>
2:58 am - Tuesday May 24, 2022

የዘ-ህወሀት ተራ ቅጥፈት እና የማወናበጃ መረጃ የማዛባት ዘመቻ፣ [ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም - ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ]

Deception 2“TPLF” በሚለው የእንግሊዝኛው አህጽሮ ቃል ውስጥ የሚገኙት እና “LF” ተብለው የተጻፉት ሁለት የመጨራሻ ፊደሎች ሲተነተኑ “Lie Factory/የቅፈት ማሽን/ፋብሪካ” የሚለውን ይወክላሉን? 

እንደዚሁም ሁሉ “ህወሀት” በሚለው የአማርኛው አህጽሮ ቃል ውስጥ የሚገኙት እና “ሀት“ በማለት የሚነበቡት የመጨረሻዎቹ ሁለት ፊደሎች “ሀሰት ትረካ“ የሚለውን ይወክላሉን? 

ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከጫፍ እስከ ጫፍ እራሱን ዶግ አመድ ለማድረግ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ የሚገኘውን የሕዝቦችን ታሪካዊ እና መጠነ ሰፊ አመጽ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘንድ እውቅና ለማሳጣት እና አኮስሶ ጥላሸት ቀብቶ ለማቅረብ በሚል ዕኩይ ምግባሩ የተዛባ እና የማወናበጃ  መረጃን በማሰራጨት ዘመቻ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ገዥው ፓርቲ ዘ-ህወሀት ስሙ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ ወንጀለኛ እና አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡

ማወናበጃ መረጃ “ሆን ተብሎ ውሸት  የሆነ  ወይም ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማሰራጨት “ማለት ነው፡፡ የማወናበጃ ሀሰት መረጃ የማሰራጨቱ ዋናው ዓላማ አታላይ እና በቅጥፈት የተሞሉ መግለጫዎችን በመስጠት የለየላቸው ተራ እና ነጭ ውሸቶች እውነተኛ እንደሆኑ አድርጎ በማቅረብ በሕዝብ ላይ የማጭበርበር ስልትን በመተግበር ያነጣጠረ ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

ማወናበጃ መረጃ በዘ-ህወሀት የፖለቲካ ሰውነት ደም ስር ውስጥ ይዘዋወራል ፣ 

ከዘ-ህወሀት የማወናበጃ  መረጃ ስርጭት ዘመቻ ውስጥ በምሳሌነቱ ከሚነሳው አንዱ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ በሞተ ጊዜ ያሰራጩት ቅጥፈት ነው፡፡

የሚገርመው ነገር መለስ ከሞተ ከሳምንታት በኋላ ዘ-ህወሀት መለስ ከህመሙ እንዲያገግም በእረፍት ላይ ነው በማለት ተራ ቅጥፈቱን ለቆ ነበር፡፡

የዘ-ህወሀት አመራሮች የዓለምን ህዝብ በውሸት ለማሳመን በሚል ዕኩይ ምግባር መለስ ለበርካታ ጊዜ ለሕዝብ አገልግሎት ሲል ራሱን መስዋዕት አድርጎ ያለምንም እረፍት ሌት ቀን ይሰራ ስለነበር በአሁኑ ጊዜ ታሞ ከነበረበት በሽታ በማገገም ላይ ይገኛል በማለት ክብር በሆኑት የሰው ልጆች ላይ ዋሽተዋል፡፡ አሁን በህይወት ስለሌለው ስለአምባገነኑ መለስ የጤንነት ሁኔታ በየቀኑ የሀሰት እና የተዛባ ቅጥፈት የሞላው መግለጫ ለሕዝብ ይሰጡ ነበር፡፡

በዚያን ወቅት ዋናው የቅጥፈት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር የነበረው እና በመዋሸት ልቅናን የተጎናጸፈው እንደ አቡጀዲ የሚተረተረው  መሰሪው በረከት ስምኦን በኢራቅ ጦርነት ወቅት የሳዳም ሁሴን የመረጃ ሚኒስትር ሆኖ የሀሰት መረጃን ሲያስተላልፍ የነበረውን ኮሚካል (አስቂኙ) አሊን አስታወሰኝ፡፡ እ.ኤ.አ በ2003 በአሜሪካ እና በኢራቅ መካከል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት አሜሪካኖች ጦርነቱን በድል አድራጊነት አጠናቅቀው ሁሉንም ነገር በቁጥጥራቸው ካዋሉ እና ታንኮቻቸውንም በከተማው ማዕከላዊ ቦታ ላይ በማቆም እየተዘዋወሩ በመዝናናት ላይ በነበሩበት ወቅት ኮሚካል አሊ የተባለው የበረከት ዓይነት ቀጣፊ እንዲህ የሚል የጦርነት ዜና ዘገባ ሲያሰራጭ ነበር፣ “አሜሪካኖች በከፍተኛ ሁኔታ እየተማረኩ ነው ወይም ደግሞ ከነታንኮቻቸው ይቃጠላሉ፡፡ ይማረካሉ፣ እነርሱ ናቸው የሚማረኩት“ ነበር ያለው ዓይኑን በጨው ታጥቦ እና ጆሮውን ሸምጥጦ በሚዋሽ እና በሚቀጥፍ አንደበቱ፡፡

በእርግጥ ቀጣፊው ኬሚካል ዓሊ አሜሪካኖች የመማረክ እና ከነታንኮቻቸው እየጋዩ ነው እያለ በመቅጠፍ ላይ በነበርበት ወቅት አሜሪካኖች ግን ሁሉንም ነገር አጠናቅቀው ታንኮቻቸው እና የጦር መሳሪያ የሚጭኑት ታላላቅ ተሽከርካሪዎቻቸው ከመረጃ ሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ገትረው ተረጋግተው ቆመው ይታዩ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የቅጥፈት አንደበት ባለቤቱ ሸረኛው በረከት ስምኦን አምባገነኑ መለስ ከሞተ ሳምንታት አልፈውት እያለ መለስ ከህመሙ አገግሞ በአሁኑ ወቅት በእረፍት ላይ ነው እያለ ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ እንደ አቡጀዲ ይቀደድ ነበር፡፡ ከእንደዚህ ያለ ቀጣፊነት እና ስንኩል አንደበት እግዚአብሄር በቸርነቱ ይጠብቀን!

እርግጥ ነው  እንደዚያ ዓይነት ዓይን ያወጣ ውሸት እየተፈበረከ ለሕዝብ በሚነገርበት በዚያን ጊዜ መለስ ያለምንም ጥርጥር ወደማይመለሰው ዘላለማዊ እረፍት ሄዶ ነበር፡፡

ውሸት፣ ሀሰት እና ተራ አሀዛዊ ቅጥፈት የህወሀትን የፖለቲካ ሰውነት የመሰረተ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ መለስ ነው ወይስ ደግሞ የምላስ ቅጥፈት?

አሁን ባለፈው ሳምንት ኒዮርክ ታይምስ የተባለው መጽሄት የሩሲያ አገዛዝ የማወናበጃ መረጃን እንዴት አድርጎ ጠንካራ መሳሪያ በማድረግ እንደሚጠቀምበት የሚገልጽ ትረካ እንደነበረው ይፋ አድርጓል፡፡ ያ ትረካ ሩሲያዎቹ እንዲህ የሚል ሀሳብ እንደሚያመነጩ ግልጽ አድርጓል፣ “ስለሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን ድርጅት /North Atlantic Treaty Organization ጉዳይ እና ስለምዕራብ ሀገሮች የኒኩሊየር መሳሪያዎች ስልት በሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች የተዛቡ እና ሙሉ በሙሉ ውሸት የሆኑ የመረጃዎች ጎርፍ በማጥለቅለቅ ላይ ይገኛሉ“ ነበር ያለው፡፡

የውሸት መረጃ ማሰራጨት ማኦ ዜዱንግ እንዲህ በማለት እንዳስቀመጠው ነው፣ “መቶ ጊዜ የተደጋገመ ውሸት እውነት ይሆናል“ የሚልን አስተሳሰብ የሰነቀ ነው፡፡ እነበረከትም መቶ ጊዜ እየደጋገሙ እንደ አቡጀዲ የሚቀደዱት ሕዝቡ እውነት ነው ብሎ እንዲቀበላቸው ከማሰብ የሚመነጭ ድሁር አስተሳሰብ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘ-ህወሀትን በመቃወም ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ ቋያ እሳት ተቀጣጥሎ የሚገኘውን ሕዝባዊ አመጽ የሻቢያ (ኤርትራ)፣ የግብጽ እና የሌሎች ምዕናባዊ ጠላቶች ስራ ነው በማለት የዘ-ህወሀት መሪዎች በምዕናባቸው ውስጥ በመፈብረክ ከእውነታው ውጭ በሆነ መልኩ በቀጣፊ አንደበታቸው መቶ ጊዜ ደግመው እና ደጋግመው በመዋሸት እንደበቀቀን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ እነርሱን በመቃወም በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጣጥሎ የሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ ላይ አጀንዳ ባላቸው እና የዓባይ ግድብ እንዲጨናገፍ በሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች አጋዥነት አሸባሪዎች የሚያካሂዱት ሁከት ነው በማለት መቶ ጊዜ ውሸታቸውን በመንዛት ላይ ይገኛሉ፡፡

የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አሁን በቅርቡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ እነርሱን በመቃወም ተቀጣጥሎ ለሚገኘው አመጽ ማብራሪያ ሲሰጥ በግድያ እና በማፈን ተግባራት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ “የሕገ ወጥ ኮሚቴዎች“ ስራ ሲሆን እጅግ ብዛት ያለው ድብቅ የጦር መሳሪያም አላቸው በማለት ተናግሯል፡፡

የዘ-ህወሀት የይስሙላው አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስትር (የወንጀል ሚኒስትር አላልኩም) በአሁኑ ጊዜ የሚታዩት ረብሻዎች በሰው ህይወት፣ በመንግስት እና በግል ንብረት ላይ ጉዳትን በማስከተል ላይ የሚገኙት የሕዝቦችን ሕጋዊ ጥያቄዎች ለማስቀየስ የሚሸረቡ የጸረ ሰላም ኃይሎች ድርጊት ነው ብሎ ነበር፡፡ ድንቄም ጽረ ሰላም ኃይሎች! እውነት ነው የእነርሱን ጭቆና እና አፈና በሰላማዊ መንገድ የሚቃወም እና እምቢ ለመብቴ የሚል ዜጋ ሁሉ ለእነርሱ ጸረ ሰላም ኃይል ነው፣ የጭቆና አገዛዛቸውን ገመድ ከስሩ በጥሶ ይጥለዋላ!

ከዚህም በተጨማሪ አሻንጉሊቱ እና የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬው እንዲህ ብሏል፣ “ኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር ባለበት በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ውስጥ የምትገኝ የተረጋጋች ደሴት ናት፡፡ ሕዝቦቻችን ጸረ ሰላም ኃይሎችን እና አሸባሪነትን በመዋጋት ተግባር ላይ ይገኛሉ“ ነበር ያለው፡፡ በሌላ አገላለጽ ዘ-ህወሀት ከሌለ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም የምትበታተነው እና ወደ አመድነት የምትቀየረው ሆኖም ግን የአፍሪካ ቀንድም በእሳት ነበልባል ይጋያል!

ዘ-ህወሀትና መለስ ቢች ናቸው አፍሪካ ቀንድን ከጥፋትና ምፃት ሊያድኑ የሚችሉ። ድንቄም!

ዘ-ህወሀት የኦባማ አስተዳደር እና የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች እንዲያስቡ የሚፈልገው እንደዚህ ነው፣ እናም በፈቃደኝነት ይታዘዛሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ኢትዮጵያን የውሸት መቀፍቀፊያ ምድር አድርጓታል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 “የመለስ የእንቅልፍ ሰዓት ተረቶች“ እና እ.ኤ.አ መጋቢት 2015 “የኢትዮጵያ ታላቅ ዴፕሎማት ታላቅ ቅሌት“ በሚሉ ርዕሶች ትችቶችን አቅርቤ ነበር፡፡

የማያወዛግበው እውነታ በእርግጥም የማይካደው ሐቅ በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያሉት ሕዝባዊ አመጾች በብዙሀኑ በታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የሚካሄዱ ተጨባጭ ንቅናቄዎች ናቸው፡፡

እንደ መስታወት የጠራውን እውነታ በመካድ ላይ የሚገኘው መቅኖቢስ የሆነው እና የድግግሞሽ ቀጣፊው ዘ-ህወሀት ብቻ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ለዘ-ህወሀት በአሸዋ ላይ መስመር አስምረውለታል፡፡ ዘ-ህወሀት ብን ብሎ መጥፋት አለበት፡፡ ይህ ምንም የሚያነጋግር ጉዳይ አይደለም።

ኢትዮጵያውያን ዘ-ህወሀት የሚለው ቃል ያማቸዋል ሰልችት ብሎዋቸዋል፡፡

በእርግጥ ዘ-ህወሀት አሁንም ቢሆን በጥሩ የጥንካሬ ደረጃ ላይ እንዳሉ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት በመውተርተር ላይ ይገኛሉ፣ እናም ሁሉንም ነገር እንደያዙ እና አሁንም ጌቶች እንደሆኑ ለመዝለቅ የሚችሉ መሆናቸውን ለማሳየት በመፍጨርጨር ላይ ይገኛሉ፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ ለመጨረሻው የግብዓተ መሬት ውድቀቱ በእግሮቹ ከወዲያ ወዲህ እየተላጋ በመንገዳገድ ላይ ይገኛል፡፡

ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ ከፈረስ ላይ ወድቆ የተፈረካከሰ ሽባ ሆኗል፡፡ ከዚህ በኋላ የንጉሱ ሰዎችም ሆነ ራሳቸው የንጉሱ ፈረሶችም እንደገና ደጋግፈው ሊያስቀምጡት በፍጹም አይችሉም፡፡

ለዚህም ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ ሳሞራ የኑስ፣ ስብሀት ነጋ፣ ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ጸሀዬ፣ አባዲ ዘሞ፣ ጸጋይ በረኸ፣ አዜብ መስፍን፣ ሀፍቶም አብረሃ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ (?) ወይም ደግሞ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ሰብስብ ውስጥ ያለ ሌላ ማንም ቢሆን የተፈረካከሰውን ዘ-ህወሀት እንደገና ጠጋግኖ ኮርቻ ላይ ሊያስቀምጡት በፍጹም አይችሉም፡፡

ዘ-ህወሀት የደነቆረ እና የማይሰማ መሆኑን ማንም ያውቃል (ቢያንስ የደነቆረ ለማስመሰል ይሞክራል) ሆኖም ግን በጆሮው ውስጥ የታመቀውን አንኩክ ቢያወጣው ኖሮ የደወሉን ድምጽ ሊሰማ ይችል ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት ደወሉ ለማን እንደሚደወል ቢጠይቀኝ ኖሮ ጆን ዶኔ  በአንዲት መስመር እንዳለው፡ “ለእናንተ ነው የሚደውለው፡፡“

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ዘ-ህወሀት እኛን ለማታለል እንዲችል ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ በሌላ አገላለጽ የዘ-ህወሀት አጭበርባሪዎች እኛን እንዲያታልሉን፣ የዘ-ህወሀት  አታላዮች እኛን እንዲያሞኙን በፍጹም ልንፈቅድላቸው አይገባም፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ይህንን ትችት እያቀረብኩ ያለሁበት ምክንያት ዘ-ህወሀት ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተዛባ እና የሀሰት መረጃ በማሰራጨት ሕዝብን ሲያደናገር የቆየ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል እንዲገነዘብ እና አሁንም ቢሆን አንጸባራቂ የሆነውን ሕዝባዊ አመጽ አሳንሶ እና አኮስሶ ጥላሸት ቀብቶ በማቅረብ ምንም ነገር እንደሌለ እና በጥቂት ጽንፈኛ ዲያስፖራዎች እና በሀገር ውስጥ ባሉ ተላላኪዎቻቸው የሚደረግ የሻይ መገንፈል ዓይነት ቀላል ነገር ነው የሚለውን የቅጥፈት የማወናበጃ መረጃ ዘመቻ ሕዝቡ ሳይቀበል የነጻነት ትግሉን በተጠናከረ እና በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ እንዲቀጥል አጽንኦ በመስጠት ለማሳሰብ ነው፡፡

ለበርካታ ዓመታት ዘ-ህወሀት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ሲያራግብ የቆየውን በርካታ የተዛባ እና የቅጥፈት መረጃዎች ዘመቻዎችን እየተከታተልኩ በማጋለጥ ትችት ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ውዝግብ ተከትሎ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ አድራጊ ፈጣሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁትን ሰላማዊ ዜጎች ድምጻችን ተዘረፈ በማለት ተቃውሟቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ በመሰለፋቸው ብቻ በጠራራ ጸሀይ በጥይት እየተደበደቡ እንዲያልቁ ካደረገ በኋላ እነዚህ ሰዎች ሕገመንግስቱን እና ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጸረ ሰላም ኃይሎች ናቸው በማለት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳመን የተዛባ እና በቅጥፈት የተሞላ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሲያደርግ ነበር፡፡

በቪዲዮ በተቀረጸ ቃለመጠይቅ ቀጣፊው መለስ ዜናዊ እስከ 194 የሚደርሱ ሲቪሎች የተገደሉበት እያለ በሚጠራው በቅጥፈት ለማሳመን ያለ የሌለ ጥረቱን እድርጓል፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “…በኢትዮጵያ ውስጥ በሕገመንግስታዊው ስርዓት ላይ ያንዣበበ ትልቅ አደጋ ነበር፣ እናም ያ አደጋ መመከት ነበረበት፡፡“ በእርግጥ እልቂትን በመፈጸም ማለቱ ነበር፡፡

በሌላ አገላለጽ ሰላማዊ አመጸኞች ሞታቸውን እራሳቸው ጋበዙ እናም የእነርሱ ሞት ምንም ማለት አይደለም ምክንያቱም ሕገመንግስታዊውን ስርዓት በኃይል ለመናድ ሙከራ አድርገው ነበርና ማለቱ ነው፡፡ እንግዲህ የአሸባሪዎች የማለት መግባቢያ ኮድ (የተሸፈነ ቃል) ይኸው ነው፡፡

ቀጣፊው መለስ እልቂቱ የዓለምን መሪዎች አመለካከት ስለመቀየር አለመቀየሩ እና በእርሱ ላይ አሉታዊ አመለካከት እንደማይኖር በመጠራጠር ተናግሮ ነበር፡፡ “ሆኖም ግን የኢትዮጵያን ገጽታ በግልጽ ጠላሸት ቀብቷል” ነበር ያለው፡፡ ቀላል በሆነ አገላለጽ አሸባሪዎችን መግደል ከጉዳይ የሚገባ ነገር አይደለም፣ እናም በእርሱ ክብር እና ተማዕኒነት ላይ የሚያስከትለው ምንም ዓይነት ነገር የለም ማለት ነው፡፡ አዎ ርግጥ ነው ቀጣፊው መለስ ያንን ሲል ልክ ነበር፡፡ ምንም የሆነው ነገር የለማ! እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን የሰላማዊ ዜጎች እልቂት ተከትሎ በነበሩት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ጊዜ ውስጥ አሜሪካ ለዚህ እጁ በደም ለታጠበው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ገዳይ ስብስብ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ አስታቅፋዋለች፡፡ እናንተ ሕዝብን ለመግደል ያበርታችሁ እንጅ እኛ በዶላር እናንበሸብሻችኋለን ከማለት ሌላ ይኸ የዓለም የዴሞክራሲ እና የሰላም ጠበቃ ነኝ ከሚል ሀገር የሚጠበቅ ጉዳይ ነውን?

እንደ አጋጣሚ ሆኖ በእራሱ በአምባገነኑ መለስ ትዕዛዝ ተቋቁሞ የነበረው የምርመራ ኮሚሽን ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው ዘገባ “መሳሪያ ባልታጠቁት ሰላማዊ አመጸኞች የወደመ ንብረት የለም፣ እንደዚሁም ሁሉ አንድም ተቃዋሚ አማጺ ጠብመንጃም ሆነ ቦምብ የታጠቀ አልነበረም (ጥቂት አማጺዎች የጦር መሳሪያ ታጥቀዋል በማለት በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት የመገናኛ ብዙህን የተሳሳተ መረጃ አሰራጭተው ስለነበር) በማለት የመለስን ያፈጠጠ እና ያገጠጠ ቅጥፈት አጋልጧል፡፡ ፖሊስ እና የደህንነት ኃላፊዎች ሆን ብለው እያነጣጠሩ በመተኮስ ግንባራቸውን እና ደረታቸውን በጥይት እየደበደቡ 193 ሰላማዊ ዜጎችን የገደሉ ሲሆን 763 የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርገዋል፡፡” (የምርመራ ኮሚሽን ነው ያለው በቅንፍ የተቀመጠውን።)

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 ዘ-ህወሀት የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት እና የአልሻባብ አሸባሪዎችን ለማጥፋት በሚል ሰበብ በሶማሊያ ላይ ያደረገውን ወረራ የሀሰት የመረጃ ቅጥፈት መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋልጫለሁ፡፡

ቀጣፊው መለስ ዜናዊ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት በኢትዮጵያ ውስጥ የታጠቁ ተቃዋሚ ኃይሎችን በማሰልጠን፣ በማስታጠቅ እና ሰርገው እንዲገቡ እና ጥቃት እንዲፈጽሙ እያደረገ ነው ያለው፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ብጥብጥ እና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ነው የሚፈልጉት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ከደህንነት ኃይሎቻችን ጋር ፍልምያ በመግጠም ላይ ይገኛሉ“ በማለት ነበር ተራ ቅጥፈቱን በአደባባይ ያሰራጨው፡፡ ቀጣፊው ዜናዊ ገና ለገና  ጥቃት ይደርስብኛል በማለት በፍርሀት ተውጦ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር አንቀጽ 51ን በመተላለፍ የውሸት የሕግ ድጋፍን በመጥቀስ ባዶ እርቃኑን የቀረ መሆኑን ለመሸፈን ሲል የቅጥፈት የመረጃ ማሰራጨት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሎበት ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 “የክህደት (መዋሸት) አባዜ“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ረሀብ በማስመልከት ዘ-ህወሀት ሲያሰራጭ የነበረውን ተራ የቅጥፈት ዘመቻ አጋልጫለሁ፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ 1991 ስልጣንን ከተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የሚባል ነገር በፍጹም እንደሌለ ሁልጊዜ በመስበክ እና ተራ ቅጥፈት በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ረሀብ ሳይሆን “የምግብ እጥረት”፣ “ከፍተኛ የሆነ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት”፣ “ድርቅ”፣ ወዘተ  ነው በማለት በማደናገር እና የውሸት መረጃ በማሰራጨት ዘመቻ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢኮኖሚው በዓመት በአማካይ ከ10 በመቶ በላይ እድገት እያሳየ የዘለቀበት ሁኔታ ነው ያለው በማለት ወተት እና ማር የሚታፈስባት እና የሚዛቅባት ሀገር (በእርግጥ ለእነርሱ አሁንም ናት) እንደሆነች አድርገው የቅጥፈት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን አጠናክረውበት ይገኛሉ፡፡ ረሀብ በፍጹም ሊከሰት አይችልም ይላሉ፡፡

ዘ-ህወሀት ከዚህም አልፎ የዩኤስ አሜሪካንን እና የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎችን የባዶ ፕሮፓጋንዳ አጫፋሪነት በማግኘት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በጣት ከሚቆጠሩት በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ካሉት ሀገሮች ተርታ መካከል ተሰልፋለች በማለት አብረው በመዘመር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም ዓይነት ሀፍረት የማይሰማቸው ፍጡሮች ዓይናቸውን በጨው ታጥበው እንደገና ምላሳቸውን በተለመደው መልኩ በማጠፍ ኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት በማያውቅ የረሀብ አደጋ ውስጥ ወድቃ ትገኛለች ብለው አረፉት፡፡ ጉድ እኮ ነው! ለመሆኑ በየዓመቱ ከ10 በመቶ በላይ እያደገ እና እየተመነደገ የቆየ ኢኮኖሚ አልሆነ በሶስት አራት ዓመታት እንዴት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝቡን ለረሀብ ሊያጋልጥ ይችላል? የእነዚህ የሶስቱ ውሸታም እና ተራ የቁጥር ጨዋታ ደርዳሪ ኃይሎች (ዘ-ህወሀት፣ ዩኤስ አሜሪካ እና የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች) ተራ ቅጥፈት ከዚህ ላይ የበለጠ ቁልጭ ብሎ እርቃኑን ቆሞ በግልጽ ይታያል፡፡ እነዚህ ስብዕናቸውን በቅጥፈት የለወጡ አካሎች እኛ ምንም ነገር የማናውቅ ደደቦች እንደሆንን አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እውን በእርግጥ ነን እንዴ ጃል? (እጅግ በጣም የሚያስገርም ነገር ነው!)

እንደ እድል ሆኖ ከምንም በላይ ከጥርጣሬ በጸዳ መልኩ በተጨባጭ መረጃ በመመስረት ዘ-ህወሀት አስመዘገብኩት እያለ በመጥራት የሚደረድረው የኢኮኖሚ እድገት ተራ ውሸት እና የቁጥር ጨዋታ መሆኑን የሚያረጋግጥ ትችት ካቀረብኩ በኋላ ያ የውሸት የመረጃ ማሰራጨት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቆሟል፡፡ ይኸ አንድ የትግሌ ውጤት ብዬ አምናለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን ዘ-ህወሀት በየዓመቱ ላለፉት አስር ዓመታት ከ10 በመቶ በላይ ዓመታዊ አማካይ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቧል እናም እውነት ነው ብሎ ለማሳመን የሚሞክር እና መረጃ ለማቅረብ ድፍረቱና በቂ ማስረጃ ያለው ማንም ሰው ካለ መቶ ጊዜ ደግሜ እና ደጋግሜ ለመሞገት ዝግጁ ነኝ፡፡

እ.ኤ.ኤ በ2016 ኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት የማያውቅ አስከፊ ረሀብ የተጋረጠባት መሆኗ ሲረጋገጥ ዘ-ህወሀት ከጥንት ከጫካ ጀምሮ ተጠናውቶት የመጣውን ጥልቅ ጥላቻ በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሌለ የሚቆጥረውን ተራ የረሀብ የመረጃ ማሰራጨት ዘመቻ ውሸታቸውን በማናፈስ ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን በቅርቡ በኒዮርክ ኒውስ መጽሔት በወጣ ጽሁፍ (ዓለም አቀፋዊ ህትመት) አንድ በጥልቅ ጥላቻ የተሞላ እና የታወቀ የህወሀት አባል ኩራትን በተላበሰ መልኩ “በኢትዮጵያ የታላቁ ረሀብ ፍጻሜ ነው፣ ኢትዮጵያውያን በረሀብ አይሞቱም፣ እንስሶቻቸው ናቸው በውኃ ጥም የሚሞቱት” በማለት እምቧ ከረዩ የሚል እንደምታ ያለው የቅጥፈት ጽሁፍ አስነብቧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ሆና የምትገኘው ጋይሌ ኢ. ስሚዝ እና ከጫካ ጀምሮ ሌላዋ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊ በተመሳሳይ መልኩ ይህንኑ አንድ ዓይነት ነገር ነው የተናገረችው፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 አሁን በህይወት የሌለው ቀጣፊው መለስ ለምን ወደ ኢትዮጵያ በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጨውን የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎትን ለማፈን እንደወሰነ በማስተላለፍ ላይ የነበረውን የሀሰት የመረጃ ስርጭት ዘመቻ አጋልጨ ነበር፡፡ ቀጣፊው መለስ “ቪኦኤ የሩዋንዳን ዓይነት ኢንተርሃሞይ (በክንዋንዳ ወይም ደግሞ በሩዋንዳ ቋንቋ ማለት “በአንድነት የቆሙ፣ የሚሰሩ፣ የሚዋጉ እና ጥቃት የሚያደርሱ“ የዘር ፍጅት የሚያደርስ ነው” በማለት የቅጥፍና ቱልቱላውን ለቆ ነበር፡፡ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት እንዲሉ ደም የተጠማው ዛሩ እያሰገደደው የተናገረው ይመስላል፡፡ ቀጣፊው መለስ ማብራሪያውን በመቀጠል እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በበርካታ አጋጣሚዎች የቪኦኤ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት የሩዋንዳን የሬዲዮ ሚሌ ኮሊንስን ሬዲዮ ጣቢያ ተሞክሮን የቀዳ እና የጋዜጠኝነት የመጨረሻ መስፈርት ስነምግባርን እንኳ የማያሟላ እና በአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተጠምዶ የሚገኝ ሬዲዮ ጣቢያ ነው” ነበር ያለው፡፡

እውነቱ ሲፈተሽ ግን ቀጣፊው መለስ እና ዘ-ህወሀት ሁለቱ እራሳቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲካሄድ ሲሰብኩ እና አጠናክረው ሲተገብሩ የቆዩ የማፊያ ቡድን ስብስብ አባላት የነበሩ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 ዘ-ህወሀቶች በጠላቶች ላይ የሚደረግ ጦርነት እያሉ በባዶ ምዕናባቸው ላይ ብቻ ፈጥረውት ያለ እና የሕዝብን ቀልብ የማስቀየሻ ዘዴ እንደሆነ እና የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ላይ እንደሚገኙ በመግለጽ ዘ-ህወሀት ሲያራምድ የነበረውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማጋለጥ ጽፌ ነበር፡፡

ቀጣፊው መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “አሁን በቅርቡ ኤርትራ ሀገራችንን ለማሸበር አልሻባብን እና በሀገር ውስጥ ያሉትን አውዳሚ ኃይሎች በማሰልጠን እና በማሰማራት ላይ ትገኛለች፡፡ ሆኖም ግን ከእነዚህ አውዳሚ ኃይሎች ግብጽ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፋ ትገኛለች“ ነበር ያለው፡፡ ቀጣፊው መለስ እንዲህ በማለት የጭቃ ጅራፉን አጩሆ ነበር፣ “የኤርትራ ሕዝቦች አምባገነኑን አገዛዝ ገርስሰው እንዲጥሉት በተለያዩ መንገዶች ማገዝ ይኖረብናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኤርትራ መንግስት እኛን ለመውጋት የሚሞክር ከሆነ እኛም ተመጣጣኝ የሆነ የአጻፋ ምላሽ እንሰጣለን” ነበር ያለው፡፡ ይህም ማለት የአይጥ ጦረኛ በድንቢጥ ጦረኛ ላይ ዉግያ ጀመረ እንደማለት ነው ፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2/2014 ዘ-ህወሀት ከአዲስ አበባ መናገሻ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ በ80  ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው በአምቦ ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ ወጣቶች በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት በመቃወም ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ በመግለጻቸው ብቻ በ47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እምቦቃቅላ ተማሪዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት እልቂትን ፈጽመዋል፡፡ ዘ-ህወሀት የፈጸመውን እልቂት ለማስተባበል በሚል ዕኩይ ዓላማ ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች የለኮሱት እና ያስተባበሩት የኃይል አመጽ ነው የሚል የቅጠፈት መረጃ ዘመቻ አካሂዷል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ዘ-ህወሀትን በማውገዝ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቷል፣ “በአምቦ፣ በነቀምቴ፣ በጂማ እና በሌሎች ከተሞች በሰላማዊ አማጺዎች ላይ ግድያ እና ድብደባ ተፈጽሟል፡፡“

ፕሬዚዳንት ኦባማን  እንኳ ሳይቀር የዘ-ህወሀት ቀጣፊ አወናባጆች በቁጥጥራቸው ስር አርገዉት ነበር ፡፡ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ኦባማ ኢትዮጵያን በጎበኘበት ወቅት እንዲህ በማለት እስከጥርሱ ድረስ ዋሽቷል፣“ወደ እነዚህ ጉዳዮች በምመጣበት ጊዜ ምላሴን አላጥፍም፡፡ ማንኛውንም መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ጨምሮበኃይል ለማስወገድ የሚጥርን ቡድን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ የሄደችበትን መንገድ እና ያጋጠማትን ችግር በውል እንገነዘባለን፡፡ አሁን በቅርቡ ነው ሕገ መንግስት የተቋቋመው እና በተደረጉት ምርጫዎች ዴሞክራሲያዊ መንግስት የተቋቋመው በማለት እንደ የገደል ማሚቶ ውሸቱን ያስተጋባው። ኦባማ ያአለምን ህዝብ በመቂስፈት አድናገጠው አንደዚህ በሬ ወለደ አይነት ዉሸት ሲዋሽ ፡፡

ኦባማ ትክክል ነበር ምላሴን አላጥፍም ሲል ፡፡ ለዚህ ይሆን እባብ መንታ ምላስ ያለው? ለዚህ ነው እባብ ጥርስ የሌለው?

እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ዘ-ህወሀት ምርጫዎችን አካሄደ እናም ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍኩ በማለት አወጀ፡፡ አዎ፣ መቶ በመቶ፡፡

በነገራችን ላይ እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 በዚያው ዓመት ተደረገ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ አለ፡፡ በዚያን ጊዜ እ.ኤ.አ በ2015 በሚደረገው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ዘ-ህወሀት መቶ በመቶ ያሸንፋል በማለት ተንብየ ነበር፡፡

ዘ-ሀወሀትም ያምንም ጥርጥር እንደተነበይኩት አደረገ፡፡

ባለፈው ዓመት ዘ-ህወሀት የኦሮሚያን እና የአማራ ክልሎችን የግድያ የጦር ሜዳ ቀጣናዎች አድርጓቸዋል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ ሰኔ 16/2016 እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡

“በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በአብዛኛው ሰላማዊ በሆኑ ተቃዋሚዎች ላይ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ እንደሚወስዱ እና ጥልቅ ጥላቻ አሳይተዋል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች በተሰበሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚ ዜጎች ላይ ተኩስ በመክፈት በብዙሀኑ ሰልፍ ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፣ አሰቃይተዋል፣ ወደ እስር ቤት ዘብጥያም ወርውረዋል፡፡ አብዛኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወይም ደግሞ የተገደሉት ከ18 ዓመት በታች እድሜ ያላቸው ልጆች ናቸው፡፡ የጸጥታ ኃይሎች በእያንዳንዱ ተቃውሞ በመደበኛ ሁኔታ በደርዘን የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር ያውሉ እንደነበር እንደዚሁም ሁሉ የጸጥታ ኃይሎች በበርካታ አካባቢዎች በጨለማ ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ያውሉ እና ከመኖሪያ ቤቶቻቸው እያፈኑ ይወስዷቸው ነበር፡፡ የጸጥታ ኃይሎች እስረኞችን ያሰቃዩ እና ከሕግ አግባብ ውጭ የሆነ አያያዝ እንደነበር እና በርካታ ሴት እስረኞችም በጸጥታ ኃይሎች ሰራተኞች ይደፈሩ ነበር፡፡ በጣም ጥቂት እስረኞች ለሕግ አማካሪ፣ በቂ ምግብ ወይም ደግሞ በቤተሰብ አባሎቻቸው የመጠየቅ ተደራሽነት ነበራቸው፡፡“ (በኦሮሚያ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን እልቂት እና ስቅይት ከሂዩማን ራይትስ ዎች የቪዲዮ ምስል ይመልከቱ፡፡)

እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 “የኢትዮጵያ-ኤርትራ የሕዝብ ስሜት ማስቀልበሻ የጦርነት ጨዋታዎች“ በሚል ርዕስ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እያራመደው ስላለው ጦርነት፣ የጦርነት ወሬ እና የከበሮ ድለቃ የውሸት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ተራ ውሸት እና ቅጥፈት መሆኑን በማጋለጥ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር “አፈ ቀላጤ“ ጌታቸው እንዲህ ብሏል፣ “በሁለቱም ወገኖች በኩል ከባድ ጉዳት ድርሷል ሆኖም ግን በኤርትራ በኩል ያለው የበለጠ ነው፡፡ በዚህ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ በማድረግ ላይ እንገኛለን ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ መውሰድ ያሉብን እርምጃዎች በመጠንም ሆነ በዓይነት ቀደም ሲል ስንወስዳቸው ከነበሩት እርምጃዎች ከፍ ያለ መሆን ይኖርበታል፡፡“ ኤርትራ በበኩሏ ደግሞ 200 ኢትዮጵያውያንን ሙት እና 300ዎችን ደግሞ ቁስለኛ አድርጊያለሁ የሚል ዘገባ አቅርባለች፡፡ አይጥ ድንቢጥ ላይ ጦርነት ስትከፍት! ድንቢጥ አይጥ ላይ ጦርነት ስትከፍት፡፡

ዘ-ህወሀት በጎንደር፣ በባህርዳር በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች የሰብአዊ እልቂት ወንጀሎችን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ኃይልን በመጠቀም የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመጽ በኃይል በማኮላሸት እንደተለመደው ሲያራምድ የነበረውን አምባገነናዊ ስርዓት ማስቀጠል እንደሚችል አድርጎ ያምናል፡፡

ዘ-ህወሀት እና ወሮበላ ዘራፊ አባላቱ ወደመጡበት ገሀነም ተመልሰው መውረድ አለባቸው እላለሁ፡፡

በምድሪቱ የዘ-ህወሀት የማወናበጃ መረጃ ዘመቻ የክህደት ቴክኒክ፣

ዘ-ህወሀት በውሸት፣ በተራ ቅጥፈት እና የቁጥር ጨዋታ እኩይ ምግባሩ የተለያዩ የመረጃ ዘመቻ ቴክኒኮችን በመጠቀም በተለይም የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ያጭበረብራል፣ እንዲሁም ያታልላል፡፡

የማይካዱ እውነታዎችን መካድ፣ መካድ እና መካድ፣ ለምሳሌ ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ የሕዝቦችን ድምጽ በጠራራ ጸሐይ ከዘረፈ በኋላ ዓይኔን ግንባር ያድርገው በማለት ያለምንም ሀፍረት ካደ፡፡ ቀጣፊው መለስ የተከበረውን የኢትዮጵያን ሕዝቦች ድምጽ ከዘረፈ በኋላ መዝረፉም አልበቃው ብሎ ድምጻቸው በመዘረፉ የተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ወጎኖቻችን ያንን የመሰለ የድምጽ ዘረፋ እና ማጭበርበር የኢትዮጵያ ሕዝቦች እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ሳይታጠቁ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በመውጣታቸው ብቻ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የተነሱ ጸረ ሰላም ኃይሎች ናቸው በማለት የቅጥፈት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻውን ቀጥሎበት ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ ሕዝባዊ አመጽ ወይም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ በሚኖርበት ጊዜ እውነታውን ሁልጊዜ ይክዳል፡፡ የዘ-ህወሀት የውሸት የመረጃ ዘመቻ በሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱትን ሁሉንም ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እና ማናቸውንም የሕዝባዊ እምቢተኝነት ድርጊቶች “ሁከቶች” እና “የአሸባሪ ድርጊቶች” በማለት ይገልጻቸዋል፡፡

እያወቁ መካድ፣ ለምሳሌ ዘ-ህወሀት ረሀብ በኢትዮጵያ ውስጥ የለም በማለት የውሸት መረጃ ያሰራጫሉ ምክንያቱም ረሀብ ስለመኖሩ ግንዛቤው የላቸውም፡፡ ረሀብ ቢኖርም ቅሉ ስለእርሱ አያውቁም ነበር፡፡ ረሀብ መኖሩን እስካላወቁ ድረስ (ላለማወቅ የማስመሰል ስራ እየሰሩ) ረሀብ የለም በማለት ሙልጭ አድርገው ይክዳሉ፡፡ በጫካ ውስጥ ያለ ዛፍ ቢወድቅ እና መውደቁን ማንም ባይሰማው ወድቋልን? ለዘ-ህወሀት ዛፉ በፍጹም አልወደቀም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዘ-ህወሀት ማንኛውም ሕዝባዊ አመጽ ለመከሰቱ አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን ሕዝባዊ አመጾች እንደ ሰደድ እሳት ከጫፍ ጫፍ ተቀጣጥለው እየተመለከተ አልተከሰቱም የሉም በማለት የዘ-ህወሀትን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ማመን የለበትም፡፡

ኃላፊነትን መካድ፣ ዘ-ህወሀቶች እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣንን ከተቆጣጠሩ ጀምሮ ረሀብ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰተ ለመሆኑ በፍጹም አይፈቅዱም፡፡ የውሸት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻቸው ከፊል አካሉ ረሀብ በፍጹም የለም፣ ሆኖም ግን ረሀብ ቢኖርም ወይም ደግሞ ቀደም ሲል ተከስቶ ከሆነም እንኳ ለዚህ ተጠያቂው እግዚአብሄር/አላህ ነው ምክንያቱም ዝናም እንዲዘንብ አላደረገምና፡፡ እናም የእርሱ ችግር እንጅ የእነርሱ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ለተከሰቱት ሁከቶች ዋናው ምንጫቸው ላለፉት 25 ዓመታት ተንሰራፍቶ የቆየው እና የሚገኘው የእነርሱ ሙስና፣ የበከተው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ኃይል ውጤት ሳይሆን የውጭ ኃይሎች እና በተሳሳተ መንገድ የሚመሩት አሸባሪዎች ናቸው ብለው የቅጥፈት መረጃቸውን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡

ፋይዳን መካድ፣ ለምሳሌ ዘ-ህወሀት በእርግጠኝነት በሀገሪቱ ውስጥ ረሀብ የለም፣ አለ ከተባለም ያለው ከፍተኛ የምግብ ንጥረ ነገር ጉድለት ነው፡፡ የዘ-ህወሀት የውሸት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ በዓለም የድህነት አቃጣሪዎች የተፈበረኩትን እና ሕዝብን የሚያታልሉ እና የሚያደናግሩ ቃላትን በመተካት እና በመጠቀም ረሀብ በምንም ዓይነት መልኩ ተከስቶ እንደማያውቅ መከላከል ነው፡፡ በረሀብ በሚሰቃይ ሕዝብ እና በከፍተኛ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? የመጨረሻው ለመጀመሪያው ሀረግ ርህሩህ እና አስመሳይ ሀረግ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በተነጣጠሉ ሁከቶች እና በሕዝባዊ አመጾች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? የኋለኛው ዘ-ህወሀትን የሚያስፈራው ገሀነም ነው!

ድግግሞሽን መካድ፣ ዘ-ህወሀት እውነታን ለመቀበል እና ለመካድ በተመሳሳይ መልኩ በአንድ ጊዜ የውሸት መረጃ የማሰራጨት ዕኩይ ተግባሩን ይሰራል፡፡ ለምሳሌ ዘ-ህወሀት ጊዚያዊ የሆነ ረሀብ መሰል ነገር ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ አምኖ መቀበል ሆኖም ግን ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደማይችል የቅጥፈት መረጃቸውን ያሰራጫሉ፡፡ የዘ-ህወሀት የውሸት መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀሰው “ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት” በሚል ቅጥፈት ላይ የተመሰረተ እና ማንኛውም ረሀብ-መሰል ነገር ግን ወዲያውኑ ይጠፋል የሚል ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ምንም ዓይነት አመጾች የሉም፣ ሆኖም ግን አመጾች የሚኖሩ ቢሆንም እንኳ በአካባቢ የመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የመጡ አንድ ጊዜ የሚከሰቱ ክስተቶች ናቸው ብለው ተራ ቅጥፈታቸውን ያሰራጫሉ፡፡

አምኖ መካድ፣ የዘ-ህወሀት የውሸት መረጃ ሁሉንም ነገር ይቀበላል ሆኖም ግን ዋናውን ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምግብ እጥረት፣ የምግብ ዋስትና እጦት፣ ፍጹም የሆነ የምግብ እጦት፣ አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ከፍተኛ ድርቅ፣ ወዘተ ልትጋፈጥ እንደምትችል ያምናሉ፣ ሆኖም ግን ረሀብ የሚለውን ቃል በምንም ዓይነት መልኩ አይቀበሉም፡፡ ዘ-ህወሀት ደስተኛ ያለመሆንን፣ እረፍትየለሽነትን፣ ያለመርካትን፣ ያለመረጋጋትን፣ በቋፍ ላይ መሆንን፣ ወዘተ ይቀበላሉ፣ ሆኖም ግን ሕዝባዊ አመጽ የሚለውን ሀረግ በፍጹም አይቀበሉም፡፡

አጋጣሚን መካድ፣ ለምሳሌ ዘ-ህወሀት የውሸት መረጃ ምንም ነገር የለም ይላል፣ ረሀብን ማጥፋት አለብን ምክንያቱም የለምና፡፡ የሚኖር ከሆነ የእራሱን የመከሰት አካሄድ ይይዛል፡፡ የአካሄድ መንገዱን ለመቀየር የሚሰራ ነገር የለም፡፡ የማልተሳውያኖች ዋና ሕግ በስራ ላይ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ሕዝባዊ ተቃውሞ የለም ሆኖም ግን የሚኖር እንኳ ቢሆን ያለምንም ችግር የሚወገዱ ናቸው ይላሉ፡፡

ምን ዓይነት መቸረሻው ገሀነም ነው ጋንዲ እንዲህ ሲሉ?፣ “በታሪክ አምባገነኖች እና ገዳዮች ይኖራሉ፡፡ ለጊዜው የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ጊዜ ሁልጊዜም ቢሆን ይወድቃሉ፡፡ ሁልጊዜ፡፡“

ምንም ሆነ ምን መሆኑ አይቀርም…

ማኦ ዜዱንግ እንዲህ ሲል ትክክል ነበር፣ “መቶ ጊዜ ደግሞ እና ደጋግሞ የተነገረ ውሸት እውነት ይሆናል፡፡“

ዘ-ህወሀት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ውሸቶችን ይናገራሉ፣ ሆኖም ግን ቅንጣት ታህል እውነትን አይናገሩም፡፡

የዘ-ህወሀትን የውሸት መረጃ ዘመቻዎች በተለይም በአሁኑ ጊዜ ማጋለጥ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ የአማራ-ኦሮሞ ህብረት ብለው የሚያምኑትን ለማኮላሸት እና ለማጥፋት መጠነሰፊ የሆነ የውሸት መረጃ ስርጭት ዘመቻ የምህንድስና ስራቸውን በመስራት ላይ እንዳሉ ምክንያቶች እንዳሉኝ አምናለሁ፡፡ 

የውሸት የማወናበጃ መረጃ ስርጭት ዘመቻ በርካታ ነገሮችን ያካትታሉ፡፡ እነዚህም፡

1ኛ) በሁለቱ ቡድኖች መካከል የማይታረቅ ጥላቻ ለመፍጠር የተወሰኑ ታሪካዊ ክስተቶችን እና ግጭቶችን በመምረጥ መጠቀም፣

2ኛ) በሁለቱ ቡድኖች መካከል የጎሳ ጥላቻ ለመቀስቀስ የእራሳቸውን ደጋፊዎች እንደ ወኪል መጠቀም፣

3ኛ) በእያንዳንዱ ቡድን መካከል መተማመን እንዳይፈጠር እና መከፋፈል እንዲፈጠር እና በመጨረሻም እያንዳንዱ ቡድን እንዲበታተን ለማድረግ ከፋፋይ ፕሮፓጋንዳ መንዛት፣

4ኛ) ስለ ኦሮሞ እና አማራ መሪዎች እና ድርጅቶች በደህንነት ኃይሎች አማካይነት ከፋፋይ ሀሜትን መፍጠር፣

5ኛ) አንጸባራቂውን ሕዝባዊ አመጽ የአሸባሪዎች ንቅናቄ እና ተጠርጣሪዎች ያንን እንዲያረጋግጡ ማስረጃ በመፈብረክ ጥላሸት መቀባት፣

6ኛ) ሕዝባዊ አመጹን ለማስቆም በሚል ተስፋ ለዘ-ህወሀት የሚሰሩት የክልል እና የአካባቢ አመራሮች ለጥፋቱ ኃላፊነቱን ወስደው ጥፋተኝነታቸውን እንዲቀበሉ የሕግ ስርዓቱን መጠቀም፣

7ኛ) በሕዝባዊ አመጹ ውስጥ ሰርጎ መግባት እና ከውስጥ ጥንካሬ እና ትብብር እንዳይኖር ለማድረግ የእራሳቸውን የኦሮሞ እና የአማራ ቡድኖችን ማደራጀት፣

8ኛ) የሕዝቡን ቀልብ ከሕዝባዊ አመጹ ለማስቀየስ (በጎረቤት ሀገር ላይ ጦርነት ማወጅ አላልኩም) መጠነ ሰፊ የማስቀየሻ ዘዴ መፍጠር፣

9ኛ) ልዩ ማበረታቻዎችን ለምሳሌም የብድር አገልግሎት በመስጠት ወጣቶችን መግዛት እና ገለልተኛ እንዲሆኑ ማድረግ፣

10ኛ) በሪዮ ኦሎምፒክ ከፈይሳ ሌሊሳ የእምቢተኝነት ምልክት ድርጊት በዓለም ላይ በሚገኝ በ3.5 ቢሊዮን ሕዝብ ከታየ በኋላ ገጽታቸውን ለማሻሻል ወትዋች ባለሙያዎችን እና የሕዝብ ግንኙነት ወኪሎችን መጠቀም ወዘተ፡፡

በትክክል ለመናገር ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ላለው ሕዝባዊ አመጽ ከፍተኛ የሆነ ትኩረት በመስጠት እና በስልጣኑ እና የእርሱን የውጭ ተጠቃሚዎች በመጠቀም ማንኛውንም ነገር ሁሉ በማድረግ በስልጣን ላይ ተጠብቆ ለመኖር ነው፡፡

ሊካድ የማይችለው እውነታ የፈለገውን ያህል የውሸት መረጃ መሰራጨት ታሪክን ሊለውጠው አይችልም፡፡

ዘ-ህወሀት የአረብ ብረት የሆነውን የታሪክ ሕግ ፍርድ ማስታወስ፣ መማር እና መቀበል አለበት፡፡

በታሪክ አጋጣሚ ሁሉ አምባገነኖች እና ገዳዮች አሉ፡፡ ለጊዜው የማይበገሩ ይመስላሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡ ሁልጊዜ፡፡

ምንም ሆነ ምን መሆኑ አይቀርም…

ምንም ሆነ ምን…የዘ-ህወሀት የውሸት መረጃ ስርጭት ዘመቻ የአረብ ብረት የሆነውን የታሪክን ሕግ መቀየር አይቻልም፡፡

በመጨረሻ ሁሉም አምባገነኖች ይወድቃሉ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ጳጉሜ 3 ቀን 2008 ዓ.ም

 

 

Filed in: Amharic