>

ህወሀት ከነጨለማ ታሪኩ ከኢትዮጵያ ምድር  ተነቅሎ ደደቢት ዋሻ ስር መቀበር አለበት!!! (መሳይ መኮንን)

ህወሀት ከነጨለማ ታሪኩ ከኢትዮጵያ ምድር  ተነቅሎ ደደቢት ዋሻ ስር መቀበር አለበት!!!
መሳይ መኮንን
 
* የኢህአዴግ ምክር ቤት የትላንት መግለጫ የህወሀትን መንግስት ሽብርተኛ ሲለው በገደምዳሜ ሰይሞታል። ሲያልቅ አያምርም ነው። ህወሀት ጠፍጥፎ የሰራው ኢህ አዴግም ፈጣሪው ላይ እርግማን ሲያወርድበት ከመስማት በላይ ለህወሀት ሞት የለም!
ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል በትግርኛ የተናገሩትን ትርጉሙን አየሁት። እሳቸውን በተመለከተ ከወራት በፊት አንድ ነገር ማለቴን አስታውሳለሁ። ደብረጺዮን ወደአዲስ አበባ ሲመጡ ይደመራሉ። ወደ መቀሌ ሲመለሱ ይቀነሳሉ። መቀሌ የመሸጉት አዛውንቶቹ የህወሀት መሪዎች አይናቸውን ሲያጎረጠርጡባቸው ለዶ/ር አብይ የገቡትን ቃል ያጥፉና ”ህወሀት ወይም ሞት” እንደሚሉም ታዝበናል። ከእሳቸው ሌላ አንዳንድ የህወሀት ሰዎች አጥር ላይ ተንጠልጥለው ወይ አይደምሩ ወይም ከተቀነሱት ጎራ አይቀላቀሉ እንዲሁ መሀል ሜዳ ሲዋልሉ ከርመዋል። የሰሞኑ አርምጃ ግን ሰልፍ የምታስተካክል ሆነች። ደብረጺዮንም መወላወሉን አቁመው መደመሩ ላይ የጸኑ መስለዋል። የፓለቲካ ታክቲክ ሊሆን አይችልም። ህወሀትን ይዞ ከእንግዲህ የትኛውም ጨዋታ አያዋጣም።
ዶ/ር ደብረጺዮን ማድረግ ያለባቸው በዙሪያቸው ያሉትን የለውጥ ሀይሎች ሰብስበው ህወሀትን በይፋ አፍርሰው አዲስ ድርጅት ማቋቋምና የትግራይን ህዝብ ልብ ማረጋጋት ነው። ህወሀት መፍረስ አለበት። በጀርመን የናዚ ፓርቲ በይፋ የታገደ ነው። ሂትለር የሚለውን ስም ለልጅ ማውጣት የተከለከለ እንደሆነም ሰምቼአለሁ። ከተሳሳትኩ ልታረም። ህወሀትም እንደዚያ መደረግ አለበት። የኢህ አዴግ ምክር ቤት የትላንት መግለጫ የህወሀትን መንግስት ሽብርተኛ ሲለው በገደምዳሜ ሰይሞታል። ሲያልቅ አያምርም ነው። ህወሀት ጠፍጥፎ የሰራው ኢህ አዴግም ፈጣሪው ላይ እርግማን ሲያወርድበት ከመስማት በላይ ለህወሀት ሞት የለም።
እናም ዶ/ር ደብረጺዮን አሻሮ ይዘው ከቆሎ መደባለቅ እንደማያዋጣ ሊረዱት ይገባል። በቪዲዮው ላይ እንደምንሰማው ከሆነ በለውጡ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ደግፈውታል። የገዛ ጓዶቻቸውን ”ማን ተልከስከሱ አላቸው?!” ማለት ከጀመሩ በኋላ ህወሀትን ይዘው መቀጠል የለባቸውም። የምን ወዲህና ወዲያ ማለት ነው? ህወሀት ታሪኩ ጨለማ ነው። ጥቁር ነው። አጸያፊ ነው። የክፋት መገለጪያ፡ የጭካኔ መታወቂያ ነው። ስሙ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዳይጠራ ጭምር ተደርጎ ከነጉድፉ መቀበር ያለበት ድርጅት ነው። እሳቸው ለውጡን ለትግራይ ህዝብ መልካም ጊዜ ይዞ እንዲመጣ ከፈለጉ የመጀመሪያው እርምጃ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር  እንዳይገናኝ የልዩነት ግድግዳ የገነባውን ህወሀት የተሰኘውን የማፊያና የእርኩሳን ድርጅት ከደደቢት ዋሻ ስር አርቀው መቀበር ነው።
በነገራችን ላይ የሰሞኑ እርምጃ ህወሀቶችን ብቻ ሳይሆን ትጥቅ አንፈታም ብለው የለውጡ ሂደት ላይ መሰናክል የደቀኑ ኦነግን የመሳሰሉ ሃይሎችንም ጭምር ጸባይ እንዲያሳምሩ ሊያደርግ የሚችል ነው። ህውሀትና አክራሪ የኦነግ ቡድን ጥምረት ፈጥረው ለለውጡ አደጋ መደቀናቸው የአደባባይ እውነት ነበር። ህወሀቶች ኦነግ ላይ ተንጠልጥለው ለውጡን ለመቀልበስ ያደረጉት መፍጨርጨር ሳይሰምርላቸው ቀርተዋል።
ኦነግም ህወሀትን ተማምኖ፡ ከነትጥቄ እያስፈራራሁ የምፈልገውን አስፈጽማለሁ ብሎ ወገቡን ታጥቆ ተነስቶ ነበር። የዶ/ር አብይ አህመድ የሰሞኑ እርምጃ ሁሉንም ወደ ሀዲዱ እንዲገቡ አድርጓል። ኦነግ በህወሀት መሪዎች ላይ የተጀመረውን ምንጠራ ተከትሎ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ያለምክንያት አላደረገውም። የተማመነበት የህወሀት ቡድን አከርካሪው ከተመታ በኋላ ለኦነግ ምንም ምርጫ አይኖረውም። የአስመራውን ስምምነት ላለመቀበል ለሁለት ወራት ሲያንገራግር ቆይቶ እነጄነራል ክንፈ ከርቸሌ ሲወርዱ ኦነግም ረብሻውን ለማቆም መስማማቱን ሰምተናል። ጥሩ ነው። ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ………
Filed in: Amharic