አቶ መሀመድ አሊ
‘’..,አማራ መስለው ሰርጎ የገቡ ግለሰቦች አማራ በፐርሰንቴጅ ፣ በጎጥ ፣ በሰፈር እየከፋፈለሉ ልዩነትን አግዝፎ ደጋግሞ በመንገር ደጋግሞ በመስበክ “ልዩነት” በአዕምሮችን ውስጥ አያቃጨለ እንዲኖር አድርገዋል። እኛም አንድ አይደለንም እንዴ እያልን እንወዛገባለን። አንድ ማወቅ ያለብን ጉዳይ አማራ አማራ ነው። ነጭ ፣ቀይ ፣ ቢጫ ወይም ጥቁር አማራ የለም ፤ አንድ ፣ሁለት ፣ሦስት ፣አራት ፣ አምስት አማራ የለም አማራ አንድ ነው ሊለያይም አይችልም ሦስት አራት አማራ እንዳለ አስመስለው ነው በሚዲያ ፣ በግለሰብ ፣ በድርጅት እያደነቆሩ ያሉት እና ይሄ በማህበረሰብ አዕምሮ ውስጥ እንዲሰርፅ አድርገዋል ።የአማራ የህልወና ትግል ሲገባ አስቦበት እና በመዋቅር ተደራጅቶበት አይደለም።የህልውና ትግሉ ጦርነት የጀመረው በድንገት ሁኔታ በፈቀዱት አጋጣሚ ስለሆነ ትግል ላይ እየሆነ እያለ ነው ፋኖ መደራጀት የጀመረው ስለዚህ የፋኖ አደረጃጀቱ በየአካባቢው ነው የተጀመረው። እነዚህን የአካባቢ አደረጃጀቶች ወደአንድ ሴንትራል የጋራ የሆነ ኮማንድ እንዲኖራቸው የሚደረግ ውይይት ነው አሁን እየተደረገ ያለው እንጂ አማራ አንድ ለማድረግ አይደለም። እነዚህን ወይይቶችን ሰፋ አድርገው አማራ እንደተለያየ ፣ እንደተከፋፈለ አድርገው በጣም አጋነው የሚያዩት አሉ ይህ ትክክል አይደለም።
ነጭ ፣ቀይ ፣ ቢጫ ወይም ጥቁር አማራ የለም ፤ አንድ ፣ሁለት ፣ሦስት ፣አራት ፣ አምስት አማራ የለም አማራ አንድ ነው። አማራ አማራ ነው። ‘’

























