>

ካቴናኮ ቅንጦት ነው!!! (ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

ካቴናኮ ቅንጦት ነው!!!
ብርሀኑ ተክለአረጋይ
በተያዝንበት ወቅት ከ10 በላይ ከባቢዎቻችን መሀል አንድም የወታደር ልብስ የለበሰ ሰው አልነበረም የፍርድ ቤት ማዘዣማ አይታሰብም ሁሉም የተቀባበለ ማካሮቭ በእጃቸው ይዘዋል አንዱ ደግሞ ቪድዮ ካሜራ ይዟል የሁመራው ደህንነት ሀላፊ ተከስተና የጎንደሩ አሸናፊ 4ጎረምሶች ለመያዝ ጦርነት እንደሚመራ ሰው ትእዛዝ ይሰጣሉ ‘ተንበርከኩ!” ተባልን…
እውነቴን ነው ካቴና ቅንጦት ነው በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ሁሉ እጁ ላይ የሚጠልቅለት “ናማ ጠብቆብኛል አላላልኝ” ሲል ባለቁልፉ የሚያላላለት አለም አቀፍ ማሰሪያ ነው እውነት ለመናገር ዜጎች በጅምላ ሽብርተኛ በሚባሉበት ዘመን አዲስ አበባ ውስጥ ከተያዙ ጓዶች ውጪ ማንም ሰው በካቴና ታስሮ ወደ አዲስ አበባ አልመጣም እንደ ጥጃ በወፍራም ሲባጎ አልያም በወፍራም ሰንሰለት እጅና እግሩን በጨርቅ ደግሞ አይኑን ታስሮ እንጂ
በተለይም ሁመራ/ማይካድራ አካባቢ የተያዙ ሰዎች በየመንገዱ (ሁመራ-ጎንደር-ባህርዳር) በሚገኙ ድብቅ መደብደቢያዎች “እያረፉ” ስለሚመለሱ ጉዞአቸው ከዱላና ስቃይ ጋር ከ1 ወር በላይ ሊወስድ ይችላል በአብዛኛው ምርመራው በየመንገዱ አልቆ ነው ማእከላዊ የሚደርሱት የእወደድ ባይ ደህንነቶች ሰንሰለቱንና ሲባጎውን አጥብቆ ማሰር እጅና እግራቸውን እያሳበጠው በስቃይ አዲስ አበባ ማእከላዊ ይደርሳሉ ለዚያውም ያሉበት ቦታ ማእከላዊ መሆኑን የሚነግሯቸው ውስጥ ያሉ እስረኞች ናቸው አይናቸው ታስሮ ነዋ የመጡት
 በዚያ መንገድ ከተያዙ ጓዶች መሀል ቀላሉ የኔና የጓዶቼ ነው  የተያዝነው የካቲት 18/2007 ነው ማይ ካድራ ከተማ!!! በተያዝንበት ወቅት ከ10 በላይ ከባቢዎቻችን መሀል አንድም የወታደር ልብስ የለበሰ ሰው አልነበረም የፍርድ ቤት ማዘዣማ አይታሰብም ሁሉም የተቀባበለ ማካሮቭ በእጃቸው ይዘዋል አንዱ ደግሞ ቪድዮ ካሜራ ይዟል የሁመራው ደህንነት ሀላፊ ተከስተና የጎንደሩ አሸናፊ 4ጎረምሶች ለመያዝ ጦርነት እንደሚመራ ሰው ትእዛዝ ይሰጣሉ ተንበርከኩ!!! ተባልን አንገራገርን ጥፊና እርግጫ ተከተለ (በካሜራ እየቀረፁ ዱላ ፊልም ላይ ብቻ ይመስለኝ ነበር) ቁጭ በሉ ተባለ “ወደኋላ እሰሯቸው” በወፍራም ሲባጎ ታሰርን አሸናፊ ወደ ደሴ ካህሳይ እየጠቆመ “ይህንን እግሩን ጨምረህ እሰረው” አለ ታሰረ ቪድዮው ስራውን አላቆመም ይቀርፃል “አይናቸውን ሸፍኑ” ተባለ አይናችን በጨርቅ ታሰረ  ጉዞ ወደ ሁመራ ደህንነት ፅ/ቤት ሆነ በሙቀት በተቀቀለ የሲሚንቶ ወለል ላይ እንድንተኛ ተደረገ የነበረችው አንዲት ፍራሽ ነበረች ጓደኞቼ የወገብ ችግር ስላለበት እሱ ይተኛባት ብለው ለኔ ለቀቋትና ወለል ላይ እየተኙ እጃችን እንደታሰረ 2ቀን አደርን መገላበጥ ያስመታል ፍቅረ ማርያም ለምን ተገላበጥክ ተብሎ በጠባቂው ተደበደበ ጄሪ ለምን በሌሊት ነቃሽ ተብላ “ሻእቢያ ነፃ ሊያወጣሽ የመጣ መሰለሽ?”እና ሌሎችም ፀያፍ ስድቦች ተሰደበች ደሴ “ከባድ አሸባሪ”ተብሎ በሙቀት ክፍል ውስጥ ተቆለፈበት ከ2ቀን በኋላ በተመሳሳይ አይናችን ተሸፍኖ ወደ ጎንደር ተወሰድን ብሉኮ አካባቢ የምትገኝ ስውር እስር ቤትም እንዲሁ አይነት ነገር ለሌላ 2 ቀን ገጠመን አይንህን አላልተሀል ተብሎ እርግጫ (እጁን ወደኋላ የታሰረ ሰው እንዴት አይኑን እንደሚያላላ አስቡት)ከጎንደር በኋላ ወደ አዲስአበባ ስንመጣ     የደህንነቱን ቡድን የተቀላቀሉ አጃቢ የፌዴራል ፖሊሶች ሲባጎውን በካቴና ቢቀይሩልንም አይናችን ግን እስከ ማእከላዊ ግቢ አልተፈታም ነበር ይሁንና ከሲባጎ ካቴና መቶ እጥፍ የተሻለ ነበር ዛሬ ጄኔራል ክንፈ በደቂቃዎች ልዩነት በሄሊኮፕተር ተጉዞና በካቴና ታስሮ አዲስ አበባ ሲገባ ሳየው “ከስርቆቱ ውጪ”  ክንፈን መሆን ተመኘሁ ኧረ ወዳጆቼ ካቴናማ ቅንጦት ናት
Filed in: Amharic