>
2:20 am - Saturday December 10, 2022

ከአጥፍቶ ጠፊው ወንበዴ ህወሀት ራሳችንን እንጠብቅ!!! (ቹቹ አለባቸው)

ከአጥፍቶ ጠፊው ወንበዴ ህወሀት ራሳችንን እንጠብቅ!!!

 

ቹቹ አለባቸው

 

* የኛዎቹ ሰዎች በነጌታቸው አስፋ እንዲያ ሲሰቃዩ፤ ንጹሀን ሰዎችን ለመወንጀል ሲባል ብቻ እነ “አኬልዳማ”ና ሌሎች በርካታ የውሸት ዶክመንተሪ ፊልሞች ተዘጋጅተው፤ ተከሳሾቹ  ወደ ፍ/ቤት ከመቅረባቸው በፊት ለህዝብ ይፋ ሲሆን፤ ህወሀት የት ነበረች? ነው የአሁኖቹ ተረኞች ከወርቆቹ ዘር መሆኑ ነው? ብቻ በአጠቃላይ ህወሀት የፖለቲካ “ቅንጨራ”  እንደገጠማት ፍንትው አድርጎ አሳይቶባታል!

——

ያ በክፉ ቀን የተፈጠረ ድርጅት፤ ዛሬ ደግሞ ከመቸውም ጊዜ የባሰ አስጠሊታ መግለጫ አወጣ መባሉን ሰማሁ፡፡ ወሬው ቀኑን ሙሉ ሲሰራጭ የዋለ ቢሆንም፤አስተማማኝነቱን ለማረጋገጥ በሚል DW ስጠባበቅ ዋልኩ፤ይሄ የዜና አውታርም፤ዶ/ር ደብረፂወን የሰጠውን መግለጫ በደንብ አስተላለፈው፡፡  እኔም ከዛሬው የሕወሀት መግለጫዋ፤የሚከተሉትን አንኳር አንኳር ነጥቦች ተገነዘብኩ፡-

1.በአሁኑ ወቅት መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር፤ወንበዴዎችንና ዘራፊዎችን የማሰር እንቅስቃሴና አፈጻጸሙ ተቀባይነት የለውም ይላል፤

 

2.በአሁኑ ወቅት  ህግን በማስከበር ስም የሚካሄደው እንቅስቃሴ፤ በትግራይና  በህዝቧ ላይ ጫና ለመፍጠርና ትግራይን ለማጥቃት ታስቦ ና ታቅዶ የሚካሄድ እንቅስቃሴ ነው ይላል፤

3.ከበበባ (ወደ ትግራይ ሚወስዱትን መንገዶች መዝጋትና እህል ወደ ትግራይ አያልፍም መባሉ) እና ትግሬዎችን ማፈናቀሉ አሁንም ቀጥሏል ይላል፤

4.አሁን የሚካሄደው እንቅስቃሴ የውጭ  ሀይላት እጅ አለበት ( ኤርትራን መሆኑ አይቀርም) ወዘተ… የመሳሰሉ ባዝንኬዎች ናቸው፡፡

———/////——

እኔ  በበኩሌ፤ ከዛሬው  የህወሀት መግለጫ የተገነዘብኩት መሰረታዊ ነገር ቢኖር፤ ህወሀት ተስፋ ቆርጣለች፡፡ ልብ በሉ ዛሬ ህወሀት ቢያንስ ከ3 ዋና ዋና እና ግዙፍ ኋይላት ጋር ነው የተላተመችው፡- እንደ አጠቃላይ  ከኢትዮጵያ መንገህስትና ህዝብ ጋር፤ቀጥሎ ደግሞ በተለይም ደግሞ ከአማራ ህዝብ ጋር( ከበባና ማፈናቀል የምትለው ለአማራ መሆኗን ልብ ይሏል)፤ሌለው ደግሞ የውጭ ኋይል አለበት የተባለው  መከረኛው የኤርትራ መንግስት መሆኑ ነው፡፡ ታድያ  ጎበዝ! ተስፋ ያልቆረጠ ኋይል ካልሆነ በስተቀር ማን ነው ከነዚህ 3 ግዙፍ ኋይላት ጋር ለመላተም የሚወስነው? እውነትም ህወሀት ሲበዛ ተስፋ ቆርጣለች፡፡

———/////———-

የሕወሀት መግለጫ ፖለቲካና ህግ ተደባልቋል አይነት ክስም አለበት፡፡ፖለቲካና ህግ ምንና ምን ናቸው? የሚለውን ነገር ለጊዜው ልተወውና፤ እንዴት ነው የተደባለቁት? የሚለውን ነጥብ ግን መመልከት ይገባል፡፡ የህወሀት ሰዎች በካቴና ታስረው፤ ከነክብራቸው  ፍ/ቤት መቅረባቸው፤ በገመድ እየተጎተቱ ሳይሆን በምታምር ቢጫ ሄሊኮፕተር ተጭነው ወደ ፍ/ቤት መቅረባቸው፤ እንዲሁም ያ ምስላቸው በቴሌቪዥን መታየቱ እንዲህ ያበሳጫል እንዴ? እንደዛ ከሆነ ፤የኛዎቹ ሰዎች በነጌታቸው አስፋ እንዲያ ሲሰቃዩ፤ ንጹሀን ሰዎችን ለመወንጀል ሲባል ብቻ እነ “አኬልዳማ”ና ሌሎች በርካታ የውሸት ዶክመንተሪ ፊልሞች ተዘጋጅተው፤ ተከሳሾቹ  ወደ ፍ/ቤት ከመቅረባቸው በፊት ለህዝብ ይፋ ሲሆን፤ ህወሀት የት ነበረች? ነው ዛሬ የተደፈሩት ሰዎች የ”ወርቆቹ” ዘሮች ስለሆኑ ነው ይሄንን ያክል ጫጫታው?፡፡ ብቻ ዛሬ ህወሀት፤ ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁሟ ሞታለች፤ መግለጫው ህወሀት፤ ከባድ ሆነ የፖለቲካ ብሰለት ችግርና የፖለቲካ “ቅንጨራ”  እንደገጠማት ፍንተው አድርጎ አሳይቶባታል፡፡

——////———–

ከዛሬው የህወሀት መግለጫ ሌላም አንድ ነገር የተገነዘብኩ መሰለኝ፡፡ ይሄውም፤በሌሎች ክልሎች ወንጀል የፈጸሙ አካላትም ይጠየቁ፤ ከሜቴክ ውጭ ያሉ ድርጅቶችም ይፈተሸ ብለን ነበር፤ነገር ግን እስካሁን ባለው ሁኔታ ዕርምጃው ትግራይ ላይ ብቻ አትኩሯል፤ ይህ ደግሞ ፖለቲካዊ ይዘት ስላለው ነው የሚል ነው፡፡ በሌሎች ክልሎች ወንጀል የሰራ ባለስልጣን ካለ ይጠየቅ የሚለው ተገቢ ነው፡፡ ሁሉም መሰ/ቤቶች ይፈተሸ የሚለውም እንዲሁ፤እኛም አጥብቀን  የምንፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ህወት 27 አመታት ሙሉ ሲያመሰቃቅለው የኖረውን አገርና ተቋም፤ባንዴ መፈተሸና ማጥራት የሚቻል አይመስለኝም፤ የተጠያቂ ሰዎች ሁኔታም እንዲሁ፡፡ ለዚህም ነው መንግስት ደረጃ አውጥቶ ነገሩን ሁሉ በወግ በወጉ እሄደበት ያለው፡፡ ምን አልባት ግዙፉ ወንጀልና፤ሰፊው ስርቆት በህወሀት ሰዎች ዙሪያ ስለሆነ፤ ከሚታሰሩት  ወንበዴዎች መካከል  ህወሀታዊያን በዝተው ይሆናል፡፡ ከዚያ ውጭ መንግስት፤ የአማራና ኦሮሞን ሌባና ጨካኝ እየተወ ፤በትግራይና በህሀወት ሰዎች ላይ ብቻ የሚያነጣጥርበት አንዳች ምክንያት የለውም፤ እስካሁን ያለው አካሂያዱም ይህንን አያሳይም፤እኔ በግሌ  በተለይም ዶ/ር አብይ እንዲህ አይነቱን ወረደ አሰራር እንደማይከተል እተማመንበታለሁ፡፡

፡————-///—–

ለሁሉም  ዛሬ ህወሀት ያወጣችው መግለጫ፤ተስፋ መቁረጧንና ፤አጥፍቶ ወደ መጥፋት ደረጃ ለመሸጋገር የወሰነች ለመሆኑ ምልክት  አድርጌ ወስጀዋለሁ፡፡ አንዳንዴ የመጨረሻህ ሲደርስ እንዲህ ያደርግሀል፡፡ ስለሆነም፤ አሁን ከመንግሰትና ከኢትዮጵያ ህዝብ፤ በተለይም ከአማራ ህዝብ የሚጠበቀው አስቸኳይ ነገር፤ የህወሀትን ተስፋ መቁረጥና ተስፋ መቁረጡን ተከትሎ ሊከሰት ሚችለውን አደጋ ቀድሞ መገንዘብና፤ ለዚህ የሚመጥን  የቅድመ መከላከል እርምጃ  በህወሀት ላይ መውሰድ ነው፡፡ ካሁን በኋላ አንተን ሊያጠፋ የወሰነ የወንበዴ ኋይል መጣሁብህ እያለህ፤ ከወንድም /እህትህ ጋር በሆነ ባልሆነው ስትነታረክ የምትውል ነገር አይገቤ ካለህ/ካለሽ ይብለኝ ለራስህ/ለራስሽ፡፡

ስለሆነም፤በተቻለ መጠን ወደ ጦርነት የሚወስዱ ማናቸውንም መንገዶች ለማስቀረት መስራ አለብን፤ ከጦርነት ሁላችንም አንጠቀምም፡፡ ሆኖም ግን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ፤ የተቀናጀ፤ የተጠናከረ፤ ከበድ ያለ የህወሀትን ወገብ የሚሰብር፤ሰላማዊ  የትግል እርምጃዎችን መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄም ሲሆን፤ በተቻለ መጠን ትግላችን ህዝብን ሳይሆን፤ወንበዴ ህወሀትን ለይቶ እንዲያዳክም ለማድረግ እንሞክር፡፡ እነዚህን ሰላማዊ የትግል ስልቶች በቀጣይ እናቀርባለን፡፡እስከዛው ሁልህም በያለህበት ነገሮችን በንቃት ተከታተል፡፡

——–///———-

ብቻ! አሁን  መጨረሻው ሳይደርስ አልቀረም፡፡ መጨረሻው ሲደርስ ደግሞ፤ብዙ ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም፤በዚህ በኩል ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ፤ሁሉም በያለበት ነገሮችን በጥንቃቄ መከታተል አለበት፡፡ በተለይም ዋግ፤ ሰ/ወሎና ሰ/ጎንደር የመሳሰላችሁ ዞኖች፤እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል፤ ህወሀት በፖለቲካ ሰክራለች፤የሰከረ ሰው ደግሞ የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ ብቻ ህወሀት ሳያጠፋን፤ እኛ ቀድመን ቢያንስ ከበትረ-መንግስቱ እንዲነቀል ብናደረግው ሳይሻል አይቀርም፡፡ እመኑኝ፤ ህወሀት በዝች ምድር ላይ እስካለ ድረስ፤ኢትዮጵያ  እየፈረሰች የምታድር አገር ከመሆን አትድንም፤በተለይም አማራ ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝቶ ማደር አይችልም፡፡ ስለሆነም፤ኢትዮጵያም እየፈረሰች  እንዳታድር፤አማራም ሰላማዊ እንቅል ተኝቶ እንዲያድር የምትፈልጉ ሁሉ፤ ሕወሀትን እስከወዳኛው ለመሸነት ሙሉ አቅማችሁን አስተባብሩ፡፡

Filed in: Amharic