>

ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ---ድንቄም ተቃዋሚ

aregawi-berheዶ/ር አረጋዊ በርሄ የ ዶክትሬት መመረቂያ ፁሀፋቸውን ያደረጉት የመሰረቱትን በመሰሪው መለስ ዜናዊ ተንኮል የተባረሩበትን የህውሀት ታሪክ በመዘገብ ነው!
ሰውየው ህውሀትን ፈጠሩ የመሰረቷት ህውሀት ደግሞ ጥርስ ስታወጣ ጇሯቸውን በጭቃ አባረረቻቸው! በፍቅሯ በርሀ የወጡላትን ህውሀት በዩኒቨርስቲ ታሪኳን አጠኑ እና ዶክተር ተባሉ!

ህውሀት እና አረጋዊ በርሄ ቁርኝነታቸው የፍቅር እስከ መቃብር አይነት ነገር ነው ! በስደት አገር ሁነው ለህውሀት ይሰልሉላታል ! ምስጢራዊ የህውሀት ማህበር መስርተው የሚስጥር ተንኮል ያጠነጥኑላታል !ብቻ ለህውሀት ኑረው ስለህውሀት ተምረው ለህውሀት ይሞቱ ይሆናል !
ቴዲ አፍሮ ብርይናየ ያለውን ዘፈን እሳቸው እንዲህ ብለው አንጎራጉረዋል አሉ ( መቼም ሚስጢር አይደበቅ)

ህውሀቴ አንች የልጅነቴ ቀለም
እኔ እስካሁን እንዳንቺ ያጠናሁት የለም !

እኔ እንጃ በዶክትሬታቸው ይስሩበት የግድግዳ ጌጥ ያርጉት አላውቅም ብቻ ስለህውሀት ዶክተር ተብለዋል !

በነገራችን ላይ በተመረቁበት ይሰሩበታል ላልኩት ጥያቄ እኔው ልመልሰው እናንተ ምን በወጣችሁ አወ! ይሰሩበታል የህውሀት የሚስጢር አርቲተክት ሁነው ይሰሩበታል!

ተቃዋሚወች ውስጥ ገብተው ይበትኑበታል ! የእያንዳንዱን ተቃዋሚ ፓርቲ ደካማ እና ጠንካራ ጎን እያጠኑ ያቀርባሉ በርሀ የገቡትን ያስኮበልላሉ …እረ ስንቱ ! እኛ ግን ጎበዝ የዋህነታችን በዛ !

ይህችን ትንሽየ ነገር ለመሞንጨር ልቤ የተነሳሳበት አብይ ምክኒያት ሰውየው ዶክትሬት ሲመረቁ መመረቂያ ፅሁፋቸው ላይ ያች መዘዘኛ መሰሪ ካርታ ዱቅ ብላለች !

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የትም አላመጣውም ከህውሀቱ መስራች የጥናታዊ ፅሁፍ ነው ! EBC አስመሳይ ይቅርታውን ሲጠይቅ ዶ/ር አረጋዊ ይቅርታ የማይጠይቅበት ነገር አይግባኝም ! ጎበዝ እሂ ይሉኝታ ቅብጥርስ እኔ አይገባኝም ኢትዮጵያየን አፈራርሰው ታላቋን ትግራይ ሊገነቡ ይኳትናሉ እኛ ላባችነን ጠብ አርገን የሰራንበትን ገንዘብ እየጠበጠብን አረጋዊ በርሄን እንደ ክብር እንግዳ እንጋብዛለን… እረ ወግድልኝ አለ የ አገሬ ሰው ! ወግድልኝ ልንለው ይገባል ! ጥናታዊ ፅሁፉን ይህችን ሊንክ ጫን አድርጎ ማግኘት ይቻላል www.harep.org

ኣቶ ገብረመድህን አርአያም ”በአረጋዊ በርሔ ላይ ክስ መመስረት ይገባል” በማለት ያለመታከት መወትወታቸው አይዘነጋም። ሊንኩን ይጫኑ። http://quatero.net/amharic1/archives/28644 ድንቄም ተቃዋሚ!…”ዝሆን ላይ የሚጮህ እብድ ውሻ ብቻ ነው”
ከሶሻል ሚድያ
Filed in: Amharic