የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ
ዛሬ አዲስ አበባ. ይገባል!!!
ኤፍ.ቢ.ሲ

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ የኦሮሚያ አንድነት እና ነፃነት ግንባር ልኡክ የድርጅቱ አመራር በሆኑት በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ መሪነት ነው ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል። የግንባሩ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም ይጠበቃል። FBC
በተያያዘ ዜና :- አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል።