” የኩነኔ ደሴቶች’’

ከሞገድ እጅጉ

ሪዞርቶቹ የአረብ ኤሚሬት መዝናኛዎች ናቸው። ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ታዳጊዎች ጋር እየማገጡ ነው። የጄፍሪ ኢፒስቴን ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደገመ። ዕድሜ ለብርሃኑ ነጋ! 

አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ እንደተመረጠ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬት ሄደ። የአረብ ኤሚሬት ንጉሥ መሀመድ ቢን ዛይድን አገኘ። ቢን ዛይድ ቤተሰቦቹን አስጎበኘው። ይሄ ወንድሜ ነው ፣ ይቺ እህቴ ናት… እያለ አስተዋወቀው። ንጉሡ “ ይቺ ደግሞ እናቴ ናት” ሲል፤ አብይ አህመድ በፍጥነት ከቢን ዛይድ እናት እግር ወደቀ። የቢን ዛይድ ቤተሰብ ተደናገጠ!
“ተነስ ምን ፈልገህ ነው? አሉት። አብይ አህመድ “የጡት ልጅ አድርጊኝ እና የቢን ዛይድ ወንድም ልሁን” አለ። አለበለዚያ አልነሳም ብለው አስቸገረ። የቢን ዛይድ እናት “በቃ ልጄ ነህ! ቢን ዛይድ ወንድምህ ነው” አለችው። አብይም ደስ ብሎት ተነሳ።
እዚህ ላይ የአረቦችን የጡት ልጅ ባህል በጥቂቱ እናስታውስ። በአረቦች ባህል ለወንድ የሚሰጠው የጡት ልጅነት ወይም ኢብን ቢል ረዳዓህ ይባላል። ጥንታዊ አጀማመሩ እናት ለሌለው ልጅ ወይም እናቱ ጡት ማጥባት ለማትችል ልጅ ጡት የማጥባት ድጋፍ ነበር። በዘመናት ሂደት ግን ወደ ማህበራዊ ድጋፍ ማደግ ችሏል።
በነገራችን ላይ ይህ ልማድ ኢትዮጵያ ውስጥም በአንዳንድ አካባቢዎች አለ። ድጋፍ ያስፈልገኛል ብለው የሚያስቡ ሰዎች አንድን ባለሀብት ወይም የአካባቢ ባለሥልጣን ወደ ቤተሰቡ ሄደው ጡት ይጠባሉ። እንቶኔ የእንቶኔን ጡት ጠባ ከተባለ የዚያን ሰው ድጋፍ ፈልጓል ማለት ነው። ልክ እንደልጅህ ሆኛለሁ እንደማለት ነው።
አሁንም በዘመናት ሂደት መልኩን ቀይሮ ከማህበራዊ ድጋፍ ወደ ፖለቲካዊ ድጋፍ አደገ ማለት ነው። አብይ አህመድ የቢን ዛይድን እናት የጡት ልጅሽ አድርጊኝ ሲል ቢን ዛይድ የሚያደርግለት ድጋፍ እንደማንኛውም አገራት መሪዎች የፖለቲካ አጋርነት ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ፍፁም ወንድማዊ የሆነ ድጋፍ እንድደረግለት ፈልጓል ማለት ነው። እነዘሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አብይ አህመድ የኢሜሪቱን ንጉሥ ቢን ዛይድ ወንድሜ እያለ ሲጠራው እንሰማለን።
አብይ አህመድ የቢን ዛይድ የጡት ልጅ መሆን ለምን ፈለገ? ከሌሎች አገራት መሪዎች ለምን ቢን ዛይድ ተመረጠ?
እንደሚታወቀው የተባበሩት አረብ ኢሜሬት ዋና ዓላማዋ ጠንካራ ናቸው የሚባሉ አገራትን ደካማ ማድረግ ነው። ለዚህም ግልጽ ማሳያው በአገራቱ ውስጥ የሚገኙ አማጺ ሃይሎችን ታስታጥቃለች። የኢሜሬት መገለጫ ይሆነው ነው። ልታፈርሳቸው በፈለገቻቸው አገራት ውስጥ አማጺ ኃይሎችን በማደራጀት የዚያችን አገር መንግሥት እንድቃወሙ ታደርጋለች።
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ይገኛል። ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር ነበረች። ይቺን ጠንካራ አገር ለማፍረስ አማጺ ሃይል ማደራጀት ሳይጠበቅባት ራሱ የአገሪቱ መሪ አፍራሽ ሆኖ አገኘችው። ስለዚህ በሌሎች አገራት ከምታደርገው በተለየ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን የተቃዋሚዎች ተቃዋሚ ሆና የመንግሥት ደጋፊ ሆነች ማለት ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያን ለማፍረስ አዋጪ ሆኖ ያገኘችው መንግሥት ተብዬውን ነው።
አምባ ገነን መሪዎች ሥልጣናቸው አደጋ ውስጥ ሲገባ መሸሺያ እና መደበቂያ አሳልፎ የማይሰጣቸው ወዳጅ አገር ይፈልጋሉ። አብይ የመረጠው አረብ ኤሚሬትን ነው። ለመሸሽ ብቻ ሳይሆን በሥልጣን ለመቆየት የሚያስፈልጉትን ነገሮች የምታሟላለት ኢሜሬት ናት። በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎችን እያፈናቀለ ለሚሰራቸው ብልጭልጭ ነገሮች ሁሉ አጋዡ ኢሜሬት ናት።

አብይ አህመድ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሪዞርቶችን ገንብቷል። እሱ ቱሪስት ለመሳብ ነው ይላል። እዚህ ላይ እንግዲህ ቱሪዝም ምንድነው? ቱሪስት ማን ነው? የሚጎበኘው ለምንድነው? የሚለውን ልብ እንበል።
ቱሪስት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሄደው ታሪካዊ ሥፍራዎችን እና የማሕበረሰብ አኗኗር ፣ አመጋገብ ፣ ከፍታ ቦታዎችን ፣ ብርቅዬ የዱር እንስሳትን ለማየት ነው። ለምሳሌ፤ ጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተ መንግሥት፣ ራስ ዳሽን ተራራ፣ የአፋር ኤርታሌ፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የአክሱም ሀውልት፣ ደቡብ ኦሞ…. የመሳሰሉትን ለመጎብኘት ነው። ምክንያቱም እነዚህ ቅርሶች የራሳቸው መልክ ያላቸው፣ በሌሎች አገራት የማይገኙ፣ የሰዎችን ቀልብ የሚይዙ ናቸው። ፈረንጆች በራሳቸው አገር የማያዩዋቸውና የማያገኟቸው ናቸው።
የአብይ አህመድ ሪዞርቶችስ?
የአብይ አህመድ ሪዞርት የማንንም ፈረንጅ ቀልብ መሳብ አይችልም። ምክንያቱም ለፈረንጆች ሪዞርት ብርቃቸው አይደለም። ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ሪዞርት ሰልችቷቸው ለየት ያለ ሌላ የጥንት ነገር ለማየት ነው። የአብይ አህመድ ሪዞርት የቱንም ያህል አብረቅራቂና ብልጭልጭ ቢሆን ከፈረንጆች ሊበልጥ አይችልም።
“ለፈረንጆች ብቻ አይደለም!” ሊባል ይችላል። ታዲያ ሌላ ለማን አገር ነው የተሰራው? የየትኛው አገር ዜጋ ነው ብልጭልጭ ነገር ብርቅ ሆኖበት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው? የአገር ውስጥ ጎብኝም ቱሪስት ሊባል ይችላል። የትኛው የአገር ውስጥ ዜጋ ነው ጦጣ እና ዝንጀሮ ወይም ሳር ብርቅ ሆኖበት ሊጎበኝ የሚሄደው?
በሌላ በኩል፤ ሪዞርቶቹ የሚሰሩት በብዛት ጫካ ውስጥ እና በረሃ ቦታዎች ውስጥ ነው። ይሄም ችግር አልነበረውም። አካባቢዎቹ የፀጥታ ሥጋት ያለባቸው ናቸው። አገሪቱ በአራቱም አቅጣጫ በጦርነት የምትናጥ ናት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰሙት መረጃዎች በሪዞርቶች አካባቢ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን ነው። ከአዲስ አበባ 100 ኪሎ ሜትር ባልሞላ ርቀት ውስጥ ሰዎች ይታገታሉ። ሰዎች የእናትና አባታቸው ቀብር መሄድ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ጦጣ እና ዝንጀሮ ለመጎብኘት ማን መስዋዕትነት ይከፍላል?
[2/23, 11:20 PM] Shewie Retta: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚሰሙ መረጃዎች እነዚህ በአረብ ኤሚሬት የሚሰሩ ሪዞርቶች የአረብ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች እና የተለያዩ የአረብ አገር ባለሐብቶች ለአቅመ ሄዋን ካልደረሱ ታዳጊዎች ጋር የሚማግጡበት ነው። ቦታዎቹ በሪፐብሊካን ጋርድ ይጠበቃሉ። ወደ እነዚያ ሥፍራዎች ዝር የሚል የለም፤ እንደተባለው ቱሪስት የሚሄድባቸውም አይደሉም ማለት ነው። አንድ ሰው ወደ ሪዞርቶች ሂጄ መዝናናት እፈልጋለሁ ቢል እንኳን የሚሄድበትን ቀን የሚወስንለት መንግሥት ነው። መጎብኘት የሚቻለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሲፍቅድ ብቻ ነው።
ነገሩ ልክ እንደ ጄፍሪ ኢፒስቴን ያለ ነው። ጄፍሪ ኢፒስቴን የራሱ ደሴት ነበረው። የታላላቅ እና የድሃ አገር መሪዎች ፣ ዝነኛ ሰዎች ፣ ሳይንቲስቶች፣ የንጉሳዊያን ቤተሰቦች ወዘተ ወደ ኢፒስቴን ደሴት እየሄዱ ለአቅመ ሄዋን ካልደረሱ ታዳጊዎች ጋር ሲማግጡ ኖረዋል። አሁን ላይ የኢፒስቴን ፋይል እየተዘከዘከ ነው። ዘነኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ባለሐብቶች ፈርተዋል። ጉዳቸው እየወጣ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሪዞርቶችም ለምን ሥራ እንደዋሉ ወደ ፊት መውጣቱ አይቀርም። የአረብ ባለሐብቶች እና ባለስልጣናት በግል ጄቶቻቸው በሚስጥር ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ወደ ሪዞርቶቹ እየሄዱ ይገኛል። እድሜ ለብርሀኑ ነጋ ታዳጊዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዳያልፉ ተደርገዋል። ታዳጊዎቹ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ከአረብ ባለሀብቶች እና ንጉሳዊያን ጋር መተኛት ግድ ሆኖባቸዋል።
እነዚህ ደሴቶች(ሪዞርቶች) ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ ሴራዎችም የሚሰሩባቸው ናቸው። አገራትን በማፍረስ የምትታወቀው የተባበሩት አረብ ኢሜሬት እነዚህን ሪዞርቶች ያሰራቻቸው ምን እንደሚጠቅሟት አስልታ ነው።
ወደፊት የሚሆነውን ነገር ወደፊት የምናየው ሆኖ እስካሁን ባለው ግን የአብይ አህመድ ሪዞርቶች ብርሃኑ ነጋ ትምህርት እንዳያልፉ ያደረጋቸው ወጣት ሴቶች የባለሀብቶችና የባለሥልጣናት የወሲብ ባሪያ የሚሆኑበት ሆኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.