የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ  ዛሬ አዲስ አበባ. ይገባል! (ኤፍ.ቢ.ሲ)

የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ

 ዛሬ አዲስ አበባ. ይገባል!!!

ኤፍ.ቢ.ሲ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በውጭ ሀገር ላሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ የድርጅቱ አመራር በሆኑት በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ መሪነት ነው ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል። የግንባሩ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም ይጠበቃል። FBC
በተያያዘ ዜና :- አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.