>

ዘረኝነት ከሰውነት ክብር ሲያጎል...!!! (መስከረም አበራ)

ዘረኝነት ከሰውነት ክብር ሲያጎል…!!!

መስከረም አበራ

እስክንድር ነጋ በአንድ ወቅት “የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ መሪዎች ህዝባችን ሲሉ የኦሮሞ ማለታቸው ነው”ብሎ ነበረ።
ህዝቤ  ላሉት ምን እንደሆኑ  አንዱ ምስክር የዚህችን ሴት ሞት በተመለከተ የአዲስ አበባ መስተዳድር አሻቅቦ  ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የላከው መልዕክት አይሉት ትዕዛዝ ቅጥ የጠፋው ነገር ነው።
በርግጥ በእህታችን አጊቱ ሞት እንደ ሰው ሀዘን ያልተሰማው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም። ነገር ግን
በእነሱ እሣቤ “የእኛ!” ያልሆኑ፤  አልያም ከነገዳቸው ያልሆኑ ወገኖች ደግሞ እንደ ቆሻሻ በግሬደር ተጠርገር በጅምላ ሲቀበሩ የዳር ተመልካች መሆናቸውን ሲታይ…፤
 እዚሁ አገር ቤት ጄኖሳይድ ተፈጽሞባቸው በግፍ የተጨፈጨፉ ዜጎችን በክብር መቅበር ያልቻለ መንግሥት ጋራ ዞሮ ባህር ተሻግሮ ጣልያን ሀገር ለተገደለች አንዲት ሴት ሰውነቷ ሳይሆን ዘሯ ታይቶ አስከሬኗን በክብር ስለማሳረፍ በከንቲባና በምኒስትር መስሪያ ቤት ደረጃ ሲጻጻፉ ስታይ  ዘረኝነታቸው ምን ያህል ከሰውነት እንዳጎደላቸው ትረዳለህ።
 የበፊቱ መሪ ” በአጠቃላይ ወርቅነን”ሲል እነዚህ ደግሞ ለወርቅነታቸው ካራትም ሳይመድቡ አልቀሩም።
 የሚገርመኝ ከዚህ ሁሉ መልስም የኦሮሞ ብልፅግና መሪዎች ሌላውን ሰው ከኢትዮጵያዊነት በመጉደል ሊከሱ መምጣታቸው የማይቀር መሆኑ ነው ።
Filed in: Amharic