>
5:13 pm - Thursday April 20, 2682

"የፈራ ይመለስ" የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አዲስ መፅሀፍ ከዝዋይ እስር ቤት

የፈራ ይመለስ Journalist Temesgen Desalegn from prisonታሪኩ ደሳለኝ

“የፈራ ይመለስ” ዛሬ ነሐሴ 10/08 ዓ.ም በገበያ ላይ ዉሏል። ይህ መፅሀፍ በ5 ክፍሎችና በ23 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን ለያንዳንዱ ክፍሎች ያራሳቸው መግለጫ ወይም ማሰሪያ ግጥሞች አሏቸው ።

ሀገር ለመታደግ
የአንድነትን ጎጆ ዳግም ለመቀለስ
“ያልተንበረከኩትን”
አንበርክኮ ለመመለስ
ዘረኛውን ሥርዓት
በሀይል ለመገርሰስ
የጀገነ ትውልድ
ጎዳናው ላይ ይፍሰስ
ግና
አምፆ ከመሞት የቀለለው ማልቀስ
ጥሪው ለሱ አይደለም
ከሠልፉ አይድረስ
ቀድመን ተናግረናል
የፈራ ይመለስ!!!
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
(ከዝዋይ እስር ቤት)

 

Filed in: Amharic