>
5:20 pm - Tuesday May 17, 2022

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ስላስጠለፋቸው ተማሪዎች እንቅጩን ተናገረ!!! (አምሳሉ ገ/ኪዳን)

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ስላስጠለፋቸው ተማሪዎች እንቅጩን ተናገረ!!!

 

 

አምሳሉ ገ/ኪዳን
* የተከበሩ ዐቢይ ሆይ! በዚህ በሚመለከቱት ፎቶ የሚታዩ ታጋቾች በማን እጅ ያሉ ይመስልዎታል???
 
የወያኔው ምንደኛ ዐቢይ አሕመድ ዛሬ “በፓርላማው” ቀርቦ በአጋር ኃይላቸው ኦነግ ስላስጠለፋቸው ተማሪዎች ሲናገር የሚከተለውን ብሏል፦
ተማሪዎችን የጠለፍኩ እኔ ነኝ ብሎ ኃላፊነትን የወሰደ የተደራጀ ቡድን የለም!” አለ፡፡ ይሄንን አንድ በሉልኝ፡፡
ቀጠለና የት? እነማን? ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ ባልሰጠ መልኩ ድፍን አድርጎ “ተጠለፉ ከተባሉ ተማሪዎች ከፊሎቹ ሌላ እንዳሉ ብንሰማም፣ መረጃ ቢደርሰንም በሰዓቱ እንዲህ ብለን መልስ መስጠት አልፈለግንም ነበር!” አለ፡፡ ይሄንን ሁለት በሉልኝ፡፡
ቀጠለና ደግሞ “ተጠለፉ የተባሉ ተማሪዎችን ለማግኘት ተጠለፉ የተባሉበትን ቦታ ሁሉ በሠራዊታችን ብናስስም ልናገኛቸው አልቻንም ወይም የሉም፡፡ ደረሰባቸው ከተባለው ጉዳት ጋርም ልናገኛቸው አልቻልንም!” አለ፡፡ ይሄንን ሦስት በሉ፡፡
ስለዚህ  ዐቢይ ሊነግረን የፈለገው ድምዳሜው “ተማሪዎቹ በኦነግ ሸኔ እጅ አይደሉም፡፡ የጠለፋቸውም እሱ አይደለም!” የሚል ነው!!!
የተከበሩ ዐቢይ ሆይ! በዚህ በሚመለከቱት ፎቶ የሚታዩ ታጋቾች በማን እጅ ያሉ ይመስልዎታል???
ንጉሡ ጥላሁን “አስለቅቀን ወደ ዩኒቨርሲቲው መልሰናቸዋል!” ያላቸው ታዲያ እነማንን ነው???
በተጨማሪም “ተማሪዎችን የጠለፍናቸው እኛ ቄሮዎች ነን ባሕርዳር የታገቱ የኦሮሞ ተማሪዎች እስካልተለቀቁ ድረስ አንለቃቸውም!” ብሎ ለኢሳት የስልክ ቃለምልልስ በመስጠት ተማሪዎቹን መጥለፉን የተናገረውና ኃላፊነቱን ወስዶ ያስታወቀው ቡድን የ….. ልጅ ነው ወይ???
የኔ ድምዳሜ፦ አገዛዙ ተማሪዎቹን አስገድሏቸዋል!!! ተማሪዎችን ጠልፎ ለኦነግ ያሻገራቸው አገዛዙ ያጀራጀው ቡድን ነው፡፡ የአማራ ተማሪዎችን የመጥለፍ ሐሳቡ ሙሉ ለሙሉ የአገዛዙ ነው፡፡ ከማል ገልቹ እንደተናገረው አገዛዙና የኦነግ ሠራዊት በድብቅ አብረው የሚሠሩ በመሆናቸው አገዛዙ ተማሪዎቹን ለኦነግ አሳልፎ ሰጣቸውና አግቷቸው እንዲቆይ አድርጓል፡፡ ኦነግ “ግደል!” ሲባልም የአለቃ ትዕዛዝ ሆኖበት ገሏቸዋል፡፡ አገዛዙም በመንተፍረቱ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ ከኦነግ ጋር ውጊያ የገጠመ መስሎ ሰሞኑን ተውኗል!!!
የአማራ ተማሪዎች መጠለፍ መገደል ዓላማም በጥቃቱ የአማራን ቅስም መስበር፣ አንገቱን ማስደፋት፣ አማራን ማኅበራዊ እረፍት መንሳት፣ የአማራን ተማሪዎች ኢላማ በማድረግ ተማሪዎቹ ተረጋግተው እንዳይማሩና የትምህርት ዘመናቸውን በጭንቀት የተሞላ በማድረግ ብዙዎቹን ከትምህርት ገበታቸው ማፈናቀል የማይፈነቅሉትንና ችግሩን ተቋቁመው መማር የሚፈልጉትን ደግሞ በሚገጥማቸው ፈተና ችግር አሳር ተፎካካሪ እንዳይሆኑ ወይም ውጤታቸው እንዲያሽቆለቁል በማድረግ አማራ ብቁና የተማረ የሰው ኃይል እንዳያገኝ እንዳያወጣ ማድረግ ነው!!!
ዐቢይ ዛሬ ከተናገረው ልብ ብላቹህ ከሆነ “ተጠለፉ የተባሉ ተማሪዎችን ለማግኘት በሠራዊታችን ተጠለፉ የተባሉበትን ቦታ ሁሉ አስሰን ልናገኛቸው አልቻንም ወይም የሉም፡፡ ደረሰባቸው ከተባለው ጉዳት ጋርም ልናገኛቸው አልቻልንም!” ሲል የተናገረው አዲስ መረጃ ነው፡፡ እስከአሁን የነበረው መረጃ የተወሰኑ ተማሪዎች በኦነግ ሸኔ እጅ ኦነግ ሸኔ ባለበት ስፍራ መኖራቸውን ነው እንጅ ሠራዊቱ ሁሉንም ስፍራ እንዳሰሰና ተማሪዎቹ እንደታጡ የተነገረ መረጃ አልነበረም፡፡ የዚህ አዲስ መረጃ ትርጉምም “እርማቹህን አውጡ!” የሚል ነው!!!
ይሄ “የአማራ ተማሪዎችን በመጥለፍ አማራን ከላይ ለገለጥኳቸው ዕኩይ ዓላማዎች ማጥቃት!” የኦነግ ሐሳብ ቢሆን ኖሮ ከተማሪዎቹ ይልቅ እዚያው ቦታ በርካታ የአማራ ገበሬዎችና የከተማ ነዋሪዎች ነበሩለት!!!
ሲቀጥል ኦነግ ሸኔ ተማሪዎችን ጠልፎ በመግደል በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአሸባሪነት ተፈርጆ የፖለቲካ ኪሳራ እንዲደርስበት ይፈልጋል ተብሎ አይታሰብም!!!
ለምን ይመስላቹሃል የኦነግ ሠራዊት እዚሁ ሀገር ውስጥ ቁጭ ብሎ ከባንክ ዘረፋ ዜጎችን በየስፍራው እስከመግደል ድረስ የደረሰ የሽብር ተግባር እየፈጸመ አገዛዙ እርምጃ ወስዶ መደምሰስ ሲኖርበት ይሄንን ማድረግ ያልፈለገውና የማያደርገው ለምን ይመስላቹሃል??? ይሄው አሁን በአማራ ተማሪዎች ላይ እንደፈጸመው ሁሉ በኦነግ እያሳበበና ኦነግን እያዘዘ መግደል የሚፈልገውን ለመግደል፣ ማፈናቀል የሚፈልገውን ለማፈናቀል፣ ማሸበር የሚፈለገውን ለማሸበር እንዲያስችለው ነው ሌላ አይደለም!!!
ይሄ የአማራ ተማሪዎችን የማስጠቃት፣ የማስጠለፍና የማስገደል ኦፕሬሽን እንዲሁ በዘፈቀደ የተፈጸመ እንዳይመስላቹህ፡፡ እያንዳንዷ ነገር ከነ እርስበእርሱ ከሚጋጨው መረጃቸው ጭምር ሆን ተብሎ በሚገባ ተቀናብሮ የተፈጸመ የጥፋት የሽብር ኦፕሬሽን ነው!!!
ታስታውሱ እንደሆነ ይሄንን ኦፕሬሽን ለመውሰድ ሲያስቡ መጀመሪያ ያደረጉት ሆን ተብሎ የተቀናበረ ሴራ መሆኑ በግልጽ ሊታይ በሚችል ደረጃ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የደቡብና የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎችን በኳስ ጨዋታ ጉዳይ አጋጭተው ሁለት የኦሮሞ ተማሪዎችን እንዲገደሉ በማድረግ የግጭቱ ምክንያትና ማን ከማን የሚለው ሳይገለጥ በአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎችና በጽንፈኞች የብዙኃን መገናኛዎች በሙሉ ከሚገባው በላይ ተራግቦ እንዲዘገብ አደረጉ!!!
ለወትሮው የአማራ ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲው በዘግናኝ ሁኔታ ሲገደሉ በእነኝህ የአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎች አንዱም ተዘግቦ አያውቅም፡፡ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አማራ በየስፍራው እንደጉድ በግፍ የትም ሲገደልና ሲፈናቀል እነኝህ የአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎች ዘገባ ሠርተው አያውቁም!!!
ለምን ይመስላቹሃል ታዲያ ለአማራ መበደል ግፍና ሰቆቃ ጆሮ የማይሰጡ የአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎች ያንን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ግድያ የፀቡን ምክንያት ሳይጠቅሱ ኦሮሚያ በሚሉት የሀገራችን ክፍል ባሉ የአማራ ተማሪዎች የአጸፋ እርምጃ እንዲወሰድ በሚገፋፋ መልኩ ብቻ “ተማሪዎች ተገደሉ!” እያሉ አራግበው የዘገቡት??? ምክንያቱ ኦፕሬሽኑ በደንብ የተጠናና የተቀናበረ ስለነበረ ነው!!!
በሰዓቱ አገዛዙ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል የአማራ ተማሪዎች ላይ ጥቃት ሊያስፈጽም አስቦ ያንን እንዳደረገ በመግለጥ በዚያ አካባቢ ያሉ የአማራ ተማሪዎች የዘንድሮው ትምህርት ቀርቶባቸው ዊዝድሮዋል እየሞሉ ፈጥነው እንዲመለሱ አስጠንቅቄ ነበር፡፡ ያልኩት አልቀረም ይሄው የምታዩት ሁሉ ሆነ!!!
እናም ፈጣሪ ውሸት ያድርገው እንጅ የኔ ግምት “ልጆቹን ገለዋቸዋል!” የሚል ነው!!! ሊያቀርቧቸውና ከቤተሰብ ጋር ሊያገናኟቸው ያልቻሉበት ምክንያት ይሄው ነው ሌላ አይደለም፡፡ ይሄው  ዐቢይም በኦነግ እጅ እንደሌሉ አረጋገጠልህ፡፡ ስለሆነም ተገለዋል፡፡ የልጆችህን ደም መመለስ የምትፈልግ ጀግና አማራ ካለህ የልጆችህን ደም የምትመልሰው እያስበላንና በነፍስ በሥጋችን እየቀለደብን ያለውን የብአዴንን ባለሥልጣናት በፊት ለፊት በማውገዝና በመጋፈጥ ነው። ይሄ ሁሉ ግፍ ሰቆቃና ጥቃትም አማራ “በቃ!” ብሎ እስኪነሣ ድረስ ገና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መታወቅ አለበት።
Filed in: Amharic