>

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔሬራል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር ዋሉ !!!

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔሬራል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር ዋሉ !!!
ያሬድ አየለ
የቀድሞው ምክትል የደህንነት ሀላፊ ከወራቶች በፊት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔሬራል ሆነው የተሾሙት አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን ከተደበቁበት መያዛቸውን ጠቅላይ አቃቤህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በፌዴራል ፖሊስ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው ይፈለጉ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ለጊዜው በግብረ አበሮቻቸው ለመሠወር ሞክረው ነበር፡፡ አቶ ያሬድ እንዲሸሸጉ እርዳታ አድርገዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ማለትም ንስሀ አባታቸው እና ሹፌራቸው በትላንት እለት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡
አቶ ያሬድ ዘሪሁን በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በሚያዚያ 19 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ሆነው በተሾሙ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በጤና እክል በሚል ምክኒያት  ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ አቶ ያሬድ ዘሪሁን ወደ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነርነት ተሹመው ከመምጣታቸው በፊት በደህንነት ተቋም ውስጥ በምክትል ዳሬክተርነት ያገለገሉ እና የጌታቸው አሰፋ ቀኝ እጅ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
Filed in: Amharic