>
4:38 pm - Thursday December 2, 8624

በምርምርና በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓት ስልጣን እድሜ ማስረዘሚያ እና የትኩሳት መለኪያው 'ጀኔራል?' ጆቤ

Jobe TPLFምንሊክ ሳልሳዊ:- ጆቤ በአሁኑ ወቅት ይዘውት እየተራመዱት የሚገኘው አስተሳሰብ ሕወሓትም በማዘናጊያ አጀንዳነት እያራገባቸው ነው::ወደ ሚዲያው እንዲወጡ የተደረገው የቀድሞ የወያኔ አየር ሃይል አዛዥ ከተንበርካኪው ቡድን ወገን እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታጋይ አበበ ተክለሃይማኖት በሽምቅ ተዋጊነት የጄኔራልነት ማእረግ አግኝተው አየር ሃይል እንደ ፋንታ በላይ ባይመሩትም ገለውት ነበር::ሰሞኑን በወያኔ መንግስት እየተደጎሙ በሚኖሩት አዲስ አድማስ እና ሪፖርተር ጋዜጣ እዩኝ እዩኝ ያበዙት አበበ ተክለሃይማኖት አንድም ትኩሳት መለኪያ ሌላም ሕወሓት እድሜዋ እንዲረዝም እንደ መሽረፈት ሲሆኑ ጎን ለጎን ወደ ስልጣ እየተጠጋጉ መሆኑን ጽሁፎቻቸው ያሳብቃሉ::ሕወሓት በስልጣን እንዲቆይ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የተሻለ አምባገነንነት እንዲፈጠር እየሰሩ ሲሆን የትግል አጋሮቻቸውን የተቹ መምሰሉ የሕወሓት የማዘናጊያ እና የማደናበሪያ አንዱ ስትራተጂ መሆኑን ልንነቃ ይገባል::

በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አድማስ እንዲተነፍሱ የተደረጉት ጆቤ በሶማሊያ የሞቱ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በተመለከተ የክብር መቃብር ጥያቄን አስመልክቶ በሰጡት መልስ ላይ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እያለ ራሱን የሚጠራው ጦር የሚተዳደረው በሽምቅ ተዋጊነት መመሪያ ደንብ በሆነ በጫካ ሕግ መሆኑና ወታደራዊ ሳይንስ ቀመስ ሆኖ ለሀገር የተገነባ ሰራዊት ባለመኖሩ የሞቱ ወታደሮች እንደ ሽምቅ ተዋጊ ወንበዴ ክብረቢስ ሆነው በሜዳ እንዲጣሉ እና ማስታወሻ እንዳይኖራቸው መደርጉ ከትጥቅ ትግል ጋር ተያይዞ የመጣ ልምድ እደሆነ ነግረውናል::የወታደራዊ ሳይንስ ስላለእላቸው የአንድ ሃገር ሰራዊት እና የሽምቅ ተዋጊ ወንበዴዎች ሰራዊት ልዩነቱን እንዳያውቁ እያወቁ ወንጀል በመስራት ላይ ናቸው::ጆቤ ከስልጣን ባይባረሩ ኖሮ የዚህ የግፍ አመራር አንዱ አካል እንደሚሆኑም መዘንጋት የለብንም ከመጀመሪያም በቦታው ላይ በነበሩ ሰአት ወታደራዊ ሳይንስን ሳይሆን ውንብድናን በሰራዊቱና ደህንነቱ ውስጥ ሲያሰራጩ እንደነበር ባይዘነጋም በአሁኑ ወቅት ይዘውት እየተራመዱት የሚገኘው አስተሳሰብ ሕወሓትም በማዘናጊያ አጀንዳነት እያራገባቸው ነው::

ጆበ ስለ አሰብ ጉዳይ ዘግይተው እንደነቁ ሊነግሩን ይፈልጋሉ::በሻእቢያ እና ወያኔ መካከል ውጥረት መኖሩን ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች መከላከያ ሰራዊያችን አሰብን ማስመለስ አለበት ብለው ሲደነፉ እንደነበረው ሁሉ የጆቤም አስተሳሰብ ይህ ነው::ጆቤ እንዲያጦዙት በሩ ተከፍቶላቸው የሕወሓትን የማዘናጊያ የአሰብ ወደብ አጀንዳ አራግበውታል::ስለ አሰብ የባነንኩት ዘግይቼ ነው ቢሉም እነዶክተር ያቆብ በተናገሩበት ወቅት ለምን ሰከን ብሎ የማሰብ እድሉን ለራሳቸው እንዳልሰጡት ግን አልነገሩንም:: የአስተሳሰብ መቀየር መዳበር መብሰል እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ አሰብ የሚያነሱ ግለሰቦችን ወደ እስር ከሚልኩ ሰዎች ጆበእ አንዱ የነበሩ ሲሆን ዛሬኤ ላይ ከአባት ፓርቲያቸው ሕወሓት ካድሬዎች ጋር ሆነው ራሳቸው ፈርመው ያስረከቡትን አሰብን እየተመኙ ይገኛሉ::

ምንሊክ ሳልሳዊ በመድበለ ፓርቲ ሲስተም ውስጥ መግባት ስለማይችል እና የ97 አይነት ሽንፈት እንደሚከናነብ ስለሚያውቁ ሕወሓትን እየደከመ የሚገኘውን እስትንፋሱን ለመቀጠል በሚደረገው ሩጫ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት አበበ ተክለሃይማኖት ያለምክንያት በዚህ ቀውጢ ሰአት ላይ የሕወሓት እምባ ጠባቂ የፖለቲካ ተንታኝ ሆነው እያላዘኑ ይገኛሉ::ታጋይ አበበ የሚነግሩን ነገር እና ያስተላለፉት መልእክት ሁሉ የምናውቀው እና ድምጻችንን እያሰማን እየታገልንለት የምንገኘው ጉዳይ ነው ምንም አዲስ ነገር አልነገሩንም::ለሕዝብ ልጆች ሲባል ሕወሓት ስልጣኑን ይልቀቅ ቢሉ አሊያም ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ቢሉ የተሻለ አማራጭ ነበር::ይህንን አላሉም ሕገመንግስቱ በተግባር ላይ ይዋል ማለት በሌላ አነጋገር የወያኔ የፖለቲካ ፕሮግራም በተሻለ አምባገነናዊ ዘዴ ይከሰት ማለት ነው::መጀመሪያ ሕገመንግስቱ በኢሕ አዴግ እና አባሎቹ ተረቆ የጸደቀ የፖለቲካ ፕሮግራም ግልባጭ እንጂ ሕዝብ የወከላቸው ልጆቹ ያጸደቁት ሕገመንግስት ስላልሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምም የፈየደው ነገር የለም::

ኤርትራ እና ኤርትራ ውስጥ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ታጋዮች እደ እርኩስ መንፈስ አይቶ እንዲደመሰሱ መመኘት ሌላኛው የታጋይ አበበ እብደት ነው::ለኤርትራ ጉዳይ ተጠያቂው ሕወሓትና ሕወሓት ብቻ ነው::ከተጠያቂዎቹም አንዱ ራሳቸው ታጋይ አበበ ናቸው::ኤርትራ ሉእላዊ መንግስት ናት ብለው ለተመድ ፈርመው ያመኑ ራሳቸው ሕወሓቶች ናቸው::እስኪ ፈርመው ባመኑበት እጃቸው ቃታ ስበው የኢሳያስን መንግስት ያውርዱና ይሞክሩ::ጉራ ብቻ ፋይዳ የለውም በደቂቃዎች ውስጥ መጥፊያቸው መሆኑን ያውቁታል::ኢሳያስ በሃይል ይውረድ የምትለው የ2016 የሕወሓት የማዘናጊያ ዜማ መሆኗን ራሳቸው ተንቅቀው እያወቁ ትኩሳት ለመለካት መሮጥ ራሳቸውን ለትኩሳት ዳርጓቸውል::

ሌላው ክዚህ ጋር የሚያያዘው በኤርትራ ያሉት ኢዮጵያውያን ታጋዮች ሲሆኑ ወደ ትጥቅ ትግሉ የሄዱት በወያነእ ተገፍተው የነጻነት ምሕዳር የለውጥ ጥያቄ የፖለቲካ ምሕዳሮች ስሌተዘጋጉ በሰላማዊ መንገድ መታገል ስላልቻሉ ነው::መፍትሄውን ክመሻት በጋራ እንደ ኢትዮጵያዊ አቀራርቦ የፖለቲካ መስመር ከማሲያዝ ይልቅ ኤርትራን በአፍራሽነት መፈረጅ በኤርትራ የሚገኙ ሃገር ወዳዶችን ከመዝለፍ አይለይም::ሌሎች በሃገራቸው ጉዳይ አያገባቸውም አይነት አመለካከት ጋር እየተላተሙ የሚገኙት ታጋይ አበበ ሊያውቁት የሚገባው ወያኔ ስልጣኑን ለሕዝብ እስካላስረከበ ድረስ እንዲሁም በጫካ ሕግ ሕዝብም ማአስተዳደር እስካላቆመ ድረስ ትግሉ እየቀጠለ ይሄዳል::የወያነ አምባገነንነት ሕዝቡን አንድ እያደረገው እንጂ እየለያየው አይሄድም ማለያየት ባለፉት 25 አመታት በወያኔ ተሞክሮ አልተሳካለትm ታጋይ አበበ የሕወሓቱ ጄኔራት ልፋታቸው በዳበረ ሃሳብ ሽፋን የሕወሓትን እስትንፋስ ለማስቀጠል እና የፖለቲካ ጥኩሳቱን ለመለካት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አንዱ የስትራቴጂ መንገድ መሆኑን ሁላችንም እንረዳዋለን::

Filed in: Amharic