>
9:56 am - Monday August 15, 2022

እናንት አባት አስለቃሾች     እንኳን ደስ ያላችሁ።   (ዘመድኩን በቀለ)

እናንት አባት አስለቃሾች 
   እንኳን ደስ ያላችሁ። 
 ዘመድኩን በቀለ
 
★ አብሮ ከማልቀስ ውጪ ምንአደርጋለሁ? ምንም? ምንም ማድረግ አልችልም። በዚህ ደግሞ የባሰ አዝናለሁ። 
 
★ የወንድ ልጅ እንባ እሳት ነው። ያውም የአባት፣ የሽማግሌ፣ የአረጋዊ እንባ እሳት ነው። 
•••
አረጋዊ አባትን ማስለቀስ በ666 ሃይማኖት አላውቅም እንጂ በክርስትና ግፍ ነው። በደል ኃጢአት ነው። በእስልምናም ሃራም ነው። አባት ሽማግሌ ይጦሩታል እንጂ አያስለቅሱትም። ወዴት ልግባ ወዴት ልሂድ እስኪል ድረስ አያስለቅሱት።
•••
ብዙዎች እንዲነሳ ባይፈልጉም እውነታው ግን ይኸው ነው። አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥራት ተግባር ነው። የዘር ማጥራት። ዐማራ፣ ጉራጌና ደቡብን ከማዕከላዊው መንግሥት መቀመጫ ከአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ዙሪያ የማጥራት ሥራ ነው እየተካሄደ ያለው። እደግመዋለሁ የዘር ማጥራት ነው። የሃይማኖት መልክ ጭምርም አለው የዘር ማጥራት ተግባሩ።
•••
ቪድዮውን እያለቀሳችሁ ተመልከቱት። ወንድ ልጅ ሲያለቅስ ተመልከቱት። ልቅሶ በተፈጥሮው የማያውቀው አባት ሲያለቅስ ተመልከቱት። ተመልከቱትና ፍረዱ። ወዳጄ አባት እኮ ጌጥ ነው። አባት ሞገስ ነው። አባት የቤት ምሰሶና ማገር ነው። አባት እኮ የሰፈር፣ የመንደር፣ የሀገር አድባር ነው። አባት የሀገር ዋርካ ነው። አባት ገበና ሸፋኝ ነው። አባት መመኪያና መኩሪያ ነው። አባት አስታራቂ ሽማግሌ ነው። አባት መራቂ ነው።
•••
ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ አባት አለው። ምንም እንኳ በፓርላማ ንግግሩ የሴቶችን ቀልብ ለመስረቅ የአባቱን ስም ባያነሳም ግን አቶ አህመድ የሚባሉ አባት አሉት። የእሱ አባት እንዲህ ሲያለቅሱ ቢያይ ምን ይሰማው ይሆን? የለማ አባት ኦቦ መገርሳ? የአዲሱ አባት ኦቦ አረጋ እንዲህ የሚያስለቅሳቸው ቢኖር ምን ይሰማቸው ይሆን? ሰው ናቸው የአባታቸውን ልቅሶ አይፈልጉም። ዲቃላዋ ብአዴን ግን አባትም እናትም ስለሌላት ደንታዋ አይደለም። ሌሎቹን ነው ያልኩት።
•••
“ በስማችን እንለያለን፣ በአነጋገራችን እንለያለን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የትም ቦታ ተዘዋውረን መሥራት አልቻልንም” እያሉ ነው የሚያለቅሱት እኚህ አባት። ህውሓት ዐማራውን በሁሉም ብሔር ብሔረሰብ እንዲጠላ ያደረገችው ሥራ እነሆ ፍሬ ያፈራላት ይመስላል። ብድራቱን ታቦተ ጽዮን ትክፈላቸው።
•••
በተፈጥሮዬ የማላውቀው ሰው ሞቶ ሊቀብሩ የሚሄዱ ለቀስተኞች ቢገጥመኝ እንኳ በልቅሶው ላይ ሺ ሴቶች ሲያለቅሱ ባይ ከማዘን ውጪ እንባዬ አይመጣልኝም። ወንድ ልጅ ሲያለቅስ ካየሁ ግን ከምር ጉዳዩን ባላውቀው እንኳ እናቱ እንደሞተችበት ህጻን አብሮ ያስለቅሰኛል። አዎ ወንድ ልጅ አያልቅስ። ያውም ሁለት ፀጉር ያበቀለ ወንድ ልጅ አያልቅስ። አባት አያልቅስ። አይጨነቅ። አያንከራተት።
•••
ኦህዴድ፣ ኦነግ፣ ህውሓት ሆይ እንኳን ደስስ አላችሁ። እንደምትመኙት ያው ዐማራው አቅም አጥቶ ወንድ ልጅ እጅ እግሩን ተጠፍንጎ ወገን ዘመድ፣ ተቆርቋሪ አጥቶ አረጋዊ ሽማግሌ ቆሞ አለቀሰላችሁ። ደስስ ይበላችሁ ልጡ የተራሰ፣ መቃብሩ የተማሰ ለሞት የቀረበ ሽማግሌ መውደቂያ አሳጥታችሁ፣ ጎጆውን አፍርሳችሁ አስለቀሳችሁ። ደስስ ይበላችሁ። ያ እንዲሞት፣ እንዲጠፋ የምትመኙለት ዐማራ መድረሻ አጣላችሁ ደስስ ይበላችሁ። ተዝናኑ በቪድዮው። ውስኪ ክፈቱ፣ ቢራ ተራጩ። ደስስ ይበላችሁ። ደስ ይበላችሁ አቅመ ደካማ ዐማራ አስለቀሳችሁ። እንባ አውጥቶ እየዬ አለላችሁ። ደስስ ይበላችሁ።
•••
ታዲያ ይሄንን ከቄሮ ጋር እዩት። ከአባ ገዳዎች ጋር እዩት። የድል ውጤታችሁን ሰብሰብ ብላችሁ እዩት። የምኒሊክ ሰፋሪ መድረሻ ሲያጣ፣ በቁሙ በስተእርጅና ሲያለቅስ ሰብሰብ ብላችሁ እዩት። ለልጆቻችሁም አሳዩ። ግዳይ የጣላችሁትን አሳዩት። አሳዩዋቸው ዐማራ እንዴት እንደሚያለቅስ። በስተእርጅና እንዴት እንደሚንከራተት አሳዩዋቸው። እንኳን ደስስ አላችሁ።
•••
እግዚአብሔር ግን ያያል። ከላይ ከዙፋኑ ያያል። ይመለከታልም። እግዚአብሔር ያያል አልኳችሁ። ዝም አይልም። ሙሴን ያስነሳል። ነፃ አውጪ ሙሴን ያስነሳል። ባህሩን ከፍሎ የሚያሻግር ሙሴን ያስነሳል። ያስነሳል እግዚአብሔር። ፍርድም ይሰጣል። የሽማግሌ ምርቃቱ እንጂ እንባው እሳት ነው። መከራ ነው። መዓት ነው የሚጠራው።
•••
1 ሚልየን የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተቀብላ ዜግነት ሰጥታ ልታኖር በይፋ ያወጀች ሀገር። ሀገር ፈጣሪውን ዐማራ፣ ሀገር ጠባቂውን ዐማራ እንዲህ ማስለቀስ ዋጋ ያስከፍላል። የዐማራ ሚስት አቅፈው እየተኙ፣ ከዐማራ ሴት ተወልደው ሲያበቁ። እነሱም ከዐማራ ሴት ወልደው ሲያበቁ የልጆቻቸውን አያት፣ የሚስቶቻቸውንና የእናቶቻቸውን አባቶች እንዲህ ደም እንባ ማስለቀስ ዋጋ ያስከፍላል።
•••
አይዞኝ አባቴ። አይዞኝ አባትዓለም። ይሄ እንደ ክረምት ፈሳሽ የሚያልፍ ጊዜ ነው። ለዐማራው ጥቂት የመከራ ጊዜ አለበት። ከዚህ የከፋ ጊዜም በዐማራና በኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ይመጣ ዘንድ ይነገራል። እናም አይዞኝ። እንባዎትን ፈጣሪ ይቀበልዎት። ፈጣሪ ይስማዎት።
•••
አስለቃሾች እደግመዋለሁ እግዚአብሔር ይፍረድ። አሁን እንዲህ የሚያለቅሰው ከሌላ ብሔር ቢሆን ኖሮ ሀገር ምድሩ በፕሮፓጋንዳ ይደበላለቅ ነበር። ግን ምንያደርጋል። አልቃሹ ከላይም ከታችም ወኪል የሌለው ምስኪኑ ዐማራው ነው። ብአዴን ሆይ በድን ያድርግህ። የእነዚህ አረጋውያን እንባ እንጦረጦስ ያውርድህ።
•••
የህወሓት መታወቂያ አሁን በግልጽ እየሠራ ነው። አነጋገርህ ይታያል። መታወቂያህ ይታያል። እናም ኦሮምኛ ካልቻልክ ሀገር የለህም። በተለይ ዐማራ ከሆንክ ሀገር የለህም። ይህ የግፍጽዋ ሞልቶ የፈሰሰ እንደሆን ግን መቆሚያም የለውም። ተናግሬያለሁ አስቡበት።
ሻሎም !   ሰላም  ! 
የካቲት 16/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic