የድንግርግር ኮሚሽኑ ውድቀትና የታሪክ ድግግሞሽ !

 

የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ በወቅቱ መለስ ዜናዊ የሚመራውና ራሱን ኢህዴግ ብሎ በህወሓት ጋላቢነት ብአዴን ኦህዴድና ደህዴን በሚባሉ መጋዣዎች ተጋላቢነት አመፁን ለማረጋጋት የተመደበው የፀጥታ ሃይል በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል የሚል አለም አቀፍ ጫና ስለበዛበት ጉዳዬን የሚያጣራ ኮሚሽን በተወካዮች ምክር ቤት ተሾሞ ውጤቱ ከታወቀ ድፍን 20 አመታት ተቆጠሩ።

የዚያን ጊዜ የነበረው ኮሚሽን ልክ እንደ አሁኑ የአብይ አሻንጉሊቶች ለመለስ የገበሩ ቄሶች ሸሆች ፓስተሮችና እግር አጣቢ ዳንኤል ክብረቶች የታጨቁበት ቢሆንም ለህሊናቸው ያደሩ የህዝብን እልቂት መካድ ያልፈለጉ ሁለት ኢትዬጲያውያን ከመሐል ሾልከው መረጃውን ይዞ እስከመሸሸ ደርሰዋል ።እነዚህ ታረክ በየዘመኑ የሚተረክላቸው ሁለት ግለሰቦች ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል (አሁን በአሜሪካ የሚኖሩና ) ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ (በኔዘርላንድ የሚኖሩ) ሲሆን በወቅቱ የመለስ ዜናዊ ማንበብና መፃፍ እንኳን የማይችለው የአጋዚ ልዬ ገዳይ ሃይል የ 14 አመቱን ህፃን ነብዩ ሳሙኤልን ጨምሮ ከ 200 በላይ የአዲስ አባባ ንፁሐንን የጨፈጨፉበት እንዲሁም በመላው አገሪቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዬጲያውያንን በግፍ መግደላቸውን ይፋ በማድረግና ባለማድረግ መካከል በተነሳ የውሳኔ አቋም ልዬነት አብዛኞቹ የኮሚሽን አባላት መለስ ዜናዊን ነፃ ለማውጣት ሲንደፋደፉ ሁለቱ የህግና የህሊና ሰዎች ግን “እውነትን አንሸፍንም”ብለው ሃገር እስከመልቀቅ ደርሰዋል ።እናመሰግናቸዋለን ።

የዚህ ታሪክ መሰል ክስተት መስፍን አርአያ በሚባል የኦህዴድ ካድሬ ከአራት አመት በላይ በድሃ የግብር ገንዘብ አበል እየበላ ሲዝናና ከከረመ በኋላ የኦሮሙማውን አጀንዳ ለማስፈፀም ጊዜው አሁን መሆኑ ታምኖበት በጓዳ ከተመከረ በኋላ 8 አጀንዳዎች እና 4000 ተሳታፊዎች በሚል የኦህዴድ አባላት የሚዘውሩት ንግግር ሳይሆን ድንግርግር ተጀመረ ከተባለ አንድ ሳምንት አለፈው ።የሚገርመው ነገር አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ከኦሮሚያ ክልል የመጡና የሽመልስ አብዲሳ የቀበሌ ካድሬዎች ሲሆኑ የውይይት አጀንዳዎችን ቀደም ሲል መክረውበት በየትኛው ቀን የትኛውን ጉዳይ ማንሳት እንዳለባቸው አቅጣጫ የተሰጠበትም ጉዳይ በመሆኑ አበል ከመቀበል ውጪ ውሳኔዎች ላይ አንዳችም ሚና ያለው ኮሚሽነር ወይንም ተሰብሳቢ የለም ።አሰቂኙ ጉዳይ ደግሞ ተሳታፊዎች በየቦታው ተበታትነው በተለያዩ ጉዳዬች ላይ ጊዜ እንዲያጠፉ በመደረጉ የተኛው ተሳታፊ ከየትኛው ጋር በምን አጀንዳ እንደተመካከረ የሚታወቅ ነገር የለም ።ሁሉም በየማደሪያ ጣቢያው ምግብ እስኪተርፈው ይበላል እስከአሁን ባይሰጣቸውም በቀን ሁለት ሁለት ሺህ ብር ይከፈላል ተብሎ የተገባለትን አበል ውሎ ባደረ ቁጥር እየደመረ የሚተኛ ሥራ አጥ የተሰበሰበበት አዲሱ የአብይ ቲያትር ነው ብለህ ውሰደው?

ለማንኛውም በኦህዴድ በኩል የቀረቡት

1.አብይ አህመድን ወደ ፕሬዚዳንት የመቀየር አጀንዳ
2.አዲስ አበባንና ድሬዳዋን ወደ ኦሮሚያ ክልል መጠቅለል
3.የኢትዮጵያን ሰንደቅ አለማ ቅርፅና የቀለም አቀማመጥ መቀየር የሚሉት ዋና ዋና አጀንዳዎቹን መስፍን አርአያ የሚባለው አድር ባይ ምሁር እንኳን በማያውቅበት ሁኔታ ተወስኖ ስብሰባው በሚጠናቀቅበት እለት የአቋም መግለጫ ሊሰጥበት ከወዲሁ ተዘጋጅቷል ።ከ 11 ወደ 8 ሆድ አደሮች የቀነሰው የድንግርግር ኮሚሸን አባላቱ እርስ በእረስ ተከፋፍለው ከፊሎቹ ለመሸሽ ቢፈልጉም አብይ አህመድ ካልፈቀደ ስለማይወጡ በጭንቀት ተወጥረው መረጃ በየግላቸው ማሾለክ ጀምረዋል ።እውነት እንደ 1998 አይነት ህሊና ያለው ሰው ከመሐል ይወጣ ይሆንን?በቅርቡ የሚሆነውን እናያለን ።

ጎበዝ ነገርን ነገር ያነሳዋል ይባል የለ።የአፋብን አመራር የሆኑ ሁለት ወይንም ሶስት ሰዎች ከድንግርግር ኮሚሽኑ ጋር ይሰበሰቡ ይሆን እንዴ? ደጋ ዳሞት ላይ ንፁሐን አማራዎች ሲጨፈጨፉ መሪ ነን የሚሉት ድምፃቸው ጠፋሳ??

በዚህ የአፋብን የሚባል አመራር ላይ አሁንም ታጋዩ መሪዎችን በአፋጣኝ መርጦ በአዲስ መልክ ማደራጀትና ትግሉን መቋጨት ካልቻለ መጪው የበጋ ወራት ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ ።በግሌ የራሱን የስልጣን ርሃብ ማስታገስ ያልቻለ በተሸናፊነት ሥነ ልቦና እጅ የሰጠ ግለሰብ ወይንም ስብስብ ይህንን ትልቅ አላማ ያለው የህልውና ትግል መርቶ ወንዝ ያሻግራል የሚል ቅዠት የለብኝም ።በዚህ ጉዳይ ምን አይነት አሻጥር ለመፍጠር እየተሞከረ እንደሆነ የትስስር ሰንሰለቱን ጭምር ማጋለጣችንን እንቀጥላለን ።

ዝኒ ከማሁ!
ድል ለአማራ ህዝብ ነፃነት በእውነት ዋጋ ለምተከፍሉልን ፋኖዎቻችን!
ከአዳባይ
ሃምሌ 15/2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.