ለህወሃት ያለው ጥልቅ ፍቅርና ፍጹማዊ ታማኝነት ትናንት በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ላይ ክህደት እንደፈጸመ ሁሉ ዛሬም ስለህወሃት ብሎ በአማራ ሕዝብ ላይ የክህደት ሰይፉን የመዘዘው ሰው!
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
የጽምዶ ፓኬጅ ሲገለጥ ካሳየን በርካታ ክስተቶች ውስጥ እንደ አንዱ ሊጠቀስ የሚገባው የ 56 አመቱ ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው እና የጀዋር መሀመድ ጎራ ለይተው ሁለቱም ለተሰለፉለት ቡድን ልደቱ ለጽምዶ፣ ጀዋር ለብልጽግና እያደረጉት ያለው የሀሳብ ፍልሚያ ነው። የጀዋርን ጉዳይ እዚህ ላይ ቀጭቼ ወደ ልደቱ አያሌው ሳመራ ሰሞኑን ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ በሰራቸው ተከታታይ ቪዲዮዎች ላይ የገለጻቸው ኩነቶች ለዚህ ጽሁፌ ምክንያት እንደሆነኝ ለመግለጽ እወዳለሁ።
ከልደቱ አያሌው ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋን ተተርሶ ባስተላለፋቸው ቪዲዮዎች ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ሲገልጽ ከሰማሃቸው ውስጥ ለ20 አመታት እኔን ስትተች፣ ስታወግዝና ከህዝብ እንድነጠል ስትሰራ …. የሚሉ በስቃይ የተሞሉ ንግግሮቹ በእርግጥ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ነውን ነጻ ፕረሱን አስዘምቶበት ከህዝብ እንዲነጠል ያደረገው ? ወይንስ ልደቱ አያሌው እራሱ በመረጠው የፖለቲካ መስመር ነጻ ፕረሱ እንደ አንድ የሕዝብና የሀገር ድምጽ፣ ጠበቃና ወገንተኝነቱ ድብቅ ምስጢሮቹን እያጋለጠና እያሰጣ ለፖለቲካ ክስረት የዳረገው ?? ለክስረት ፖለቲካ የዳረገው ስል የራሱን የልደቱ አያሌውን “..እኔ የከሰርኩ ፖለቲከኛ ነኝ ..” ገለጻን መሰረት በማድረግ እውነታውም ከዚያች የ97 ምርጫ በኃላ የልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወት ያለበት ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳይ ነው።
እናም ለመሆኑ ልደቱ አያሌው እና የኢትዮጲያ ነጻ ፕሬስ ምን እና ምን ነበሩ ??? በ27ቱ የህወሃት መራሹ የኢሕአዴግ አገዛዝ ዘመን እራሱን ተቃዋሚ ብሎ ከነጻው ፕሬስ ጋር ጥርስ የተጋባ ፖለቲከኛ ቢኖር አንድ ልደቱ አያሌው ነው ብዬ ስገልጽ በፕሬሱና በተቃዋሚው መካከል ያለውን ጥብቅ ወዳጃዊ ግንኙነትን ለመግለጽ ነው።
ልደቱ በ1980ዎቹ ላይ ዛሬ እንደሚያወራው ሳይሆን በማንም የማይታወቅ -ምናልባትም በመዐሕድ ውስጥ ባለው አጭር ተልእኮ መር ቆይታ በሰርክሉ ያሉ ሰዎች ከሚያውቁት በስተቀር ነጻ ፕረሱ ሽፋን ሊሰጠው የሚፈልገው ሰው ፈጽሞ አልነበረም። በዚያን ግዜ ከዛሬው ሁሉ የሚያውቀው ልደቱ ይበልጥ በስሙ የሚጽፍ የአንድ ጋዜጣና መጽሄት ቋሚ አምደኛ፣ እና የጋዜጣው አዘጋጅ ይበልጥ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቂበት ወቅት መሆኑን የዛሬ አንባቢ ማወቅ ያለበት እውነታ ነው። የልደቱ ፖለቲካ የጀመረው በ1993 ሚያዚያ 1 ቀን የአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ተማሪዎች የትምሀት ጥራት ጥያቄን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማን በአንድ እግራ ያስቆመ ህዝባዊ አመጽ መነሳትና ያንን ተከትሎ ልደቱ ታፍሶ ሸዋሮቢት ጸጉሩን ተላጭቶ ከታሰረ በኃላ ነው ብሎ መግለጽ ይቻላል።
ልደቱ አያሌው እና ፕረሱ የተዋወቁት ኢዴፓ ሲመሰረት በ1992 ቢሆንም ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ እና ዶ/ር ኃይሉ አርአያ የድርጅቱ ፕሬዚዳንትና የድርጅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት እስከሆኑ ድረስ ኢዴፓ የነጻ ፕረሱን ሽፋን ፈጽሞ አግኝቶ አያውቅም፣ ካገኘም በትችት መልክ ይሆናል።
ልደቱ አያሌው እና ነጻ ፕረሱ ሁለቱም ከሀገር ተሰደው እስከተለያዩበት ግዜ ድረስ ፖሊስና ሌባ ያህል ሲተያዪ የነበሩ ናቸው።
ታሪኩ እንደዚህ ነው…..
በህወሃት መራሹ የኢሕአዴግ ዘመን የተቃዋሚ ፖርቲዎች፣ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና በነጻው ፕረስ መካል ያለው ግንኙነት እጅግ የሚያስቀና Cordial የሆነ Relationship ያለ ቢሆንም ያ ጥሩ ግንኙነት ግን ከልደቱ አያሌው ጋር ፈጽሞ አልሄደም።
ዘመኑ እንደዛሬ ዲጂታል ፕላትፎርም የማይገደብ አምራጭ የቀረበበት ዘመን ሳይሆን መንግስት ከሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙን ጎን ያነበረው የነጻ ፕረስ ውጤቶች ብቻ ነበሩ። The 4th State የሚባለውን የሚዲያ አገልግሎት ለማግኘት በወቅቱ ለተቃዋሚ ፖርቲዎች እጅግ ፈታኝ ነበር። በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉት Tv Radio,News Paper, Magazine ላይ የተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ ሽፋን ማግኘት የማይቻል ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ የማይታሰብም ጭምር ነው። ስለሆነም እነዚህ ፕሮግራሞቻቸውን፣ መግለጫዎቻቸውን እና መልእክቶቻቸውን ለሕዝብ ለማድረስ እጅግ ለሚፈልጉ ተቃዋሚዎች የነጻው ፕረስ ህትመቶች እጅግ ወሳኝ አማራጭ በመሆናቸው በሁለቱ መካከል እጅግ ጥብቅ ግንኙነትና የአጋርነት መንፈስ ነበረ ብሎ መግለጽ ይቻላል።
የመንግስት ባለስልጣናት በሙሉ ቢሮአቸውን ለነጻ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ ሙሉ በሙሉ ጠርቅመው የዘጉ ሲሆን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ በሮቻቸውን ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠርቅመው በመዝጋት አግደዋቸው ነበር።
በዚህ ሁኔታ ነጻ ፕረስና የኢትዮጲያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ በመሆን እስከመጨረሻው ድረስ ዘልቀዋል። ግን የልደቱ አያሌው እና የነጻ ፕረስ ግንኙነት እጅግ የተለየ ነበር። ለምን እና እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን መልስ እንደሚከተለው ልግለጽ።
ይህ ጸሀፊ በወርሃ ጥቅምት 1992 በአንደኛው ቀን ግዮን ሆቴል ሲያመራ በመዋኛው ገንዳ ክፍል አንድ አምስት የማይሞሉ ( ሶስት ናቸው ልደቱ አያሌው፣ አብዱራህማንና ሙሼ ሰሙ ) ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ መሆናቸውን በማየቱ ተቀላቀላቸው። መግለጫው የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መመስረቱን የሚገልጽ ነበር። በስፍራው አንድም የነጻ ፕረስ ጋዜጠኞች አልነበሩም። ይህ ጸሀፊም የተገኘው ለሌላ ጉዳይ ወደ ግዮን ሆቴል እያመራ ባለበት ወቅት ጋዜጣዊ መግለጫ በመዋኛው ስፍራ እየተሰጠ ነው የሚል Notice የሆቴሉ ቦርድ ላይ አንብቦ ነው። አንድም ነጻ ፕረስ ጋዜጠኛ ባይኖርም በጎሳዬ ተስፋዬ ከሚመራው አዲስ አድማስ፣ በአማራ አረጋዊ ከሚመራው ሪፖርተር፣ ፋና ራዲዮ፣ እና የኢትዮጲያ ራዲዮ የተላኩ ጋዜጠኞች ግን ነበሩ። እናም ልደቱ አያሌው፣ሙሴ ሰሙ ፣ አብዱራህማን እና ሌሎች ስማቸውን የማላውቃቸው ሁለት ሰዎች ሆነው ያወጡትን የኢዴፓን መመስረት ጋዜጣዊ መግለጫን አንድም የነጻው ፕረስ ሽፋን ሳይሰጠው አልፈው። በአንጻሩም ከኢሕአዴግ ጋር ቅርበት ያላቸው የኢሕአዴግ “ነጻ ” ፕረስ ህትመቶች ሽፋን ሰጥተውታል።
ለመሆኑ በ1992 ጥቅምት ላይ የልደቱ አያሌውን ማንነት የሚያውቅ የአዲስ አበባ ልጅ ነበር ?? እጅግ ጥቂት በእሱ ሰርክል ውስጥ ያሉት ብቻ የሚታወቅ እንጂ ዛሬ ላይ ልደቱ እንደሚያወራው አይደለም በ 1980ዎቹ ውስጥ ይቅርና በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንካን ልደቱን ህዝብ አያቀውም ነበር። ሆኖም ከነጻ ፕረስ ውስጥ ልደቱን የሚያውቅ ተገኘ። ልደቱን ማወቅ ብቻ ሳይሆን የመሰረተውንም ድርጅት ኢዴፓን ምስጢር የሚያውቅ ተገኘ። የኢትኦጵ መጽሄትና ጋዜጣ አዘጋጅና አሳታሚ ሲሳይ አጌና ነው ያወቀው። ኢዴፓ በክንፈ ገብረመድህን የተፈጠረው ኢሕአዴግ በቀጣይ ግንቦት 1992 ለሚካሄደው 3ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚሳተፍ ታማኝ ተቃዋሚ ፓርቲ መሆኑን መረጃ አገኘ። ሲሳይ አጌና በወቅቱ ከኢሕአፓዎች በጣም ጠንካራ መረጃዎች የሚደርሱት ሰው ነበር። የ1990ዎቹ ኢሕአፓ ራዲዮ ያላት፣ በምስራቅ አፍሪካ (ሱዳን፣ ኬኒያ) ጦር ያላት፣ የህወሃት፣ የብአዴን ውስጠ ምስጢር መረጃ መመንተፍ የቻሉ ኔትወርክ ያላት ነበረች። እናም በልደቱ አያሌው ዋና ባለቤትነት ክንፈ ገብረመድህን ኢዴፓ የሚባል ታማኝ ተቃዋሚ ፓርቲ መፍጠራ መረጃው ይደርሰውና ድርጅቱ በተመሰረተ ማግስት የህወሃት ድርጅት መሆኑን ገልጾ ሲሳይ ሽፋን ሰጠ። ከዚያች እለት ጀምሮ የልደቱ አያሌው እና የነጻው ፕረስ ግንኙነት የፖሊስና የሌባ ግንኙነት ሆኖ ዘለቀ። 90%ቱ ነጻው ፕረስ ስለልደቱ ፓርቲ ትንፍሽ አልል አለ። እጅግ ጥቂቶቹ ደግሞ ስለኢዴፓ ከጻፉ በህወሃት የተፈጠረ ታማኝ ተቃዋሚ ድርጅት መሆኑን የሚገልጽ ዘገባ ሆነ።
በእርግጥ በወቅቱ የልደቱ አያሌው ኢዴፓ ፓርቲ ብቻ አልነበረም በህወሃት የተፈጠረው። ይህ ጸሀፊ ከሀገር ከተሰደደ በኃላ ባገኘው መረጃ መሰረት በመረራ ጉዲና የተመሰረተው የ Oromo National Congress በሃላ ላይ ኦፌኮ የሆነው በተመደበለት 300.000ብር ማቋቋም እንደቻለ እና በበየነ ጴጥሮስ የሚመራ ደህዴን በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝ በ1996 ላይ ተመልምለው ለለጋሾች ኢሕአዴግ Multi- Parry System ይመራል ለማስባል የተፈጠሩ ታማኝ ተቃዋሚዎች መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችላል።
ይህ በ 1996/97( 2004) በአሜሪካን ከተመሰረተው እና 14 ድርጅቶችን ያቀፈው የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረት አሜሪካ ላይ ተመስርቶ በየን ጴጥሮስ ፣መራራ ጉዲና በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት ሲመሩት በነበረው ስብስብ ውስጥ የልደቱ አያሌው የክንፈ ገብረመድህን ተወካይነትን ያረጋገጠ በርካታ መረጃዎች መሰብሰብ ተችላል።
ይህ በልደቱና በነጻው ፕረስ መካከል የነበረው የፖሊስና የሌባ ግንኙነት ሳይለወጥ ልደቱ አያሌው ዶ/ር አድማሱ ገበየሁን እና ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ወደ ፊት በማምጣት የድርጅቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ ኢዴፓ በክንፈ ገብረመድህን የተመሰረተ የህወሃት ታማኝ ድርጅት ነው የሚለውን ስም ለመግፈፍ የቱንም ያህል ቢጥርም እስከ 1997ቱ ምርጫ ድረስ ግን ፈጽሞ የተሳካለት አልሆነም ነበር።
እንዲያም ሆኖ የ97ቱ ምርጫ ደረሰና በምረጡን ቅስቀሳ ልደቱ በሕዝብ አይን ውስጥ ሊገባ ቻለ። እጅግ በጣም በከፍታ እውቅና ማማ ላይ በወጣበት ቅጽፈት እና ከመቼውም ግዜ በላይ በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ዘንድ በአንጸባራቂ ኮከብነት እየታየ ባለበት ማማው ላይ ባለበት ሁኔታ የልደቱ አያሌውን የፖለቲካ ህይወት እስከ ህይወት ፍጻሜው ድረስ ይዞት የሚዘልቅን እጅግ ታላቅ እራስን የማጋለጥ ስራን ሰራ። በአንፃራዊነት በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት ከነጻው ፕረስ ጋር ፈጥሮት የነበረውን ጥብቅ ቁርኝትና ግንኙነት በአንድ ምሽት በዜሮ አባዝቶ ከወዳጅነት ወደ ጠላትነት እንዲቀየር አደረገው።
በዚያ የክብር ከፍታ ማማ ላይ ሆኖ ድፍን የኢትዮጲያ ሕዝብ እውነተኛ የህዝብ ልጅ እያለ በሚጠራበት ሰዓት ልደቱ ከኢትዮጲያ ሕዝብ ይልቅ እነሆ በ56 አመት እድሜው እንኳን እየደገፋት ያለቺውን ስልጣን አልባዋን ህወሃት አብልጦ መረጠና በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ አይንህ ላፈር ተባለ።
የኢትዮጲያ ነጻ ፕረስ ውግንናው ለሕዝብ እና ለሕዝብ ነው። በነጻ ፕረስ ታሪክ ውስጥ ትንሽ በኢሕአዴግ እና በነጻ ፕረስ መካከል መቻቻል ተፈጥሮ የነጻ ፕረስ ጋዜጠኞች ከመታሰር እፎይ ያሉበት ታሪካዊ ወቅት ቢኖር ከ1990-1992 የነበረው የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት ብቻ ነበር። ሀገርና ሕዝብ ወዳዱ ነጻ ፕረስ አቅጣጫውን ሙሉ በሙሉ በሻእቢያ ላይ በማድረግ በፍጹም ኢትዮጲያዊ አርበኝነት በብእሩ ሻእቢያን በሚፋለምበት ወቅት ህወሃት ማሰዳዱን ተወች፣ ይባስ ብላም ለአዳዲስ የህትመት ድርጅቶች ፍቃድ ለማግኘት የሚያስፈልገውን የዞያን ግዜ 10.000 ብር ካፒታል ያለህግ በማንሳት ካፒታሉ ለሌላቸው እውነተኛ ነጻ ፕረሶች ፍቃድ እስከመስጠት የደረሰችበት ወቅት ነበር።ሆኖም ያ የጫጉል ሽርሽር ብዙም አልዘለቀም። ጦርነቱ ሲቆምና በህወሃት ውስጥ መከፋፈል ሲፈጠር ህወሃት ከነጻ ፕረሱ ጋር ስታደርግ የነበረውን ጦርነት መልሳ ማሳለጥ ጀመረች።
ይህንን የምገልጽበት ምክንያት የነጻው ፕረስ ታማኝነትና ፍጹማዊ ወገንተኝነት ለሀገር፣ ለህዝብ፣ ለእውነትና ለፍትህ ብቻ እና ብቻ የመሆኑን ሁኔታ በማሳየት በአንጻሩም ማን ሆነ በተቃዋሚ ስም የህወሃት አገልጋይና የኢሕአዴግ መጠቀሚያ የሆነ ሲገኝ ነጻ ፕረሱ ከላይ እስከታች የሚያጋልጠውና የሚታገለው መሆኑን ለመግለጽ ነው።
ከዚህ አንጻር በልደቱና በነጻ ፕረስ መካከል ኢዴፓ ሲፈጠር ጀምሮ ቀዝቀዝ ባለ ሁኔታ ተጀምሮ የነበረው የፖሊስና የሌባ ግንኙነት ከ97ቱ የልደቱ አያሌው ይፋዊ ክህደት በኃላ እከሌ ከእከሌ ሳይባል መላው የነጻ ፕረስ እንደ የህዝብን ጥቅም እስጠባቂነቱ በልደቱ ላይ ሙሉ ጦርነት ለመክፈት የቻለ ቢሆንም ጦርነቱን የከፈተው ግን እሱ እራሱ ልደቱ አያሌው መሆኑን መረሳት የሌለበት ነው።
ከዚያች ከ97ቱ ምርጫ በኃላ የልደቱ የፖለቲካ ህይወሃት ላይመለስ የሞተ የፖለቲካ ህይወት ነው መኖር የጀመረው። እነሆ ከ22 አመታት በኃላም ቢሆን ልደቱ አያሌው በ56 አመቱ በስደት ሀገር ሆኖ በ97 የፈጸመውን ይፋዊ ክህደት ዳግም በመድገም ከህወሃት ውጪ ወደ ውጪ በሚል አቋም ህወሃትን ያልተቀበሉ ሁሉ ብልጽግና ናቸው ፣ ለብልጽግና የሚያገለግሉ ናቸው እያለ በመፈረጅ ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ለህወሃት ያለው እጅግ ስር የሰደደ ፍቅር እና ፍጹማዊ የእድሜ ልክ ታማኝነት Loyalty በኢትዮጲያ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ያለው ባለ ሁለት ፈረስ Tow Horse አንዱ ብልጽግና ሌላኛው ጽምዶ ብቻ ናቸው በማለት እራሱን በተቃረነ ሁኔታ ከብልጽግና ያልሆነ ጽምዶ ነው፣ ከጽምዶ ያልሆነ ብልጽግና ነው በማለት የሶስተኛው መንገድ ባለቤት ነኝ የሚለው ልደቱ እነሆ Just የጽምዶ ፕሮጄክት ብቅ ባለ ማግስት ፌስቡክ፣ ቲክቶክና ዩቲውብ ለዚህ አላማ በመክፈት ህወሃትን የመታደግ ተጋድሎ በሀገር ስም ሊሸጥ ሲታገል የሚውልና የሚያድር ሰው የሆነ ነው።
📌- የአማራን ሕዝብ ጄኖሳይድ እና የህወሃትን የአማራ ጠላትነትን መክዳት ለአማራ ሕዝብ ካለ ጥላቻ የሚመነጭ ነው!!!!?
በዚህም ምክንያት ህወሃትንና ኦነግን ያልተቀበሉ እውነተኛ የአማራን ልጆች – እንደ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ አይነቱን “…ህወሃትንና ኦነግን ያልተቀበለ ለትግራይ ሕዝብና ለኦሮሞ ሕዝብ ባለው ጥላቻ ነው ..” እያለ ለመፈረጅ ሲጋጋጥ ለማየት የቻልነው። በልደቱ አያሌው አገላለጽ እና እምነት ህወሃትን ያልተቀበለ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥላቻ ያለው ነው፣ ኦነግን ያልተቀበለ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጥላቻ ስላለው ነው የሚል ትርጉም በመስጠት ሰዎች ከሕዝብ ጋር ሊያጋጨን ነው በሚል ማስገደጃ ጽምዶን ይቀበላሉ በሚል ጅል ምኞት በፍረጃ ላይ የተጠመደ ሰው ሆናል።
ለመሆኑ ልደቱ አያሌው የአቢይ መራሹን ብልጽግናን መንግስት ሲቃወም ለኦሮሞ ሕዝብ ጥላቻ ኖሮት ነውን??
ብልጽግና ማለት 40%ቱ በኦህዴድ የተያዘና ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግስት የኦሮሞ መንግስት ነው እያሉ እነ አቢይ አህመድ ልክ እንደ ህወሃቶች እየገለጹ ነው። እናም ልደቱ አያሌው ይህንን ኦህዴድ መራሹን ብልጽግናን ሲቃወም የኦሮሞ ሕዝብ ጥላቻ ስላለበት ነው??
ሌላኛው ልደቱ አያሌው ከህወሃትና ከኦነግ ጋር መስራት አይቻልም የሚሉትን አማራዊያንን ሲፈርጅና ሲያወግዝ ለአማራ ህዝብ ጥላቻ ስላለው ነውን ??
አማራው ለኦሮሞም ሆነ ለትግራይ ሕዝብ ጥላቻ የለውም። አማራው እስካሁና ሰአት ድረስ እንደ ሕዝብ ጠላቴ ነው ብሎ የፈረጀው አንድም ብሄርና ህዝብ የለም። ሆኖም አማራ የምንታገለው ጠላታችን ነው ብለው በጠላትነት የፈረጁትን ህወሃትና ኦነግ ጠላት ስላደረጉት እሱም በጠላትነት ያያቸዋል፣ይታገላቸዋል።
የዛሬዋ ህወሃት በ1967 ደደቢት በረሃ ላይ አማራ የምታገለው ጠላቴ ነው ብላ በማንፌስቶዋ ላይ የጻፈች ህወሃት ናት። ከአንዳንድ አመራሮች በሞት፣ በመባረር መለወጥ በስተቀር የዛሬዋ ህወሃት ፕሮግራማን፣ አላማዋን ፈጽሞ ያልለወጠች እና ዛሬ ጽምዶን ፈጥሬያለሁ በምትልበት ዘመን 40% የትግራይ ግዛት በወረራ የተያዘብኝ ነው የምትል ጸረ አማራ ድርጅት ነው። አነ አማኑኤል አሰፋ 40%የትግራይ ግዛት በወራሪዎች ተይዞብናል የሚሉት ወልቃይት ፣ጠገዴ፣ሁመራና ጠለምትን ሲሆን ስድስት ወረዳዎችን የያዘው የራያ አላማጣን ቀጠና ተቆጣጥሬያለሁ ብለዋል። ለልደቱ አያሌው ይህ ምንም ስሜት የማይሰጥ ትክክለኛና የህወሃት ፍትሃዊ ጥያቄ ነው ባይ ነው። ለእኛ አማራዊያን ግን ይህ የህወሃትን ጸረ አማራነትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።
በአርግጥ ልደቱ አያሌው ህወሃት አማራን በጠላትነት ፈርጃለች የሚለውን እውነት ግጥም አድርጎ የካደ ሰው ነው። ህወሃቶቹ ያልካዱትን አጅሬው ግጥም አደጎ በመካድ ፍረጃው ውሸት ነው ሲል ያለ አንዳች ሀፍረት ሲናገር ተሰምታል።
ለህወሃት ያለው አጥንት ድረስ የዘለቀ ፍቅር ትናንት በ1997 በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ላይ ክህደት እንዲፈጽም እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ከ22 አመታት በኃላ በአማራ ላይ የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ጸረ አማራ ተግባር በመካድ መላውን የአማራን ህዝብ እና በተለይም የአማራ ፋኖ ህወሃትን እንዲታደግ ሌት ተቀን የሚጋጋጥ አይኑን በጨው ያጠበ አይነ ደረቅ ሰው ሆናል።
ዛሬም ቢሆን ከ22 አመታት በኃላ በ1997 አንዳችም ክህደት እንዳልፈጸመ ለማሳመን ሲጥር እና ሲተርክ ይታያል፣ይደመጣልም። ግን ፈረንጆች እንደሚሉት The damage is already done ከዚያች ይፋዊ ክህደት ቀን በኃላ የልደቱ ህይወት ሙሉ በሙሉ ያንን ክህደቱን Justify ለማድረግ ለድፍን 22 አመታት በመጽሀፍ፣በመጣጥፍ የሚጥር ሰው ቢሆንም መላው የኢትዮጲያ ሕዝብ የሚያውቀው ግን በተቃዋሚ ስም ሰርጎ የገባ የህወሃት አገልጋይነቱ ነው። ይህንንም ስሙን ዛሬ መልሶ እያደሰና እያጠናከረው ይገኛል። ያውም እየሞተች ላለች ህወሃት ፍጹማዊ ታማኝነቱን በመግለጽ ህወሃትን በእኛ አማራዊያን ዋጋ ከፋይነት ለመታደግ እየተጋጋጠ ይገኛል።
ትናንት በ1997ቱ ምርጫ የቅንጅቶችን ማህተም ይዞ ውህደቱን በማክሸፍና ከቅንጅቱ እራሱን ነጥሎ ፓርላማ የገባበትን ሁኔታ Justify ለማድረግ ዛሬ ላይ ሆኖ የሚከራከራው ልደቱ አያሌው በተመሳሳይ ሁኔታ ዛሬ በ 56 አመቱ በስደት ሆኖ ኦነግ፣ህወሃት፣ ጉምዝ ታጣቂ፣ ONLF,፣ ሱዳን፣ ግብጽና ሻእቢያ ያሉበት ጽምዶ ለአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ መልስ ያለው ስብስብ ነው፣ ለሀገረ ኢትዮጲያ ሀገራዊ ህልውና እጅግ አስፈላጊና የመፍትሄ ቁልፍ ይዞ የመጣ ኃይል ስለሆነ የአማራ ፋኖ ሊቀላቀልበት ይገባል፣ ይህንንም የማይቀበል የትግራይ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ጥላቻ ያለበትና የብልጽግና አገልጋይ የሆነ ነው እያለ ውሃ የማይቃጥር ክርክር ሲያስተጋባ እየሰማን ነው።
ለዚህ ጸሀፊ ልደቱ አያሌው እና ዘመነ ካሴ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ አካሎች ሆነው ይታዪታል። ልደቱ አያሌው በ1990ዎቹ በመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና በተለይም የወጣቱ ክፍል ሞዴል ተስፋ በመሆን የት ይደርሳል የተባለ ሰው ሆኖ ሳለ በ97ቱ ምርጫ ደብቆት የነበረውን ጭንብል ገልጦ ታማኝነቱን ለህወሃት ካሳየበት እለት ጀምሮ የፖለቲካ እድሉን እንዳያንሰራራ በመግደል የእድሜ ልክ Justifier ሆኖ የከሰረ ፖለቲከኛ እንደሆነ ሁሉ የዘመናችን ዘመነ ካሴም በአማራ ሕዝብና በተለይም በወጣቱ የአማራ ክፍል የታጋይ፣ የአርበኛና የነጻ አውጪ ሞዴል ሆኖ ሳለ በድንገት ጭንብሉን ገላልጦ መጀመሪያ ከስብሃት ነጋ ጎን ተቀምጦ ሲሰበሰብና ለጥቆም ከትግራይ መቀሌ ሆኖ ጽምዶን ሲያውጅ ከመላው የአማራ ሕዝብ እና በሞዴልነት ከሚያየው ወጣት አማራ ልብ ተፍቆ በከሀዲ ባንዳነት በመተካት የተቀረውን የህይወት ዘመኑን ልክ እንደ ለደቱ አያሌው ከህወሃት ጋር መሰራት ትክክል እንደሆነ ለማሳመን የሚጥር የፖለቲካ ህይወቱን የገደለ ሰው በመሆን ሁለቱ ግለሰቦች እጅግ ይመሳሰሉብኛል።
እጅግ ወሳኝ በሆነው በ97ቱ ምርጫ ወቅት ልደቱ አያሌው እጅግ ያገነነውን የኢትዮጲያን ሕዝብ ክዶ ህወሃትን እንደመረጠ ሁሉ ዘመነ ካሴም በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ እጅግ ወሳኝ በሆነ ሰዓትና ስፍራ አማራውንና ፋኖን ክዶ ታማኝነቱን ለህወሃት በመስጠትና ህወሃትን በመምረጥ ሁለቱም እኩል የቆሙለትን ሕዝብ ስለህወሃት ፍቅር ብለው የካዱ በመሆን ፍጹም ተመሳሳይነት ታይቶባቸዋል።አበቃሁ።


















