእጃቸው እያወጣባቸው ስለሆነ ነው የንዴታቸው ምንጭ እንጂ ከህወሃት ጋር አብሮ መጣመር አይቻልም ስለተባሉ ይህን ያህል በንዴት ጦፈው ሲንጨረጨሩ አናይም ነበር።

በንዴቱ ቴዲ ብቻውን አይደለም። ብዙ አጃቢዎችና ተናዳጅ ተከታዮች አሉት። እነ ስታሊን፣ ሀብታሙ፣ አሳዬ፣ መአዛ፣ ይልቃል፣ አብርሃም፣ ትንግርቱ፣ እና ዩጋንዳ የተሰገሰጉ ግሳግስ ኮልኮሌዎች በሙሉ ለአማራ ሕዝብ ህልውና እና ጥቅም ከተቆረቆረው እውነተኛው አማራ ታላቁ እስክንድር ነጋ ይልቅ ጸረ አማራዋ ህወሃትና ኦነግ በልጠውባቸው በአርበኛው ንግግር በንዴት ጨርቃቸውን ጥለው ከእነ ቴዲ ጋር ያበዱ ሴኩቱሬዎች አሉ።

በእኛ እና በህወሃት መካከል ያልተፈቱ ችግሮችን ሳንፈታ በአንድነት መጣመር አይቻለንም ተብለው እውነቱ ሲነገራቸው እሺ ብለው በመቀበል ሁለታችንን ሊያቀራርቡ ያልቻሉትን ተግዳሮቶችን ከመፍታት ይልቅ ለምንድነው ሙጭጭ ብለው በንዴት ወደ ስድብ ሊገቡ የቻሉት???

ከዚህ በፊት ደብረጺዮን ከሚጎራበተን አማራ ይልቅ የሱዳን ሕዝብ ይቀርበናል፣ ይበልጥብናል እያለ ከተናገረ አምስት አመት አልሞላውም። እነ ጄ/ል ማንጁስ ከአማራ ጋር አይደለም ተሰልፎ አብሮ መታገል ይቅርና ብንሞት እንካን አብረን አንለምንም እያለ ሲናገር የተሰማው Just ከወራት፣ ምናልባትም ከአመት በፊት ነው።

ታዲያ ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል እንደተባለው ህወሃት ለአማራ ሕዝብ ባላት ንቀት የተነሳ እንደፈለግኩ አድርጌው፣ ጨፍጭፌው፣ አስጨፍጭፌው በምፈልግበት ሰዓት ና እና አብረን እንጣመር ስለው በደስታ እየፈነጠዘ ከእኔ ጎን ይሰለፋል በሚል የተማመነችበት ኃይል ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ብቅ ብሎ ነገሮች ሁሉ የሚፈጸሙት በሕግ ፣ በስርዓት፣ በመርህ እና በህጋዊ አግባብ ነው ብሎ ሲናገር ይህንን በእጃችን አስገባነው ብለው የቋመጡትን የሰው ኃይል፣ የሎጀስቲክስ ምንጭ ከእጃቸው ያስወጣባቸው ክስተት በመፍጠሩ ነው ህወሃታዊያኑ በንዴት የጦፉት። የጎባጣ አሽከር ዘወትር አጎንብሶ እንደሚባለው ጌቶቻቸው የተናደዱበትን አርበኛ የእኛዎቹ ሴኩቱሬዎች ደግሞ ከጌቶቻቸው ይበልጥ አረውና ጨሰው በአርበኛው ላይ ያልተገራ ምላሳቸውን፣ እና የጭቃ ጅራፋቸውን ለማሳረፍ ሲፍገመገሙ ለማየት በቃን።

በአማራ ፋኖ እና በህወሃት፣ በአማራ ፋኖ እና በኦነግ OLA መካከል ሊፈጠር የሚችለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ቅርርበትና ብሎም ጥምረት የስልጣን ጥማትና የቁስ ሰቀቀን ባሳበዳቸው እፍኝ በማይሞሉ ጥቂት ግለሰቦች ፍላጎትና ፍቃድ ሳይሆን አግባብ ባለው መልኩ ባለጉዳዩ የአማራ ፋኖ ሰራዊት፣ የአፋብን ማእከላዊ ኮሚቴ፣ የአፋብን ፖሊት ቢሮ እና የአፋብን የሽማግሌዎች ምክር ቤት አውቆት ዘክሮበት፣ መክሮበትና አጥኚ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ጥናት ከተደረገ በኃላ:-

1ኛ- ህወሃት እና OLA ማራገፍ የሚገባቸውን እንዲያራግፉ ተደርገውና መቀበል ያለባቸውን አዳዲስ ቅደመ ሁኔታዎችን ተቀብለው

2ኛ- በትግሉ የመጨረሻ ግብ ላይ የጋራ መግባባትና የጋራ አላማ ይዘው

3ኛ- በንስሀ/ በኑዛዜና በይቅርታ የሚታለፉ ጸረ አማራ ወንጀሎቻቸውን ተናዘው፣ ይቅርታ ጠይቀውና ተጠያቂዎችን ለሽግግር ፍትህ ለማቅረብ ተስማምተው።

3ኛ- በህወሃት በኩል በወልቃይት ጠገዴ፣ ራያና በሕገ መንግስቱ ላይ ያላትን የሞቼ እገኛለሁ አቋም ለውጣ- ከአማራው የምትጠይቀው ስንዝር መሬት ያለመኖሩን በይፋ ለሕዝባና ለሕዝባችን አውጃ። በ OLA በኩል ሀገረ ኦሮሚያን እመስርታለሁ የሚለውን ቅዠት ለህዝቡና ለሕዝባችንን መተውን በደባባይ አውጆ፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት የሚለውን ቅዠቱን እርግፍ አድርጎ መተውን ይፋ አድርጎ ሲጨርሱ መጀመሪያ ታክቲካል ግንኙነት በመፍጠር በሂደት ወደ ላቀ ስትራቴጂካል አጋርነትና ጥምረት ደረጃ ማድረስ ይቻላል እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ ሆይ ሆይታ የሚፈጠር ቅንጣት ታህል ጥምረት በሉት ጽምዶ የሚፈጠር አይሆንም። ይህ ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም።

የጽምዶን ጎራ በድንጋጤ ያፍረከረከው የአርበኛ እስክንድር ነጋ ቃለ ምልልስ ብቻ አይደለም። እሱ ዋናው ሆነ እንጂ መጀመሪያ የአፋብኑ ሰብሳቢ ዘመነ ካሴ ለ DNE Africa ሚዲያ በሰጠው ቃለ ምልልስ በኤርትራ ላይ ክህደት በመፈጸም ነው ንቃቃቱ የጀመረው። ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም፣ ምንም አይነት ድጋፍ እስካሁን አግኘተን አናውቅም ብሎ በኤርትራና በህወሃት መካከል የተፈጠረውን ጽምዶ ሰብሳቢ ነው እየተባለ የኤርትራን ህልውና እና ሚናን ሲክድ ስንጥቃቱ በጽምዶ ውስጥ ጀመረ። ለጥቆም ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ አንዳርጋቸው ጽጌ ህወሃት ከፋኖ ጋር እንዲያማልደው ሻእቢያን ለምኖ ነው ሻእቢያ መሀል ሆኖ ያገናኛቸው ብሎ የአጸፋ ቦምብ ጣለ። ሰልሶም የህወሃቱ ምክትል አማኑኤል አሰፋ በብስጭት ለመድ የለበሰ ተኩል፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጄኖሳይድ ያስፈጸመ ጄኖሳይደር ሲል ስንጥቃቱን አንቦረቀቀው።

በኦሮሚያ ያለው ኦነግ OLA እኔስ ከማን አንሼ በሚል ዘመነና አስረስ የሰጡትን የአብረን ነው የምንሰራውን ንግግር እጅግ የሚያሳፍር መሰረተቢስ የፈጠራ ወሬ ነው ሲል ውድቅ አደረገ። ከጽምዶ መለየቱን ማሳያ ሆነ ማለት ነው።

ደብረጺዮን ደግሞ ከኦሊሴጎን አባሳንጆ ጋር ሲገናኝ ያ የትግራይ ህልውና በብልጽግና መቃብር ላይ ነው የሚረጋገጠው ብሎ ከሳምንታት በፊት የደነፋ ሰውዬ ለመደራደር ዝግጂ ነኝ፣ የመደራደሪያ ነጥቦቼም እነዚህ አምስት ናቸው ብሎ ለኦባሳንጆ አስረከበ። ይህንን የሰማው OLA በብርሃን ፍጥነት እኔስ ከማን አንሼ በሚል እሱም የመደራደሪያ ነጥቦቹን ለብልጽግና ላከ።

ይህ ሁሉ የሆነው በሶስትና አራት ቀናት ውስጥ ነው። አሁን አገዛዙን በትጥቅ ትግል ለመጣል ተሰባስበው ጽምዶ የሚባል ጥምረት ፈጠሩ ሰባት ድርጅቶች ውስጥ ህወሃት እና ኦነግ የድርድር መንገድ መምረጣቸውን አሳወቁ። ከሰባቱ ውስጥ ሁለቱ ሲቀነሱ ነፍስ ያለው ቀሪ አፋብን ብቻ እና ብቻ ነው። ቀሪዎቹ ONLF እስካሁን የጽምዶ አባል መሆኑን Confirm አላደረገም። አፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ከሚወክሉት ሕዝብ ብዛት አካይ ተጽእኖአቸው እምባዝም አይደለም። ሻእቢያ እራሱን የቻለ ሉአላዊ ሀገር የሚመራ መንግስት እንደመሆኑ መጠን ከሃላ ሆኖ ቢደግፍ እንጂ አገዛዙን ለመጣል ከተሰባሰቡት ሰባቱ ታጣቂዎች ጋር ሆኖ አቢይን ለመውጋት ጥምረቱን አልተቀላቀለም። እናም አፋብን ብቻዋን ጉሙዙን ታቅፋ አየር ላይ ቀርታለች። በአፋብን በኩል ታላቁ አርበኛ ብቅ ብሎ መሆን ያለበትን የመግለጹ ጉዳይ የቀረውን የጽምዶ ውስጣዊ አንድነት ፍርክርኩ እንዱወጣ አደረገው። እናም ሳይወለድ ገና በፕሮፖጋንዳ ጩህት መንግስት የሆነ ያህል አስመስለው ፕሮፖጋንዳ ሲነዙ የከረሙት ህዋታዊያን እና የእኛዎቹ ሴኩቱሬዎች የብሶትና የንዴት መወጫ ታላቁን አገኙና ብሶታቸውን ለመወጣት ሲንጫጩበት ነው መስማት የቻልነው።

ይህ ግብግብ አማራን በጠላትነት ፈርጆ ለድፍን 35 አመታት በጨፈጨፈውና ባስጨፈጨፈው ጸረ አማራ ሀይል – መልሶ በአማራ ተዋጊ ኃይል የመጠቀም ፍላጎትና የአትጠቀምም ውሳኔ መካከል የሚደረግ የቃላት ፍልሚያ ነው። አዎን አማራን በነገዳዊ ማንነቱ ፈርጀው እና የጸረ አማራ sentiment, ጸንሰው ወልደው ሀገሩን ሙሉ በጸረ አማራ ትርክት ላጥለቀለቁት ጠላቶቻችን የአማራ ወጣት አይደለም ደሙን ላቡን እንካን እንዲያፈስ የሚፈቅድ ትውልድ የለም። ይህ መታወቅ ያለበት ሀቅ ነው። አበቃሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.