>

ደሴቷ ትህነግ!!! (የሺሀሳብ አበራ)

ደሴቷ ትህነግ!!!
የሺሀሳብ አበራ
* ትህነግ በአራቱም አቅጣጫዋ እርቃኗን ቁማለች፡፡ ወጀቡም ከብዷታል፡፡ወጀቡ ማስጠሙም አይቀርም!
 …
የድሮው አብዲ ኤሊ ከሶማሊያ የለም፡፡ አፋር  ፀረ ትህነግ ሆኖ ተነስቷል፡፡ በሃማሴን በኩል  ዝምድና አለኝ  ይሉ የነበሩት አጋዝያን በፕሬዚዳንት  ኢሳያስ በኩል መክኗል፡፡ ትህነግ እና የኤርትራ  የፖለቲካ ሃይሎች ላይጋቡ ተፋተዋል፡፡ ኤርትራ በትህነግ በሯን ጠርቅማለች(closed )፡፡
ኦነግ ከኦዴፓ ጋር ተቀናጅቶ የታክቲክም ሆነ የስትራቴጂክ አጋርነቱን ፊት ነስቷታል፡፡ አማራ ድሮም ጠላቴ ነው ብላለች ፡፡ አሁን ትህነግ ብቻዋን የመቆሟ ድንዝዜ እያስቃዣት ነው፡፡ (ትህነግ ድሮም ፍጥረቷ ከጫካ ስለሆነ ከተማ ገብታ ከሰው ጋር ለመኖር ከብዷት ስትናከስ ባጅታለች:; የጫካዊነት ባህሪዋ ወደ ሰውነት አላስጠጋሽ ብሏታል፡፡)
 …
የትህነግ ቅዥት(night mare of tplf)
 …..
በማረሚያቤት ግብረሰዶም የፈፀሙ፣ሰው የሰቀሉ፣ሃገር የበሉ፣ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊያስገድሉ የሞከሩ….. ሰዎችን መንካት የትግራይን ህዝብ ህልውና መዳፈር ነው አለች፡፡የትግራይ ህዝብ ህልውና  ግን   በግብረሰዶማውያን፣በሰው ዘር ላይ እልቂት ፈፃሚዎች ፣በሙሰኞች ላይ የተገነባ ነው ወይ?! አይደለም፡፡ እውን ጌታቸው አሰፋ እንኳን የትግራይን ህዝብ የሰውን ፍጥረት ይወክላል?!
 …
ተጠርጣሪዎች በመያዝ ሂደቱ ላይም የውጭ ጣልቃ ገብነት አለ አለች፡፡ማን ነው? ኤርትራን ለመክሰስ ያለመ ይመስላል፡፡ ኢሳያስ ከትህነግ በተቃርኖ በመቆማቸው የመጣ ጣጣ ነው፡፡ደግሞ ትህነግ የዘጋችውን በር ዶክተር አብይ መክፈቱ ምቀኝነትም ይዟታል፡፡ ትህነግ የበለጠ ከኤርትራ ጋር እየተቃቃረች ነው፡፡ ኤርትራ እና ትግራይን አዋህጀ የምስራቅ አፍሪካ ገናናው የአጋዚያን  መንግስት እመሰርታለሁ የሚለው ህልምም ቅዥት ሆኗል፡፡
 …
ካለኔ ፍቃድ የፌዴራል መንግስት ትግራይ አይመጣምም አለች፡፡አላማጣ ላይ መከላከያ መግባቱን በስህተትነት ገምግማለች፡፡ ጦርም አለን፡፡የራያ መንገድ ሲዘጋ በሰው ክልል ገብተን ማስከፈት እንችላለን፡፡ጦርነት ማለቂያ ስለሌው እንጂ መጀመሩ ቀላል ነው ስትል ጦርነት መሻቷን በይፋ አውጃለች፡፡ ሚጢጢ ክልል  ሆኗ  በሌለ አቅሟ በሌላ ግዙፍ ክልል ገብታ ጦር አነሳለሁ እያለች፣የፌዴራል መንግሥት  ደግሞ ትግራይን አይረግጥም ብላ ትደነብራለች፡፡ይህ መሳቷ  አቅሟን እና ወቅቱን ለማንበብ ካለመድፈር የመጣባት ጣጣ ሳይሆን አይቀርም ፡፡
 …
በተፃራሪው ደግሞ ህገመንግስቱን የጣሱ ክልሎች ይጠየቁ ትላለች፡፡ዘወትር የትህነግ የጥፋት መደበቂያ የሆነውን ህገመንግስት አማራን ለመክሰስ ትጠቀምበታለች፡፡አቶ ገዱን እና መላው አዴፓ አባልን  ህገመንግስት እና የፌዴራል ስራዓት አላከበርክም ስትል ትከሳለች፡፡ ስትገርፍ፣ስትገድል፣ስትዘርፍ የከረመችበትን ህገመንግስት ዛሬ ራሷን ለመከላከል  ታነሳዋለች፡፡ ትህነግ ከኢህአዴግ  መታገድ ያለባት ንዑስ ድርጅት ናት፡፡የኢህአዲግ ሊቀመንበርን(ዶክተር አብይን)  ሊያስገድል የሞከረውን አቶ ጌታቸው ለህግ ሳይቀርብ ኢህአዴግ ትህነግን አቅፎ   በግንባርነት ካስቀጠለ ኢህአዴግ የአጎብዳጆች ዳርቻነቱን ያረጋግጣል፡፡ ገዳይ እና ገዳይ  ህብረት ሊኖራቸው አይችልም ፡፡
፡…
 የትህነግ ፌዝ (Irony)
ከሁሉም የባሰው ፌዟ(Irony) ደግሞ የፀጥታ አካላትን  የገደለ በይቅርታ ተለቆ ያኮላሸ፣ የገረፈ፣ የዘረፈ ለምን ይታሰራል? ማለቷ ነው፡፡በቀጥታ ይህ ኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ተፈትቶ ለምን ጌታቸው አሰፋ ይታሰራል ለማለት የታሰበ ነው፡፡ ፡፡ካሁን በኃላ እስረኛ አሳልፋ እንደማትሰጥም አቋም ይዛለች፡፡ትህነግ 1960 ዓም ላይ ማሰብ ስላቆመች ብዙ አይፈረድባትም፡፡የሃሳብ እርጣት ደርሶባታል(idea pause)
 ..
ትህነግ ከማዕከላዊ መንግስቱም ሆነ ከአጋር ፓርቲዎች በነጭናጫ እና ስግብግብ  ባህሪዋ ወዳጅ አጥታለች፡፡ደሴት ሆናለች፡፡ሲበርዳትም፣ ጦርነት ላይ ነኝ ብላ በጌታቸው ረዳ በኩል ተናግራለች፡፡ብቻ ቁሞ ማሸነፍ እንደማይቻል እንኳ ታሪኳ አላስተማራትም፡፡
 …
ትህነግ በብቸኝነት የቀደመ ጓደኛዋ ሱዳን ለጊዜው ያቀረበቻት ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል  የአማራውን ጥያቄ ከሳሎን ወደ አደባባይ(inside conflict) እንዳይወጣ በቅማንት ስም ቅማንትን  የማይወክሉ ሰዎችን እያዘጋጀች ለግጭት ትሮጣለች፡፡ግጭት የትህነግ የነፍስያዋ ማራዘሚያ መድሃኒት  ነው፡፡ትህነግ ንዑስ ስለሆነች ብዙኃንን በማጋጨት የምትወፍር  ድርጅት ናት፡፡ ነገር ግን ቅማንት በትህነግ ሴራ ነቅቷል፡፡ከአማራ ወንድሙ የበለጠ የሚቀርበው እንደሌለ አምኖ የትህነግን መግቢያ ቀዳዳ እየደፈነ ነው፡፡በዚህ ዘመን ትህነግን መደገፍ ብልግናን ማራባት ነው፡፡
ትህነግ በሞት እየነገደች የመጣች የነውር ቆብ ናት!
የቀድሞው የትህነግ ፋይናንስ ሃላፊ አቶ ገብረመድህን አርአያ እንደሚሉት  በ 1977  ድርቅ ሲሆን ለትግራይ  ህዝብ ስንዴ ግዙ  ተብሎ በለጋሾች ታዘዘ፡፡ትህነግ ግን የትግራይ ህዝብ እየሞተ አሸዋ ሞልቶ ገዛሁ አለና በተሰጠው ብር የጦር  መሳሪያ ገዛበት፡፡በተቀረው ውስኪ ተጠጣበት፡፡ ከዛ ደርግ እህል እንዳይገባ ከለከለ ብሎ በትግራይ ህዝብ ሞት ፖለቲካ ነገደ፡፡ ትህነግ በሞት እየነገደች የመጣች የነውር ቆብ ናት፡፡  ትህነግ እንደ ትግራይ ህዝብ የበደለው የለም፡፡በ 28 ዓመታት ውስጥ የትግራይ  ወጣት ከአብዮታዊ  ዲሞክራሲ ውጭ ምንም እንዳያነብ ከልክላለች፡፡መቀሌ ውስጥ የግል ጋዜጣ አይገባም፡፡በትግራይ ህዝብ ላይ የእውቀት እቀባ አድርጋ ቆይታለች፡፡
 …
ይህም አማራጭን በመከልከል   በትግራይ  ህዝብ ዘንድ አልፋ እና ኦሜጋ ሆና እንድትታይ አድርጓታል፡፡ የእውነቱ መጋረጃ ግን እየተከፈተ ነው፡፡ ትህነግ ብቻዋን ቁሟ የትግራይን ህዝብም ብቻህን ቁም እያለች ነው፡፡ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡
..
ሃይል ያለው ፍትህ አለው 
ትህነግ የጠረጴዛ  ፖለቲካ ከልምድ መዝገቧ ውስጥ ፈፅሞ  የለም(Tplf not favor  the carrot, but the stick)፡፡በመሆኑም ወልቃይትም ሆነ ራያን በጠረጴዛ ፖለቲካ ተነጋግሮ መልስ ማግኘት ይከብዳል፡፡  አይናቸውን በጨው ታጥበው ከወልቃይት እስከ ራያ ከተዟዟሩ በኃላ፣ዶክተር ደብረፅዮን  በትግራይ ክልል ውስጥ አንድም የሚነሳ የማንነት ጥያቄ የለም ብለው ክደዋል፡፡ የሚጠበቅ ነው፡፡ በፖለቲካ ልቆ መገኘት ብቻ መፍትሄው ነው፡፡ ሃይል ያለው ፍትህ አለው የሚለው የማኬቬሊ ንግግር  ለትህነግ ፖለቲካ ይሰራል፡፡
 …
ፍትህ የሃይል ባሪያ ናት፡፡ሃይል በፖለቲካ ፣በኢኮኖሚ …መጎልበትን ይጠይቃል፡፡
Filed in: Amharic