ከጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጲያ ከሆኑት ህወሃት፣ ኦነግ፣ ኦብነግና ጉምዝ መሰል ተገንጣይ ኃይሎች ጋር ሄዶ መለጠፍ የአማራን ፋኖ በአስገንጣይነት እና በአሸባሪነት የመፈረጅ አደጋ ደቅኖበታል- እንዴት ነው ከዚህ አደጋ መውጣት የሚቻለው??
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ማርኮ ሩቢዮ ህወሃት መራሹን ጽምዶን/ትብብር ለህልውናን ተገንጣይ እና አሸባሪ ሲል የገለጻቸው ሲሆን የአማራ ፋኖ በአስገንጣይነት እና በአሸባሪነት የመፈረጅ እጅግ ታላቅ አደጋ እንዲደቀንበት አድርጋል።
በእርግጥ ለብዙዎች አደጋው ዛሬ ግልጥጥ ብሎ የታየ ቢሆንም ዘመነ ካሴና ግብረ አበሮቹ የተቀደሰውን የአማራን ፋኖ የህልውናን ትግል ለግል ግለሰባዊና ጥቂት ቡድናዊ ጥቅም ብለው ከጸረ አማራ እና ከጸረ ኢትዮጲያ ከሆኑት ህወሃት፣ ኦነግ እና የጉምዝ ታጣቂና መሰሎች ጋር ያለአንዳች የድርጅቱ አጠቃላይ ስብሰባና ያለአንዳች የአማራ ፋኖ ተዋጊ ሰራዊት ውሳኔና ምክክር ብድግ ብለው ከሸጡበት እለት ጀምሮ የህልውናው ትግል በታላቅ የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ እንደገባ ይታወቃል። ሆኖም ግን አሁን ያየነው ታላቅ አደጋ በህወሃት ተመትቶ መበታተን ማግስት በህወሃት አሰባሳቢነት የተሰባሰበው ይህ ጽምዶ/ትብብር የሚባለው ስብስብ በአሜሪካ መንግስት “..ተገንጣይ እና አሸባሪ..” ተብሎ የመፈረጁ ጉዳይ ሲሆን ፍረጃው ለህወሃት – የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው እየሞተች ላለቺው ህወሃት ስሜት የማይሰጥ ሆኖ ቢገኝም የ50/60 ሚሊዮን የአማራን ሕዝብ ህልውናን መክቶ ለመጠበቅ ለተነሳው የአማራ ፋኖ እጅግ ሲበዛ ታላቅ የህልውና አደጋ ሆኖ ነው የታየው።
ማርኮ ሩቢዮ ጽምዶን/ትብብሩን “..ተገንጣይ እና አሸባሪ..” ብሎ ሲገልጽ ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ወይም የአገዛዙ አቢይ መራሹ ብልጽግና ወዳጅና ካድሬ ሆኖ ሳይሆን ሁለት መሰረታዊ የሆኑ ተጨባጭ እውነታዎችን መሰረት አድርጎ ስለሆነ Valid የሆነ Point ያለው ስለሆነ ነው።
እነዚህ ሁለት ተጨባጭምክንያቶች:-
📌 – 1ኛ- የትብብር ለህልውናን ስብስብ አላማና ግብ መሰረት በማድረግ- ተገንጣዮች ያለ ሲሆን
📌 -2ኛ- ህወሃት መስከረም 12 ቀን 2019 ለሊት በከፈተቺው ጦርነት አዲስ አበባ ላይ በተኮሰቻቸው የድሮንና የሚሳይል ጥቃት በመፈጸማ ምክንያት አሸባሪ ብሎ ሊገልጻቸው እንደቻለ ነው መረዳት የተቻለው።
እሁድ መስከረም 10 ቀን 2019 ከትግራይ መቀሌ በዘመነ ካሴ አንባቢነት ህልውናውን የገለጸው የኢትዮጲያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና ስብስብ ዋና አላማ አቢይ መራሹን የብልጽግናውን አገዛዝ ከገረሰሰ በኃላ የሚከተሉትን እርምጃዎችን እንደሚወስድ ያሳወቀ ስብስብ ነው።
📌 1ኛ- የሽግግር መንግስት መመስረትና በዚህ ወቅት ከታች የተጠቀሱትን ተግባራት መፈጸም
📌 2ኛ- የሀገረ ኢትዮጲያን ህልውና እና ግዛታዊ አንድነትን በኢትዮጲያ ሕዝብ ውሳኔና ፍቃድ የማስቀጠልና ያለማስቀጠል ውሳኔን ማሰጠት።
📌 3ኛ- የትግራይ፣ የኦሮሞና የሱማሌ ክልል ህዝብ Unilaterally በተናጥል በሚያደርጉት ሕዝበ ውሳኔ ከኢትዮጲያ ጋር ሆነው መቀጠል መፈለግ አለመፈለጋቸውን እንዲወስኑ ማድረግ
📌 4ኛ- የወልቃት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ራያና አላማጣን ዘብ ትጥቅ አስፈትቶ በመበተን አመራሩን አስሮ ለፍርድ ማቅረብ….እና መሰል የሆኑትን ተግባራትን ለመፈጸም ያቀዱ ሲሆን ይህ እቅድ ተግባራዊ ሆነ ማለት ትግራይ፣ ኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጲያ የተገነጠሉ አዳዲስ ሀገራትን መፍጠር ተቻለ ማለት ነው። ከዚህ የጽምዶ ፕሮግራም አንጻር የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስቴር ማርኮ ሩቢዮ ጽምዶ/ትብብሩ ተገንጣይና አሸባሪ ነው ብሎ ትብብሩን ሊገልጽ የቻለው።
📌- ይህ የማርኮ ሩቢዮ አገላለጽ በአማራ ፋኖ እና ብሎም በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ላይ የሚያደርሰው ጉዳትና አደጋ ምን ይመስላል??
አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያላትን ፖሊሲ መሰረት ያደረገ ውሳኔ ነው የምትወስነው። የአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ፖሊሲ
👉 Business
👉 Security
👉 Terrorism …… መሆኑን በስቴት ዲፓርትመንቱ ድረ ገጽ ላይ በይፋ ተቀምጦ የሚገኝ ሲሆን የአፍሪካ ቀንድ ለጽንፈኝነት እና ለሽብርተኝነት ተጋላጭ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጲያ እንደ የቀጠናው Anchor Stateነታ የኢትዮጲያ Disintegration የቀጠናውን ሰላም ጸጥታና ደህንነትን የሚያናጋ፣ በዚህም ምክንያት ቀጣናው ልክ እንደሱማሊያ የአሸባሪዎች መፈልፈያና መነሃሪያ ምቹ ስፍራ መሆን እንደቻለቺው ሁሉ የሀገረ ኢትዮጲያ ህልውና ፈርሶ ሶስትና አራት አዳዲስ መንግስታት መወለድ የአፍሪካን ቀንድ ሰላምና ጸጥታን በማደፍረስ:-
👉 1ኛ- አውሮፓን ሊያጠለቀልቅ የሚችል የስደተኛ ጎርፍ የሚፈጠር መሆኑን
👉 2ኛ- ቀጠናው የሽብርተኞችና ጽንፈኞች መፈንጫ ምቹ መድረክ በመሆን ከአፍሪካ ቀንድ አልፎ ለአውሮፓ የሚተርፍ ቀውስ የሚፈጠርበት ሁኔታ የሚፈጥር ስለሆነ አሜሪካ የኢትዮጲያን Disintegration በጽኑ የምትቃወም ሀገር ለመሆን እንደቻለች ነው ከስቴት ዲፓርትመንቱ ፖሊሲ መረዳት የቻልነው።
ከዚህ የጽምዶ/ትብብሩ አላማና እቅድ መሰረት ትብብሩ ህልውናውን ባበሰረ ማግስት ከአሜሪካ ጎን ጃፓን፣ ራሺያ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ተመድን ጨምሮ 17 ያህል ሀገራት የትብብሩን ህልውና አውግዘው መግለጫ ሊያወጡ የቻሉት።
በዚህ መሰረት የአማራ ፋኖ ምንም እንካን እንደ ህወሃት፣ ኦነግ እና ኦብነግ የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳ ኃይል ባይሆንም – ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ እንደሚባለው ከተገንጣዮች ጋር የተዳበለ አስገንጣይና አሸባሪ ተብሎ የመፈረጅ አደጋ የተደቀነበት ሲሆን ይህንን የማርኮ ሩቢዮን ገለጻ መስረት አድርጎ አገዛዙ ይህንን ህወሃት መራሹን ስብስብ “ትብብር ለህልውና” ን በአሸባሪነት ሲፈርጅ የአሜሪካ መንፍስት፣ ተመድ፣ የአፍሪካ ሕብረትና ብሎም የአውሮፓ ህብረት ያንን ፍረጃ በመቀበል በራሳቸው ህግ ውስጥ በማካታተ ስብስቡን አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ ስብስቡ የተነሳበትን አላማ እንዳያሳካ እርምጃ የመውሰድ ሁኔታ በቅርብ ርቀት ውስጥ ልናይ የምንችለው ሁኔታ ነው የተፈጠረው።
የአማራ ፋኖ ይህ ጽምዶ/ትብብር የተባለው ስብስብ Once አሸባሪ ተብሎ ተፈረጃ ማለት :-
👉 1ኛ- የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል እንዲከስም ያደርጋል
👉 2ኛ- ከአማራ ፋኖ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ግንኙነት አላቸው የሚባሉ አማራዊያን ፖለቲከኞች፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራን እና ዲያስፖራው የአገዛዙ የበቀል ዱላ ሰለባ ይሆናሉ
👉 3ኛ- የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ ሳይቀለበስ ተባብሶ ይቀጥላል
👉 4ኛ- የአማራ ሕዝብ የፖለቲካ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ይቀበራል።
ይህ እጅግ ከብዙ እጅግ ጥቂቱ ከሚደርስብን ጉዳት ውስጥ የተጠቀሰ ኪሳራ ሲሆን የሚያስከትለውን የስነ ልቦና፣ የሞራል ስብራትን ፈጽሞ አልጠቀስኩም።
📌- የአማራ ፋኖ ከዚህ አደጋ እራሱን ለማዳን ምን ማድረግ አለበት ??
የመፍትሄ መንገድ
ያላቻ ጋብቻ መርገምት ያህል ታላቅ ስቃይ፣ ችግርና መከራ ምንጭ የመሆኑን ያህል የአማራ ፋኖ የተቀደሰ የመታገያ አላማ እያለው ካልተቀደሰ የመገንጠል አላማ ካላቸው ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጲያ ከሆኑት ህወሃት፣ ኦነግና የጉምዝ ታጣቂ ጋር ሄዶ በመሸጎጡ የገንጣይና አሸባሪነት ተብሎ ለመፈረጅ በመብቃቱ ከዚህ የህልውና አደጋ ለመትረፍ የሚከተሉት ተግባራት በአስቸካይ መፈጸም አለባቸው።
👉 1ኛ- አፋብን እንደ ድርጅት በአስቸካይ ከጽምዶ/ትብብር ከሚባለው ስብስብ ሙሉ በሙሉ መውጣቱን ማሳወቅ አለበት።
ይህንንም ውሳኔውንና እርምጃውን ለአሜሪካ መንግስት፣ ለአፍሪካ ሕብረት፣ ለአውሮፓ ሕብረት፣ ለተመድና መሰል ሀገራት ማሳወቅ
👉 3ኛ- አፋብን ውስጣዊ ሪፎርም ማድረግ
👉 4ኛ- አፋብንን ያለድርጅታዊ ውሳኔ ድርጅቱን ይዘው ለህወሃት እና ለኦነግ የሸጡትን ግለኛ አመራሮችን ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነት ማንሳት
👉 5ኛ- የአማራ ፋኖ ከተገንጣይ፣ ከጸረ አማራ እና ከጸረ ኢትዮጲያ ኃይል ከሆኑት እንደነ ህወሃት፣ ኦነግ፣ የጉምዝ ታጣቂ፣ ግብጽ፣ ሱዳን እና መሰል ጸረ ኢትዮጲያና ጸረ አማራ ኃይሎች ጋር አንዳችም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ለሰፊው የአማራ ሕዝብ እና ለአለም ማሳወቅ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ሊድን ይችላል።
ይህን አይነቱ ታላቅ አደጋን ቀድመው ያዪ የህልውና ትግሉን ችቦ ለካሽ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ የአማራን ሕዝብ ትግል መነሻና መድረሻውን የአማራን ሕዝብ ርስት፣ ማንነትና የቀይ መስመሮችን አስቀምጦ መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጲያ ግዛታዊ አንድነት ብሎ የተነሳን ታግሎ አታጋይን መሪ ከህልውና ትግሉ ውስጥ በህወሃት ሴራና ሴራውን በሚያስፈጽሙ ግለሰቦች ገፍቶ የማራቅ ሁኔታ ያስከፈለንን ታላቅ ዋጋ እውቅና መስጠት ይገባል።
📌- መደምደሚያ :-
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ዛሬ አራተኛ አመቱን በያዘበት ወቅት ለህዝባችን የነጻነት ጎህ ከማነጸበረቅ ይልቅ በአሸባሪነት ፍረጃ የባርነት ቀንበርን ለመጫን የሚያስችል ታላቅ የጥፋት መንገድ ላይ ቆሞ መገኘት እጅግ የሚያሳምም ሁኔታ ነው። የችግሩ ዋና አስካል የ Leadership Crisis, የህልውናውን ሕዝባዊ ትግል ለጥቂት ግለሰቦች እና ቡድኖች ቅንጥብጣቢ ጥቅም ለጠላት አሳልፎ መሸጠን የመሰለ ታላቅ ክህደት የተፈጸመው በአፋብን ጥቂት ከፍተኛ አመራሮች የመሆኑ ጉዳይ አብዛኛውን የአማራ ፋኖ ከ90% በላይ የሆነውን ንጽህ ታጋይ እጅግ የሚያቃጥል እና እጅግም ታላቅ ዋጋ የሚያስከፍል ሁኔታን ነው ይህ የአፋብን አመራር ነኝ የሚለው ክፍል የፈጸመው ጥፋት።
ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ላይ ባለኝ መረጃ መስረት 18ኛ የህወሃት የመሳሪያ ዴፖ በአገዛዙ ሰራዊት እጅ ውስጥ ገብታል። ከዚህ 18 የመሳሪያ ዴፖ ውስጥ ቦያንስ ሁለት ያህሉ ለአማራ ለኣማራ ፋኖ ቢሰጥ ወይም በአማራ ፋኖ እጅ ቢገባ ኖሮ ቢያንስ የአማራን ክልል ከብልጽግና ማጽዳትና ነጻ ማውጣት በተቻለ ነበር። ግን ህወሃት ይህንን ከማድረግ ይልቅ መሳሪያዋን ታቅፋ ለአገዛዙ ሲሳይ እንዲሆን ነው ያደረገቺው። ምክንያቱም የአማራን ፋኖ መጠናከር እንደ ስጋት ስለምትቆጥረው አገዛዙን ለማሸነፍ የሚያበቃ የጦር መሳሪያ ለፋኖ ከመስጠት ይልቅ በአማራ ልጅ መስዋእትነት የህወሃት ጥገኛና ጉዳይ አስፈጻሚ በሆነ ፋኖ ዋጋ ከፋይነት ወደ አራት ኪሎ ለመጋዝ ባደረገቺው ውሳኔ በለኮሰቺው ጦርነት ተሸንፋ 18 ያህሉን የመሳሪያ ዴፖዎቻን በአገዛዙ እጅ እንዲወድቅ አድርጋለች።
ይህንን የጠቀስኩበት ምክንያት የአማራን ትግል ለህወሃት የሸጡት የአፋብን አመራሮች እንደነ ዘመነ ካሴ፣ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ሄኖክ አዲሴ፣ ምሬ ወዳጆ፣ አበበ ፈንታው፣ ሳሙኤል ባለድልና መሰሎች ፋኖ ከህወሃት ጋር የተባበረው ተተካሽና መሳሪያ ለማግኘት ነው የሚል ምክንያት ሲሰጡ ስለሰማሁ ያቀረቡት ምክንያት እንዳልሰራ እና እንደማይሰራም ለማሳየት ሲሆን ዛሬ ብትንትና ወጥቶ እና በአሜሪካ መንግስት ተገንጣይና አሸባሪ ተብላ በመቃብር አፋፍ ላይ ባለችበት ወቅት እንካን ጉዳዩ ገና አላለቀም በሚል ስንኩል እሳቤ የአማራን ፋኖ ታላቅ ዋጋ የሚያስከፍል አካሄድን ከጽምዶ/ትብብሩ ጋር ተለጥፎ መቀጠልን እንደ ትክክለኛ አካሄድ የሚገልጹ ደናቂርቶች አሉ።
ደናቂርቶቹ በህወሃት የተገዙ ህወሃትን አገልጋዮች የሆኑ ስለሆነ የአማራ ፋኖ እነዚህን መሸጦዎችን The So Called of የአፋብን አመራር ተብዬን በአስቸካይ መገላገል ይኖርበታል። የአማራ ፋኖ ይህንን እርምጃ ለራሱ ህልውና ብሎ ዛሬውኑ መውሰድ ይኖርበታል። አበቃሁ።

















