>
6:09 am - Wednesday December 7, 2022

የኦ.ዴ.ፓና ኦነግ ከጉያቸው ውስጥ ተፈልቅቆ የተገኘ ምስጢራዊ ስትራቴጂክና ፖለቲካዊ  እቅዳቸው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የኦ.ዴ.ፓና ኦነግ ከጉያቸው ውስጥ ተፈልቅቆ የተገኘ ምስጢራዊ ስትራቴጂክና ፖለቲካዊ  እቅዳቸው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
መቼቱን በመካከለኛው ዘመንና በእንግሊዝ ስኮትላንድና አየርላንድ ያደረገውና  በስትራቴጂ ፣ ታክቲክና በአደገኛና መሰሪ ኮንስፓይሬሲ የታጀበው  የሰባቱ ኪንግዴም የስልጣን ፍልሚያ ሲያስኮመኩመን የከረመው ”  Game of Thrones ” ፊልም ላይ  የፖለቲካ ጠቢቦች ፣ መሳፍንቶች በህዝባቸው ላይ መፃኢ አደጋ መምጣቱ  የማይቀር መሆኑ ሲሸታቸው << Winter is coming! ”  የምትል ማስጠንቀቂያ እንደ ቢጫ  መብራት ተምሳሌታዊ ነገር ይናገራሉ ።
በኢትዮጵያ ፖለቲካም  በተለይ በአማራ ላይ ዊንተር  መምጣቱ እየሸተተኝ ስለመሰለኝ ለማስጠንቀቅ  ነው  ።ያውም እየመጣ ያለው  ዊንተር  Morment  ለቲሪዬን ላንስተር  ” So the oncoming Winter will probably  the longest  and hardest Winter in living memory.” በማለት እንዳስጠነቀቀው አይነት “ዊንተር ” ሳይሆን አይቀርም።
የODP /OLF  ስትራቴጂካዊ እቅድ!
…………
መሪ መመሪያ ~ “ብዙ ነን ሁሉም በልካችን” አስተሳሰብን  መተግበር ።
1 ) የሁለት majority አገራዊ አሠላለፍን በመቀየር  በአንድ የኦሮሞ   Majority ለመተካት  የአማራውን ሚና መቀነስ፡-
ሀ) ) ለዚህ  እቅድ ተፈፃሚነት ዋግን፡ አዊን ምናልባትም ቅማንትን ጨምሮ ክልል በማድረግ አማራ የሚባለው ክልል በቆዳ ስፋትም፡ በህዝብ ብዛትም እንዲቀንስ አድርጎ ከmajority ሚናው እንድወርድ ማድረግ ።
*ለ) ራስን ማስፋፋት ሌላውን ማሳነስ !፡፡ ለዚህ  እቅድ መሳካት ሚድያው በጋራ ተሠልፏል፡፡ በነገዱና በነአምባቸው ቡድን መካከል ልዩነትን በማስፋት ነጣጥሎ የመምታት እንቅስቃሴም ማድረግ።፡
2 ~ ስትራቴጅክ እቅድ
አማራውን ውጥረት ውስጥ በመክተት አላማን ማሳካት! 
ሀ) በክልሉ ውስጥ የክልላዊ ማንነት ጥያቄዎችን በሚድያ ሽፋን በማናር በዚሁ አጀንዳ እንዲወጠር ማድረግ፡፡
ለዚህ እቅድ ተግባራዊነት  አሁን ኢንሳ የነበረ ተስፋሁን ጎበዛይ የሚባል የአገው ተወላጅም የጠሚሩ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ተደርጓል፡፡ ከደቡብ ልምድ እነአገውን ክልል የማድረግ ጫና የመፍጠር ነው፡፡
 [ እዚህ ላይ አፋርን ኦሮሙማ የማድረግ ሂደትን ለማገዝና አማራውን የበለጠ ለመጨፍለቅ በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ከሚሴን  በአፋር አስተዳደር ስር ልዩ ዞን እንዲሆን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በአማራ ክልል ካርታ ደግሞ በ3ቱም ብሔረሰብ ዞኖች ዳርቻ ላይ የሚገኝ ነው፡፡
ለ) በADP መፍትሔ እንዲሠጠው የቀረበውን የሱዳን ድንበር ማዋሠን ጉዳይ ችላ በማለት በዚያ በኩል ያለው ውጥረት እንዲሠነብት የማድረግ ነገርም አለ።
ሐ~ ከላይ ባለው አሠራር መሠረት በደቡብ የአማርኛን ሚና በማጥፋት የኦሮምኛ ቋንቋን የፌደራል የሰራ ቋንቋ ማድረግ፡ በአዲስአበባ አፋር ሶማሊና ቤኒሻንጉል የኦሮምኛን ሚና ማሳደግ።
መ) በደቡብ ክልል መከፋፈል የክልሉ የጋራ ድምፅ ተፅዕኖ እንዲቀር የማድረጉን ያህል፡ አማራውንም በህዝብና ግዛት ማሳነስ።
3) ታዛዦችን በየክልሉ መሾም : – በሶማሌ ፡ በጋምቤላ ፡በአፋር ቀጥሎም በቤንሻንጉል የክልሉ ህዝብና ምክርቤት ሳይሆን ጠሚሩ ፅ/ቤት እየተጠሩ አመራር መቀየር!
4)  የግዛት መስፋፋትና ቁጥጥር ፡- 
ሀ) መሪ ቃል “የኛ ነው”!  “ኬኛ  !”
አዲስአበባ የኛ ነው የሚለውን በመግለጫ ከተባለው በላይ በተግባር ታከለ ኡማ የኦሮሞ ከተማ እያደረገ ነው፡፡ ሐረርና ድሬዳዋም የኛ ነው ውጡ የሚል ጫና አለ፡፡ (የስራ ቋንቋው ኦሮምኛ ነው)
5) ሲዳማ ክልል 
ሲዳማ ክልል እንዲሆን የተፈለገው በቋንቋ መቀራረብ ብቻ ሳይሆን ሃዋሳን ጨምሮ የኦሮሞን ይዞታና ተፅዕኖ ማሳደግ ነው፡፡ የአሁኑ ደቡብ ክልል አማርኛ የስራ ቋንቋው ቢሆንም ከዚህ በኻላ ይቀራል፡፡ የክልሉ መከፋፈልም የጋራ ተፅዕኖ እንዲቀር ያስችላል፡፡
* ቤኒሻንጉል ኦሮምኛ 2ኛ ቋንቋ እንዲሆን እቅድ አለ፡፡ ሶማሊና አፋርም ተመሳሳይ እቅድ አለ፡፡
*  ከላይ ባለው አሠራር መሠረት በደቡብ የአማርኛን ሚና በማጥፋት የኦሮምኛ ቋንቋን የፌደራል የሰራ ቋንቋ ማድረግ፡ በአዲስአበባ አፋር ሶማሊና ቤኒሻንጉል  ደሞ የኦሮምኛን ሚና ማሳደግ።
ቀጣይ ክፍል ይኖረዋል……
Filed in: Amharic