>
11:23 am - Sunday May 22, 2022

ዶ/ር አቢይ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡ - ፈጣን ውሳኔ የሚሹ ሁለት ፖለቲካዊ ስንክሳሮች!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ዶ/ር አቢይ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡ – ፈጣን ውሳኔ የሚሹ ሁለት ፖለቲካዊ ስንክሳሮች!!!
ቬሮኒካ መላኩ
አሁን ጠ/ሚ አቢይ አህመድ የገለጥከውና ያለህበት የፖለቲካ ምእራፍና ገፅ በ1889 አፄ ዮሀንስ መተማ ላይ ሞተው አፄ ምኒልክ ስልጣኑን ሲይዝ ከገጠመው ታሪካዊ ምእራፍ ጋር እጅግ በጣም ተመሳሳይ ነው!
ጃ Warን እርሱት ።አጎዛ ነገር ነው። እንቁላል ለመጣል እንደምታስካካ ቄብ ዶሮ ሲቁነጠነጥ አደረ።  ጃ war ከሜቴክ የበለጠ ለዚች አገርና ለአቢይ መራሹ መንግስት አደገኛ ጋንግሪን  ነው። ጃዋር ራሱ በየደቂቃው  የማያልቅ አዙሪት እየዞረና Vicious Circle ሲሰራ እየዋለ ደብረፂዮንን በ ” U  turn ”  ሊወቅስ አይችልም።
ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን “The pendulum of opportunism never stops oscillating” ( የአድርባይነት ፔንዱለም መወዛወዙን መቼም አያቆምም  ) እንደለው ጃዋር መሀመድም እንደፔንዱለም  ሲወዛወዝና  ሲገለባበጥ እየዋለ ደብረፂዮንን በአቋም መቀየር ለመውቀስ አፉን ሲከፍት የፋራ ጮሌነቱ አስደነቀኝ።
ደብረፂዮን ትናንትም አቋሙን ቀይሮ አላየንም  ፣ ዛሬም አልቀየረም፣ ነገም ይቀይራል ተብሎ አይታሰብም። For that matter ፒኖቼ ፣ አዶልፍና ፖልፖት ተደምረው ያልሰሩትን ዘግናኝ ጭካኔ የፈፀመን ጌታቸው አሰፋን ስልጣን በመስጠት በክልሉ ያስቀመጠውን ደብረፂዮንነ  ” ተደምሯል ” እያሉ መጃጃል ወፈፌነት እንደሆነ ገብቶኝ ነበር።
ጃዋርና የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ የአእምሮ መቀንጨር ችግር ከሌለባቸው በስተቀር ደብረፂዮንን ሁለት አቋም  ኖሮት አያውቅም ። የወልቃይት አማሮች ጀኔራል ክንፈን በመያዝ  ለመከላከያ ያስረከቡበትን ገድል ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል “የትግራይ ፖሊስ የሜቴኩን ጄኔራል ይዞ አስረከበ “የሚል አርቲፊሻል ዜና በመስራት ራሳቸውን በማታለል  ደብረፂዮንን ትናንት “ተደመረ” በማለት አሞግሰው ዛሬ መልሰው ቢወቅሱ  መሳቂያ የሚሆኑት እነጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ ብቻ ናቸው።
ደብረና ህውሃቶች ሁሌ አቋማቸው አንድና አንድ ነው። ህውሃቶች ከ Day one ጀምሮ የዚህን መንግስት መሪ ከመግደል ጀምሮ ስርአቱን ለመገንደስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። አሁንም በዛው አቋማቸው ላይ ናቸው።
ወደፊትም በፍጥነት  መፍትሄ ካልተፈለገላቸው የአቢይን መንግስት ምስጥ እንደበላው ግንድ ቦርቡረው ወደ አፈርነት መቀየራቸው አይቀርም።
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ  ይልቁንስ በአጉል ፋንታዚና አፒዝመንት  ራስን ከማታለል የሚከተለውን የፖለቲካ ክኒን ለትግራይ ክልል ትሰጥ ዘንድ ትመከራለህ ።
አሁን ጠ/ሚ አቢይ አህመድ የገለጥከውና ያለህበት የፖለቲካ ምእራፍና ገፅ በ1889 አፄ ዮሀንስ መተማ ላይ ሞተው አፄ ምኒልክ ስልጣኑን ሲይዝ ከገጠመው ታሪካዊ ምእራፍ ጋር እጅግ በጣም ተመሳሳይ ነው።
ትግራይ ከአፄ ዮሀንስ ሞት በኋላ ለምኒልክ አልገዛም በማለት ስትንፈራገጥ ምኒልክ ወደ ትግራይ ዘምተው ሁለት ጥይቶች ጠሽ ጠሽ በማድረግ ችግሩን ፈተውታል።
አቢይ አህመድ የአፄ ምኒልክ የአመራር ጥበብና ቆራጥነት  በአንድ ጊዜ እንድደርስበት መጠበቅ የሂማሊያን የተቆላለፈ ተራራ ውጣ እንደማለት ስለሆነ እሱ ተገቢ አይደለም።
አቢይ አህመድ አሁን ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ  ነው …
1ኛ~ የአፄ ምኒልክን መንገድ በመከተል ትግራይን ማንበርከክና መሪነቱ 8ቱን የፌደሬሽን ክልሎች ብቻ ሳይሆን ዘጠነኛዋን ትግራይንም እንደሚጨምር  ማረጋገጥ ።
2ኛ~ የሀይለማሪያም ደሳለኝን መንገድ ተከትሎ መንበርከክና   ወደ “ነበር”ነት መቀየር ።  ሁለቱም ምርጫ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡና ውሳኔ የሚሹ ፖለቲካዊ ስንክሳሮች ናቸው
Filed in: Amharic