>
6:43 am - Wednesday December 7, 2022

ዓቢይና-ደብረጽዮን፤ ሊንከንና ጀፈረሰን (ፍጹም አለሙ)

ዓቢይና-ደብረጽዮን፤ ሊንከንና ጀፈረሰን
ፍጹም አለሙ
እያሟረትኩ አይደለም። እንደው ታሪካዉ ግጥምጥሞሽ ያለ ስለመሰለኝ ነው።ለጀማሪዎች፥
ሊንከን የአሜሪካ ፕሬዚደንት ነበር ከ1861-1865።በዛም ጊዜ አሜረካ ሀገር እርስ በርስ ጦርነት ነበር።ደቡቡ ክፍል እራሱን ከፌዴራል መንግስቱ ገንጥያለሁ ብሎ ጀፈርሰን ዴቪስን ፕሬዚደንት አርጎ መረጠ (ከ1861-1965)።ዋናው ጥል ባርነት ይቀጥል አይቀጥልነበር።
እንዲህ ዓይነት ውጥንቅጥ ውስጥ የድሮው የአሜረካን ፕሬዚዳንት አብረሀም ሊንከንም ገብቶ ነበር። አብርሀም ሊንከን የአሜሪካ  የእርስ በርስ ጦርነቱ(1861-65)ከመጀመሩ በፊት አማካሪዋቹ ጋ ሲመካከር ባንደ ወቅት “አንተ ምትገፋው ‘ባርነት ይቅር !”ሀሳብ ሀገሪቱን ይበታትናታል “ሲሉት “ሀገር ከሚበተን የባርነት ስርዓት ይቀጥል ብሎ ነበር”።
በኃላ ግን አማካሪዋቹ “አይ ግዴለም እንዋጋ እንሸንፋለን “ሲሉት ሀሳቡን ቀይሮ፣ “ሪስክ” ወስዶ ወደ ጦርነት ገባ ።
 በእንዱስትሪ የበለፀገው ሰሜንና በእርሻ ና ባርያ
የሚተዳደረው ደቡብ በፌዴረሸንና በኮንፌዴሬሽን ብሎም ደቡብ እስከመገንጠል በሚለው አቋሙ ሴሜኖቹ ባርነት ይቅር የሚለው አቋማቸው ረድቷቸው ጦርነቱን በድል ለመወጣት አስቻላቸው። በባሪያ ንግድና ጉልበት ኢኮኖሚው የተመሠረተው ደቡብ ተሸመድምዶ ወደቀ።
ሰሜኖቹ ባሪያውን ነፃ አድርገው ከዛ በፊት ያልነበረውን ወታደር መለመሉት ይህ በደቡብ ሲሰማ
ባርያው ሁሉ የጌታውን አገልግሎት በመተው እየሾለከ ወደ ሰሜን ጎረፈ ይህም ለደቡብ ኢኮኖሚውን ሲያሽመደምድ ለሰሜኑ በሚያውቀው ቦታና ስነልቦና በብቀላ በቆራጥነት የሚዋጋ የሰው ሀይል  ፈጠረለት። የደቡብ ጦር መሪ ጀነራል
ሊ አጅን በመማረክ ሰሜኖች የመጨረሻዋን ድል ተጎናጽፈው ለአንድ አሜሪካ መሠረት ጣሉ።
ባርነትም ቀረ፣ አሜሪካንም አንድ ሆና ቀጠለች።(see, Team of Rivals by Goodwin)
አሁን ወደ እኛ እንምጣ፥
ደብረጽዮን..ሲታሰር ወደእኔ ሲፈታ ወደእሱ ሆኗል:-
ደብረጽዮ ከትግራይ ክልል ሲወጣ ይደመራል፣ትግራይ ተመልሶ ሲገባ ይቀነሳል።ትናንት ሌባን አሳልፈለን እንሰጣለን ይላል፣ዛሬ ደግሞ (ሳምንቱ ማለቂያ ላይ ሽሬ ከበረከት፤ከዘረዓይ ከጌታቸው አሰፋና ከሌሎችጋ ሲዶልት ከረሞ ከመጣ በኃላ) ለምን ክንፈ ካቴና እጁ ላይ ገባ፤ትግራይ ላይ ዘመቻ ተጀመረ፣ህግና ፖለቲካ ተጣመረ እያለ ቡራ ከረዩ ይላል።ያው በል ተብሎ ነው።
እኔን ግራ ይግባኝ።
ዓቢይ ትግራይ ክልል ሄዶ ጌታቸውና ሌሌች በከፍተኛ ወንጀል የሚጠረጠሩትን ብሎም የመጣውን ለውጥ ለማደናቀፍ፤ መንግስትን ህጋዉ ባልሆነ መንገድ መለወጥ ብሎም ሀገርን ለመበጥበጥ የሚዶልቱትን ሰዋች ያሉበት ቦታ ሄዶ የማሰር መብት አለው።.ደብረጽዮን ደግሞ የመተባበር ግዴታ አለበት ወንጀሉ የፌዴራል ወንጀል ስለሆነ።
ዓቡይ የመያዣ ትዕዛዝ ከተቆረጠ በኃላ ቀኝ ኃላ ቢዞር ያው…ውርድ ከራስ ነው።
ዓቡይም ግን  ግራ የገባው ይመስላል።
እርስ በርስ ጦረነት ይነሳ ይሆን?በቢሊየንን የሚቆጠር ብርና ንብረት ያለው ህወሀት ሀገር ይበጥብጥ ይሆን? ሀገረቷ እንድትቀጥል “ሌባና ገዳዮችን”እንተዋቸው አንተዋቸው?”የሚል ሀሳብ ውስጥ የሚዋዥቅ ይመሰለኛል።
የህግ ገዢነት ሥረዓት እንዲሰፍን ከፈለገ ዓቢይ ዘመቻውን መቀጠል አለበት። አልያ ሌቦቹንና ገዳዮችን(ማለት ኢሀአዴግ ወስጥ ያሉትን ሁሉንም)እንተዋቸውና እንቀጥል ካለ ደግሞ ሕዝበ- ውሳኔ ይደረግ።
Filed in: Amharic