ለ4 ወር ተቀጥሮ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰብሮ እንዲታይ ተወሰነ…!!!
ጠበቃ አቶ ሔኖክ አክሊሉ
ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓም ድረስ ምስክሮችን ለመስማት ተቀጥሮ የነበረው የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰብሮ እንዲታይ ለመወሰን ለጥር 5 ቀን 2013 ዓም ተቀጠረ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የህገመንግስትና የሽብርተኝነት ወንጀል ችሎት ዛሬ ታህሣሥ 28 ቀን 2013 ዓም የተከሳሾቹን ጠበቆች አስጠርቶ እንዳስታወቀው ፣ ተከሳሾች ጥር 5 ቀን 2013 ዓም ችሎት ቀርበው የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን የመስሚያ ቀናትና ጊዜ ለመወሰን ቀጠሮ መሰጠቱን የእነ አቶ እስክንድር ጠበቃ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል።
