>

ታሪክ የመጨረሻዎቹ እስኪያደርገን - እኛ የመጀመርያዎቹ ነን!" (ዳንኤል ክብረት)

daniel-kibretመጀመሪያዎቹ.. . በማስተርስ ስራ ያጣን፣ በድግሪ ኮብልስቶን የፈለጥን፣ መቶ ብር የአንድን ብር ዋጋ ሲያጣ የታዘብን፣ ጤፍ በሶስት ሺህ ብር የሸመትን፣ ደሞዝ 3ቀን የማይበረክትልን ፣ ኑሮ ባላየ ያለፈን፣ ፋሲካን በበግ ቅርጫ ያከበርን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . . .
_
ለእንጀራ ለሚሰደደዉ ፀልየን ሳንጨርስ እንጀራም ሲሰደድ(ኤክስፓርት ሲደረግ) ያየን፣ ጤፍ ትቶን ላብራቶሪ የገባ፣ ማስቲካ በስድሳ ብር ገዝተን
ሳይጠዘጥዘን አላምጠን የተፋን፣
ግድግዳችንን የሚያስንቅ TV ያየን፣ በ3D የተደመምን በ7D ነፍሳችን
እስኪወጣ የጮህን፣ ባቡር ብርቅ የሆነብን እኛ የመጀመርያዎቹ
ነን. . .
_
ቡና ከአቦል ወዲያ አመድ አመድ ያለብን፣ ቡና በቂቤ ያልቀመስን፣ ነጭ ጠጅ የጠጣን፣ በወጉ ያልሰከርን፣ ሲያብዱ አይተን ያበድን እኛ
የመጀመርያዎቹ ነን. . .
_
በፌስቡክ ያጨን፣ በሰርጋችን ማግስት
‘ብርአምባር ሰበረል ሆ’ ተብሎ ያልተዜመልን፣ ድንግልና ከምድረገፅ የጠፋን (አይተን የማናዉቅ)፣ ቀብርን እንደሰርግ የቀረፅን፣ ሞተን በተቀበርንበት እያለ በሚያስመኝ የሬሳ ሳጥን ሲቀበሩ ብናይ በሟች የቀናን እኛ
የመጀመርያዎቹ ነን. . .
_
አንድ መሆን የጠፋን፣ የጀበና ቅርፆ ቢፈርስብን ክዳን የሌለዉ ማንቆርቆሪያ መሳይ የእናት ሃገር ካርታ የሳልን፣ ከ97 የተረፍን፣ ከኢቦላ ብናመልጥ ከአይኤስ የወደቅን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን.
_
. . . ለቦብ ሃዉልት ያቆምን፣ የኛን የረሳን የሰዉ ያሰብን፣ በሌጋሲ የተመራን በራእይ የበለፀግን፣ ታሪክ ስናነሳ ታሪክ ስንጥል የ3ሺ አመት ታሪክ ስናጎድፍ የ24 አመት ታሪክ ስናደምቅ የከረምን፣ መዉደቅን በተግባር የኖርን እኛ የመጀመርያዎቹ ነን. . .
_
. . . “ታሪክ የመጨረሻዎቹ
እስኪያደርገን፤ እኛ የመጀመርያዎቹ ነን!

Filed in: Amharic