>
5:13 pm - Tuesday April 20, 5660

በደካማ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኤርትራ ትገነባለች...!!! (መር እድ እስጢፋኖስ)

በደካማ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኤርትራ ትገነባለች…!!!

መር እድ እስጢፋኖስ


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቁልቁል እወረደ ነው።የ2020 አ.ም አመታዊ እድገት 1.9% ይሆናል።2021 አ.ም 0% ይሆናል 0% የሚሆነውም አሁን ያለው የትግራይ ጦርነት መፍትሄ ካገኘና የብሄር ነውጥ ግድያና ዘር ማጥፋት ከቆመ እንዲሁም የሱዳን ወረራ ሰላማዊ መፍትሄ ካገኘ ነው…!!!


ጠ/ሚ አብይ መስከረም የፓርላማ መክፈቻ ላይ ኢኮኖሚው 9% ያድጋል ብለው ሲደሰኩሩ በአሜሪካ ሀገር ይርሚገኘው የሎረ ሳመርስ አለም አቀፍ ኢንስቲቲዩት ትንበያ 1.9 %እንደሚሆን እድገቱ በማስረጃ የተደገፈ ቻርት ማውጣታችን ይታወሳል።
የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ከፍታና ዝቅታ በሀገራት እና በተቋማት ልዩነቶች የተለመደ ቢሆንም ጠ/ሚ አብይ ግን 9%ሲሉ የቅዥት አለም ላይ ቆመው እንደሆነ በግልፅ ይታይ ነበር።
ለአንድ አገር የኢኮኖሚ እድገት የመጀመሪያው መስፈርት ሴኩሪቲ ነው።ሁለተኛው መስፈርት ሴኩሪቲ ነው።ሶዎስተኛው መስፈርት ሴኩሪቲ ነው። አገር በመለኮታዊ ሀይል የምትተዳደር የመስላቸው ጠ/ሚ አብይ ኢትዮጵያ በኦሮሙማ እሳት እየተበላች እንደሆነ አልገባቸውም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ያልተረጋጋ መንግስት ዝርዝር ውስጥ ከ2018 አ.ም ጀምሮ መግባቷን እንኳ ማመን አልፈለጉም።2018 አ.ም ጀምሮ ምንም አይነት አዲስ ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ እንደሌላት መቀበል አልፈለጉም። ጥዋትና ማታ የሸገር ፖርክ እያሉ ሲያጨበጭቡና ሲያጨበጭቡ ከረሙ።ያአገሪቱን ውስብስብ የደህነት ታሪክ የእንጦጦ ፓርክ ይቀይር ይመስል።
በወያኔ ጊዜ ለ14አመታት የነበረው የኢኮኖሚ እድገት የሚቀጥል ስለመሰላቸው ያለምንም መረጃ የሚወዱትን ቅጡ የጠፋ “የመደመር ፖሊሲ” ህልማቸውን በመከተል 9%ታድጋለች አሉ።
ኦሞ ሌላ ሮል ሌላ።በስሜት ማውራት ሌላ። በስሌት ማውራት ሌላ።የኢኮኖሚ እድገት የሚመአጣው በአጨብጫቢዎች ተከቦ በሙገሳ በገፅታ ግንባታ ሳይሆን ሳይንሳዊ በሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው።
የአብይ ኦሮሙማ ዘረፋ ላይ እንጂ ፖሊሲ ላይ የለም።አገር እየመራ ሳይሆን ኦሮምያን እየመራ ነው።
የቀጥታ ኢንቨስትመንት 19%ቀንሷል።ምናልባት በ ኮቪድ ምክንያት ምንም ላይኖር ይችላል ።በ2021
35%የውጭ የእርዳታ አቅርቦቶች ላይኖሩ ይችላሉ አሁንም በኮቪድ ምክንያት። ይህ ማለት የሴፍቲ ኔት ፕሮግራሞች ሊታጠፍ ይችላሉ።ይህ ማለት በቀላሉ 9 ሚሊዮን ረሀብተኛ ተጨመረ ማለት ነው።
የአንበጣ ያስከተለው ጥፋት፥የጎርፍ ደጋ ያስከተለው ጥፋት እና ከውልቃይት ጀምሮ እስከትግራይ ድረስ ምርት በጦርነት ምክንያት ሰብል አለመሰብሰብ ተደማምሮ የኢትዮጵያን መፃኢ ሁኔታ መገመት አዳጋች ሆኗል።በትግርይ ጦርነት ብቻ 4.5 ሚልዮን ህዝብ ገና ካሁኑ ለረሀብ አደጋ ተጋልጧል።
በሌላ መልኩ የገንዘብ ግሽበቱ መቆሚያው የት እንደሆነ አይታወቅም።የኢትዮጵያ የውጭ ጫና እዳ ከመብዛቱ የተነሳ አገሪቱ በጠቅላላ የጥቁር ምዝገብ ውስጥ ልትገባ ትችላለች2021 አ.ም።ይህ ማለት ደግሞ ተጨማሪ የብድር አገልግሎት አታገኝም ወይም የማትታመን አገር ያደርጋታል ማለት ነው።
አገር ያለውጭ ፖሊሲ እና ያለ ኢኮኖሚ ፖልሲ እየተመራች ነው እያልን ላለፉት ሁለት አመታት ስንጮህ የነበረው ለዚህ ነው።
ሰባተኛው ንጉስ መሪያችን፥ ነብዩ መሪያችን፥ የሚሻግረን ሙሴው መሪያችን ፥በአረቦች እና በኢሳያስ መጫውቻ ሆኖ አገራችንን ወደ እርስበርስ ጦርነት አስገባት። ኢኮኖሚውንም ትቢያ ላይ ጣለው።
አሁን አገርቱ በውጭ ወራሪ ሀይል ተከባለች።የአፍሪካ የመን ለመሆን እየተቃረበች ነው።ሱዳን የውሰደችው መሬት አልበቃ ብሏት “ቤንሻንጉል ግዛቴነው” ስትል ተናግራለች።ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ “አልወጣን” ለተባለ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ድንድበራችን እስከ ቤንሻንጉል ይደርሳል ብለዋል።
ቱርክ እና ኳታር ሶማሌ ላንድን እያስታጠቁ ነው።ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ አጋር ነበረች ። አሜርካ ሞክራ ያቃታትን ጠ/ሚ አብይ አስታርቃልርሁ ብለው በመሞካራቸው ሶማሊላንድን አስኮርፈዋል። ለፎርማጆ በማዳላታቸው ቅሬታ ብቻ ሳይሆን “ሙአረስ” የሚል ስም አትርፈዋል።ፎርማጆ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት ልጅ ናቸው። እንደኢሳያስ እና እንደ አብይ አህመድ ሁሉ።
ኬንያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ጠላትነት ቆማለች።ምክንያት ? ዶ/ር አብይ የብስለት እጥረት እና የሚደርጉት በመርህ ላይ ያለተመሰረተ ግንኙት።አጉራ ዘለል ከግል ባህሪ የውለደው ጥላቻ በሀገር ደረጃ ወዳጅ ጎረቤት አልባ እያደረገን ነው።ይህ እንግዲህ ለወትሮው የኢሳያስ አፈውርቂ መገለጫ ባህሪ ነበር።
ኢስያስ አፈወርቂ ከአፍሪካ መሪ ይሄ ነው የሚባል አገር ውዳጅ አይደሉም።ለምን ? ሁሉንም ስለሚንቁ።
በተገናኙ ቁጥር የኢሳያስ አፈውርቂን እጅ በካሜራ ፊት ሳይቀር የሚልሱት (የሚስሙት) ጠ/ሚ አብይ የኢሳያስ አፈወርቂ በሽታ ተጋብቶባቸዋል በሚሰኝ ደርጃ ለጎረቤት አገር መሪዎች በሚያሳዩት ንቀት ጠላቶች አብዝተውልናል። ባለራእዩ መሪያችን።
የገልፍ አገሮች በጎን ለአብይ ገንዘብ እየሰጡ የአባይ ግድብ ተገንብቶ እንዳያልቅ ከግብፅና ከሱዳን ጀርባ ይፖለቲካ ሴራቸውን አጧጡፈዋል። በሀገርቱ ውስጥ ሰለፊዝም ተስፋፍቶ ይኽው ክርስቲያን እና አማራ እየተመረጠ የሚታረድባት አገር ፈጥረውልናል ።
የኢሳያስ ሲንድሮም የሚባል በሽታ የተጠናወታቸው አብይ ለኤርትራው አራጅና ገዳይ መንግስት ፍቅር ትግራዮችን ገብረው ኢሳያስ ለዘመናት ሊያፈርሳት የሚፈልጋትን ኢትዮጵያ በግላጭ አግኝቶ ቂም እና በቀሉን ተውጥቷል።
አሁን በኢሳያስ ተንኮል ልንጠፋ እንችላለን።ኢስያስ አፈውርቂ ማለት ጦርነት ነው። ኢሳያስ አፈውርቂ ማለት የኢትዮጵያ ካንሰር ነው ስንል የነበረው ለዚህ ነው።አሁን የዛሬ23 አመት በፊት ወደነበረው የኤርትራዊያን ቁማር አገራችን ተመልስለች።
የኢሳያስ ቡድን የኢኮኖሚ አውታሩን በደካማዋ ኢትዮጵያ እየዘርጋ ነው።EIA(የደህንነት ተቋም) በአዲስ አበባ ሶዎስት ቢሮዎች ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።
አዎ ኤርትራ አሁንም ዋጋ እያስከፈለችን ነው።
አሁን ግን በኦሮሙማ መንግስት ደርጃ የምትደገፍ አገር በመሆኗ የኢትይጵያ መጨረሻው ምን እንደሆነ መገመት አዳጋች አድርጎታል። ባንፃሩ የኤርትሪ ኢኮኖሚ በከፈተኛ እመርታ ላይ ይገኛል።የቻይና ኩባንያዋች በክፍተኛ ቁጥር ገብተዋል። ከ6 በላይ የኢንዱስትሪ መንደር በመገንባት ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ሰአት የኤርትራንኢኮኖሚ ደርጃ በቻርቱ ላይ ትመልከቱ።” 5.7% የኢኮኖሚ እድገት ታሳያለች ተብሎ ተተንብዩል በ2021 አ.ም። ለ3.5 ሚሊዮን ህዝብ ላላት ሀገር ይህ የእድገት አሀዝ እጅግ ግዙፍ ነው።”የአፍሪካ ሲንጋፖር ማለት ይህ ነው”።
ኤርትራ ይሄ ሁሉ የኢኮኖሚ እድገት የሚጠበቀው ሁለት ግዙፍ ውደቦቿን ገና ሳትጠቀም ነው።አዎ የኢትዪጵያ ውድቀት የኢርትራ ትንሳኤ ነው።በደካማ ኢትዮጵያ ላይ ኤርትራ ትለመልማለች።ይህ ነው የአብይ እና የኢሳያስ የፍቅር ውጤት።ይህ ነው የኢሳያስን እጅ መላስ እና መሳም ውጤት።
ከአጋም ጋር የተጠጋ ቁልቋል ሁልጊዜ ሲለቅስ ይኖራል እብዲሉ “አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ኤርትራ

ዋጋ ቢስ ጦርነት እንድናካሂድ አደረገችን የሚሳዝነው እና የከፋው 3ኛው የሱዳን ጦርነት አንሆ በደጅ ቆሞ እያንኳኳ ነው።
አገር በህብረት ቆመን እንዳንከልከል እንኳን የሽመልስ አብዲሳ እና የታየ ደንዳአ የኦሮሙማ መንግስት አማራን እያረደ እያሳረደ እያፈናቀለ በግዛት ማስፋትና መሬት ወረራ ላይ ተሰማርቷል ።በኦሮምያ ክ2 መቶ ሺ በላይ ተፈናቃይ አለ በአሁኑ ሰአት ።የኦሮምያ ፕሬዝዳት ሽመልስ አብዲሳ አፈናቃዮችን በህግ ተጠያቂ ከማድረግ የመርጡት ምንም እንዳልተፈጠረ መመልከት ነው።ይህ ብቻ አይደለም በየቀን በሚባል ደረጃ በኦሮምያ በአማራ ለይ ጭፍጨፋ እየደረሰ በየቀኑ የትዊተር መልክታቸው ላይ የሚሰፍሩት ” አዲስቷ ኦሮምያ እድገትና የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ስለመካሄዱ ነው። ስለመስኖ ስራ ነው”
ለሽመልስ አብዲሳና ታዬ ደንዳዳ በአማራዎች ላይ በኦሮምያ የሚደርሰው ጭፍጨፋ የአንድ ችግኝ ዋጋ እንኳ አላገኘም።
እንደ ሰው እንኳ ሀዘናቸውን አልገለፁም ።እንደ ብልፅግና አጋር ፓርቲ ይቅርና። እንደሰው በመተከል 220 ስው በአንድ ጉድጓድ ገብቶ ሽመልስ አብዲሳ ተውተር መልክታቸው” በኦሮምያ ዘመናዊ ግብርና እየተሳለጠ ነው የሚል ነው” ።ምናለ ለነውሩ እንኳ 3 ቀን ቢቆዩ።
ሁሉም ይቅር አገር ተወራለች በያቅጣጫው። ኦሮምያ 34ኛ ዙሩር ልዩ ሀይል አስመርቆ አሳይቶናል በጠቅላላ የሮምያልዩ ሀይል ሲታሰብ 70ሺ ደርሷል።አገር በተውረውረረችበት በአሁኑ ወቅት በግንባር ተሰልፎ ድጋፍ ይሰጣል? ውይስ ሽመልስ አብዲሳ እንዳለው ኦሮምያን ብቻ ይጠብቃል? የሚታይ ጉዳይ ነው።
አዎ” ያዋከቡት ነገር ” ያለው ጋሽ ጥላሁን ይሄንን ነው።ከጅምሩ የጠ/ሚ አብይ መንግስት አዋከብነው።ሳይገባን እልል አልን። ሳይገባን አጨበጨብን።ስይገባን ዘፈንለት።ስይገባን ፎከርንለት። ሳይገባን አቅራራን። ሳይገባን በስሙ ማልን።ሳይገባን ወደከነአን ጉዞ ጀመርን ። ሳይገባን እንሆ በስሜት እየተነዳን በምድረበዳው ሲና በረሀ ተበላን”
ኤሎሄ ..እንጠራሀለን አሞፅ 5፥4 ላይ “እኔን ፈልጉ፥በህውትም ትኖራላችሁ” ተብሎ ተፅፎልና አቤቱ አንተን እንፈልጋለን ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያን አስብ።

 

Filed in: Amharic