በዐማራ ደም የጨቀየው ርእዮትና አመለካከቱ!

አዲስ ተስፋ

የተማሪዎች እንቅስቃሴ (በተለይም በ1960ዎቹ እና 1970ዎቹ የተነሳው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማርክሲስት ሌኒንስት የግራው እንቅስቃሴ በወቅቱ የነበሩ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጭቆናዎችን ለመታገል ቢነሳም በቀየሰው የርዕዮተ-ዓለም አቅጣጫ እና በወሰዳቸው አቋሞች ምክንያት በዐማራ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ታሪክ ላይ ከፍተኛ ታሪካዊ ስህተት እና ጉዳት አድርሷል ። ለዘመናዊውና የዐማራን ዘር ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው በተጨባጭም በሚሊየን የሚቆጠር ዐማራ ለጨፈጨፈው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መወለድ ና ማደግ ዋና ተጠያቂ ነው። ይህ መራራ እውነት በብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች እና የፖለቲካ ተንታኞች ይታወቃል።

ይህ ትውልድ በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸማቸው የታሪክ ክህደቶች እና ያደረሳቸው ጉዳቶችን ዘርዝሮ መመጨረስ አይቻልም። እስኪ ባህርን በማንኪያ ያህል የትውልዱን ነውሮች ልጠቃቅስ:

1. ዐማራን ጨቋኝ ብሔር አድርጎ መፈረጅ

የተማሪው እንቅስቃሴ ትልቁ እና መሠረታዊው ስህተት የስታሊንን የብሔር ጥያቄ ንድፈ-ሐሳብ ያለ ምንም ተጨባጭ የታሪክ እና የማህበረሰብ አውድ ቀጥታ በኢትዮጵያ ላይ ለመተግበር መሞከሩ ነው።አብዛኛው የእንቅስቃሰው አራማጆች ከመጋረጃው ጀርባ ያለውን ሃይል የተደበቀ አጀንዳ በመቀበል የትርክቱን መነሻና መድረሻ ሳይገነዘቡ ወጣት ዐማሮችን ከፊት በማስቀደም ነገር ግን ደግሞ በጸረ ዐማራ ቡድኖች ኦርኬርስትሬት በተደረገ ዐማራ ጨቋኝ ነው የሚል ወረቀት በማስጻፍና ዋና ዋና ዐማሮችን በማስገደል የተጀመረው የዘር ማጥፋት እነሆ ዛሬም ሳያባራ እንዲቀጥል አድርጓል።በአንድ በኩል ዐማራውን ራሱን በጅምላ እንደ ተጨቋኝ እና ጨቋኝ ክፍል ከፍሎ በማቧደን እርስ በእርስ አጫርሷል። ልጅ አባቱን ጨቋኝ ወይም የመሬት ከበርቴ ነው ብሎ እንዲያጋልጥ በማድረግ እንዲረሽን ሚስት ብሏንና የልጆቿን አባት በእኩልነት አያምንም ጨቋኝ ነው በማለት ስታሳስር ብሎም ስታስገድል የዘር ጭፍቸፋውን የሚመሩትና ዐማራ ጨቋኝ ነው የሚል ትርክት የፈጠሩት ቁጭ ብለው ትእይንቱን እንደትያትር ይመለከቱ ነበር። ከሰማንያ የሚልቁ ከፍተኛ የአገር መሪዎች በደርግ ተስብስበው ሲረሸኑ የዐማራን ኤሊት ማጥፋት እንደነበር አንድም የተማሪዎች እንቅስቃሴ አባል የነበረ ሊነግረን አይሞክርም። በሌላ በኩል ደግሞ ሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ዐማራን እንደ ብቸኛ ጨቋኝ ብሔር ተደርጎ ስለተፈረጀለት ጸረ ዐማራ የሆነ የፖለቲካ ማህበረሰብ እንደፈጠር ሆኗል። በጠቃላይ ዐማራ ጨቋኝ ነው የሚለው ትርክት ወጤት ድሀው፣ ገበሬው እና በየክፍለ ሀገሩ በችግር የሚኖረው የዐማራ ሕዝብ ከንጉሣዊው ሥርዓት ምንም ዓይነት ልዩ ጥቅም ሳያገኝ በሥርዓቱ ስም እንደ ጨቋኝ ተቆጥሮ የጥላቻ እና የቂም በቀል ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል::

2. የሀገረ መንግሥቱን እና የታሪክ መሠረቶችን ማፍረስ

የተማሪዎች እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ረጅም የታሪክ መሠረት፣ አንድነት እና ባህል ከመጠበቅ ይልቅ እንደ የብሔረሰቦች እስር ቤት አድርጎ በመሳል ማሳነስ ብቻ ሳይሆን የ ሃገረ መንግስቱ የጸና መሰርት እንዲፈርስ አድርጓል። በዚህ የታሪክ መዛባት ሂደት ዐማራው ለዘመናት ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ያቆያትን ሀገር እና ታሪክ እንደ ግፍ እና ጭቆና ውጤት አድርጎ በማቅረብ መላው የኢትዮጵያ ህዝቡ ታሪኩን እንዲክድ ለብዙ ሺህ አመታት ለዓለም ምሳሌና የነጻነት ዓርማ የሆነውን ወርቃማ ታሪኩን እንዲሸማቀቅበት አድርጓል። ባሮን ሮማን ፕሮቻስካ የተባለው ሰው አቢሲኒያ ዘ ፖውደር ባሬል(Abyssinia: the powder barrel) በተሰኘው የጥናት ምክረሃሳቡ አፍሪካ ለቅኝ ገዥዎች ምቹ መደላል እንዳይፈጠር እንቅፋቱ አቢሲኒያውያን መሆናቸውን በመጥቀስ የእነርሱ ጥንካሬ የሚመዘዘው ደግመ ከዐማራ ስለሆነ ዐማራን ለማዳከምና ለማጥፋት የሚያገለግል አዲስ የፖለቲካ ርእዮት ያስፈልጋል ። ያም የብሄር ብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል የሚለውን ጽንሰሃሳብ መደገፍና ብሄረሰቦች ይህን የመብት ጥያቄ ሲያቀርቡ ወዲያውኑ መርዳትና ማገዝ አማራጭ የሌለው ስልት መሆኑን ባቀረበው ምክረሃሳብ የተመሰረተውን የብሄር ብሄረሰቦች ጭቆና ትርክት ይዞ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ብቅ በማለቱ የጸናውን የሃገረ መንግስት ስርዓት በመካድ ለዐማራ የዘር ጭፍጨፋ መደላድል በመሆን አገርንና ታሪክን ክዷል። ። በዐማራ ቋንቋ እና ባህል የተደረገው እጅግ ነውር የበዛበት ዘመቻም የሀገረ መንግሥቱን እና የታሪክ መሠረቶችን የማፍረስ አካል ነው።የዐማርኛ ቋንቋ እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የዐማራ ሕዝብ ማንነት ዋና አካላት ናቸው ተብሎ ስለታመነ የጭቆና መሳሪያዎች ተደርገው እንዲሳሉ አድርገዋል።

3. ለጽንፈኛ ብሔረተኛ እንቅስቃሴዎች መንገድ መክፈት

በሚያደርጉት ነውር ሁሉ ራሱን ዐማራን ተጠያቂ ለማድረግ ዛሬ ዛሬ ጽንፈኝነት የሚለው ጽንሰሃሳብ ለዐማራ ለምስጠት ሲሞክሩ ይታያል። በመሰረቱ ዐማራነት ጸረ ጽንፈኝነት እንደሆነ ማወቅ ተስኗቸው አይደለም። ይህንን ቃል ዐማራ የሚድነው ወደ ዐማራነት በመመለስ ብቻ ነው የሚሉ እውነተኞችን ጽንፈኛ ለማለት የሚሞክር የዐማራ የዘር ጭፍጨፋ አካል የሆነ ብቻ ነው። ወደ አነሳሁት ዋና ፍሬ ነገር ስመለስ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ የተፈጠሩት የብሄር ብሄረሰብ ጽንሰ ሀሳቦች በተለይም ዋለልኝ መኮንን የጻፈው ወረቀት በኋላ ለተፈጠሩት የብሔር ጽንፈኛ ድርጅቶች እንደ ህወሓት፣ ኦነግ ወዘተ ፍልስፍናዊ እና ፖለቲካዊ መሠረት ሆኗል ። እነዚህ ድርጅቶች የተማሪውን እንቅስቃሴ የብሔር ትንተና መነሻ በማድረግ ዐማራውን የጋራ ጠላት አድርገው በመሰየም የፖለቲካ ቅስቀሳቸውን አካሂደዋል። ይህም ዐማራው በገዛ ሀገሩ ላይ እንዲገለል እንዲፈናቀል እንዲጠቃና ዘሩ እንዲጨፈጨፍ በሩን ከፍቷል።

4. የገበሬውን እውነተኛ ችግር አለመረዳት

የተማሪዎች እንቅስቃሴ መሬት ለአራሹ የሚል መፈክር ያነሳ ቢሆንም የሰሜኑን በተለይም የዐማራው ርስት የመሬት ስርአት አወቃቀር በአግባቡ አልተረዳውም ነበር። በደቡብ የነበረውን የጭሰኝነት ስርዓት እና በሰሜን የነበረውን የርስት ስርዓት ሳያያይዝ በአንድ ላይ ደባልቆ በመውሰዱ የዐማራ ገበሬ መሬቱን እና ባህላዊ ሀብቱን በደርግ ዘመን በኃይል እንዲቀማ እና እንዲደኸይ ምክንያት ሆኗል።

5. በደሙ የገነባትን ሀገር ፖለቲካዊ መፃኢ እድል ማጣት

በዚህ እንቅስቃሴ ምክንያት በተፈጠሩት የግራ ዘመም ድርጅቶች እንደ ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ደርግና ወዘተ ባሉ አውዳሚ የፖለቲካ ግጭቶች ለምሳሌ በቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር የተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ብቁ እና የተማሩ የዐማራ ወጣቶች አልቀዋል። በመጨረሻም የዚህ እንቅስቃሴ ውጤት የሆነው የ1984ቱ (1991 እ.ኤ.አ) የፖለቲካ ሽግግር ዐማራውን ያገለለ እና በሕገ መንግሥቱ ላይ እንግዳ የሚያደርግ ሥርዓት የብሔር ፌደራሊዝም እንዲዘረጋ አድርጓል።የዐማራ የዘር ፍጅትንም ስርዓታዊና መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እንዲከናዎን ምቹ ሁኔታን ፈጠረ።ዛሬ ሌሎች ከተቀበሉት ዐማራ ስርዓቱን የማይቀበልበት ም ክንያት የለም በማለት በድፍረት የዐማራን ቅዱስ የህውና ትግል ለማቆሸሽ የሚወራጩ ኤሊት ነን ባዮችን ስንስማ የትግላችንን መራራነትና ከፍተኛ ጽናት ጠያቂነት ብቻ ሳይሆን ይህ ትግል ከመነድ ያፈነገጡትን እየበላ መሄድ እንዳለበት ግልጽ ሆኗል።ዐማራ በደሙ ከገነባት ሃገር ኢንዲገለልና ዘሩ እንዲጨፈጨፍ የሆነው በማርቀቁ ሂደት ባልተሳተፈበት ህገ መንግስት ድጋፍ በተቋማት በታገዘ የመንግስት መዋቅር ነው። ይህን ስርዓት ዐማራ የማይቀበልበት ምንም ምክንያት የለም ማለት ወይም እንደ ገዱ አንዳርጋቸው ሁሉ እንደዚህ ህገመንግስት ዐማራን የሚጠቅም ስነድ የለም ብሎ መናገር ያለምንም ጥርጥር ለዐማራ የዘር ጭፍጨፋ ደረጃ መገንቢያ ጡብ ማቀበል ነው።

ማጠቃለያ

የ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ለፍትህ እና ለእኩልነት ተነሳሁ ቢልም ሀገራዊ እና ማህበራዊ አውዶችን ካለመረዳት የተነሳ ያመጣው የርዕዮተ ዓለም አቅጣጫ ዐማራውን የታሪክ ባለዕዳ የቂም በቀል ሰለባ እና በገዛ ሀገሩ የፖለቲካ የበይ ተመልካች ከማድረጉም በላይ ያላበራ የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድበት ሆኗል።ከዚያ ትርክት ሰለባዎች መካከል ዐማራንና ሃገረ መንግስቱን ሊያድን የሚችል ሃይል ሊዎጣ አይችልም።አሁን ያለው የመንግስት ስርዓትም የቆመው የዐማራን ደም በማፍሰስ ነው።ይህ ስርዓት እንዲገነባ ያድረጉት የትርክቱ ባለቤቶች ግማሾቹ የመንግስት ስራ አስፈጻሚዎች ሆነው ሌሎች ደግሞ ስርዓቱን እንቃወማለን በማለት በሌላ ጎራ ተሰልፈው አሁንም የዐማራን መካራ ለማስቀጥል ይተጋሉ።ለዚህ የዐማራ ዘር መጥፋት አሳላጭ ሚዲያዎችና ፖለቲከኞች ዛሬም አሉ። የዐማራ የህልውና ትግል ንጽህናውን የጠበቀ ከቆሸሸ አመለካከትና ከውሸት የጸዳ ስርዓቱንና ትርክቱን ከስሩ መንግሎ ለመጣል የተዘጋጀ ስርነቀል ርእዮትን አንግቦ ስብዓዊነትንና ፍትህን መሪው አድርጎ አውራመንገዱን ይዟል።

እዚህም እዚያም የሚፈጠሩትን ፍንጣቂ ቆሻሻዎች ዐማራነት በራሱ ያጸዳቸዋል። የዘር ጭፍጨፋው ሞተር ትርክት በእውነተኛው የዐማራ እሴት እውነት ይጸዳል። የተማሪዎች እንቅስቃሴ አንኳር የትግል መነሻ የሆነው ዐማራ የብሄር ብሄረሰቦች ጨቋኝ እንደነበር በግልጽም በስውርም የተገነባ አስቀድሞ በቅኝ ገዥዎች ምክረሃሳብ ከዚያም በጸረ ዐማራ የውስጥ ሃይሎች ይሁንታ ያገኘ የሃሰት ትርክት የሚፈርሰው ስርዓቱን በመለወጥ ነው። አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ የዐማራን መከራና የዘር ጭፍጨፋ አንድም ከዋና አሳላጮች ጋር በዐማራ ስም ህብረት ለማድረግ የምትሞክሩ ሁለትም ዐማራ ሌሎች ከፈለጉት ስርዓቱን የማይፈልግበት ምክንያት የለምና ከህገመንግስቱ ጋር ዐማራ ጸብ የለውም ለምትሉ ደሮ ብታልም ጥሬዋን እንዲሉ ለእናንተ እውቅና ወይም ስልጣን ወይም እንጀራ የዐማራ ደም መፍሰስ አይቀጥልም። የዐማራን የዘር ጭፍጨፋ የሚቀበልና የሚያስቀጥልን ስርዓት ህሊና ያለው የይደለም ዐማራ የሰው ልጅ አይኖርምና ራሳችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። ዐማራ በዐማራነቱ አንድነቱን ህብረቱንና እሴቱን ጠብቆ ራሱን ከዘር ጭፍጨፋ የማዳኛ ጊዜው አሁን ነው።

ድል ለዐማራ ህዝብ !
ድል ለኢትዮጵያ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.