አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ለምንድነው በጠላት እንዲመታ የተፈለገው ??? አርበኛው በጠላት ኃይል እንዲደመሰስ በእጅጉ የቋመጠው ሰርጎ ገቡ ኃይል ማን ነው?? ስለምንስ አርበኛው እንዲመታ በጽኑ ለመሻት ቻሉ?!
የደጋ ዳሞት ፍልሚያ ቁልጭ አድርጎ ያሳየን በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ሰርጎ የገባ የጠላት ኃይል ሚና ሲፈተሽ!…
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
አማራይቱ ጎጃም ምድር የጀግኖች ሁሉ ጀግኖች መፍለቂያ የሆነቺው ደጋ ዳሞት ዳግም አንጸባራቂ ድል በማስምውዝገብ በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ እጅግ ደማቅ ታሪክ ጽፋለች፣ ፈጽማለች። ቀጠናው ማለትም ደጋ ዳሞት፣ ፈረስ ቤት፣ ጮቄን ጨምሮ በርካታ የወረዳና የዞን ከተሞችን የያዘች የምእራብ ጎጃም ዞን ስር ያለች ሲሆን ከሶስት አመት በፊት በ 2023 ግንቦት ወር ላይ የህልውናው ትግል ሲፈነዳ የክንደ ነበልባሉ ፋኖ እሳት የሆነ ክንድ በጠላታችን ወራሪው ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና ሰራዎት ላይ የማያዳግም እርምጃ ሸመውሰድ የጠላት አከርካሪ የተሰበረበት ልዩ ታሪካዊ ቀጠባ ነው። ይህ እጅግ አስደናቂ የሆነ የውጊያ ብቃትና ታላቅ ጀግነንት የተፈጸመበት የደጋ ዳሞት ፍልሚያ እና ድል በአማራ ፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የመጀመሪያውን እዝ ለመመስረት ያስቻለ አኩሪ የተጋድሎ ትግል የተካሄደበት ቀጠና ነው።
እንደዛሬው የአማራ ፋኖ አደረጃጀት በበርካታ እዞች ከመደራጀቱ በፊት በወርሃ መስከረም ወር 2023 የመጀመሪያው የአማራ ፋኖ እዝ በአርበኛ ሻለቃ ዝናቡ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎጃም ዕዝ የመጀሪያ በመሆን ፈር ቀዳጅ ለመሆን የታቻለው አገዛዙ በገፍ ያጎረፈው ጨፍጫፊ ሰራዊት በጀግኖቹ የአማራ ልጆች በእነ አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ እና ባልደረቦቹ ደጋ ዳሞት ላይ የጠላትን አከርካሪ መስበር ስለተቻለ ነው።
በዚህም ምክንያት ደጋ ዳሞት በጠላት ኃይል በጣም ይፈራል። በጣምም ፍርሃት በወለደው ክብር ይከበራል። የደጋ ዳሞትን አስደናቂ ተጋድሎ ሲዘገብ አንጸባራቂ ኮከብ የሆነው አርበኛ ዝናቡ ልንገረውና ባልደረቦቹ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።
ሰሞኑን አገዛዙ በዚህ ሶስት የትግል አመታት ፈጽሞ ያልሞከረውን የድፍረት ዘመቻ በደጋ ዳሞት ላይ ፈጸመ።
አንዳችም አይነት ወታደራዊ ሳይንስ ሳይማርና በየትኛውም ወታደራዊ ኮሌጅ Military College ( እንደ ሐረር ጦር አካዳሚ አይነት ) ውስጥ ገብቶ ላልሰለጠነው ወጣቱ እና ጀግናው አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረውን ለብቦ ለመድመሰስ አገዛዙ በአራት ጄኔራልና በሰባት ኮሎኔሎች የሚመራ ግዙፍ ሰራዊት በአራት እቅጣጫ በማሰማራት ደጋ ዳሞትን፣ ጮቄን፣ ፈረስ ቤትንና አካባቢው ላይ ያለውን ጠንካራውን የአማራ ፋኖ ቴውድሮስ ዕዝን ደምስሶ ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ሰራዊት በዚህ ክረምት ወር ውስጥ በገፍ እሰማራ።
ይህ በአራት ጄኔራል እና በሰባት ኮሎኔሎች የሚመራው ግዙፍ የጠላት ኃይል በሜካናይዝድ ጦር የታጀበ፣ BM,፣ መድፍ፣ ዙ-23፣ ለቁጥር የሚያታክት ዲሽቃ፣ ባዙቃ እና ስናይፐር የጦር መሳሪያ በመታጠቅ እራሱን በጣም ያጠናከረ ሰራዊት ነው።
አላማውም አገዛዙ በቀጣይ ከትግራይ ጋር ለማድረግ ላቀደው ጦርነት በቅድሚያ ጀርባውን ለማጽዳት ብሎ የከፈተው ዘመቻ ሲሆን በብርቱ ተዋጊነቱ የሚታወቀውን የአማራ ፋኖ ቴውድሮስ ዕዝን ቀድሞ ለመደመሰስ አልሞና አቅዶ የከፈተው ያልተጠበቀ ዘመቻ ነበር።
ያልተጠበቀ ዘመቻ የምልበት ምክንያት በዚህ ሶስት የትግል አመት ውስጥ በሶስቱ የክረምት ወራቶች አጥቂው የአማራ ፋኖ ኃይል እንጂ አገዛዙ ባለመሆኑ የዘንድሮው በወርሃ ሐምሌ የተከፈተው የአገዛዙ የጦርነት ዘመቻ ያልተጠበቀ ዘመቻ ለማለት ችያለሁ።
በአራት ጄኔራልና በሰባት ኮሎኔሎች በአራት አቅጣጫ በደጋ ዳሞት ላይ ያልተጠበቀ ዘመቻ ለከፈተው የጠላት ጥቃት የወገን አጸፌታዊ ምላች ምን ይመስላል???
ጄኔራሎቹ ከአለቃቸው አቢይ አህመድ እና ብርሃኑ ጁላ የተሰጣቸው ተልእኮ በደጋ ዳሞት ያለውን የቴውድሮስን እዝ ሙሉ በሙሉ ደምስሶና መያዝ የተቻለውን አመራር ይዞ ቀጠናውን ከፋኖ ኃይሎች ማጽዳትና የጎጃሙን የአማራ ፋኖ ደምስሶ ጎጃምን የብልጽግና ገባሪ ማደረግ ነበር። እናም በአራት አቅጣጫ ወደ ቀጠናው የተመመው የጠላት ጨፍጫፊ ሰራዊት በታጠቃቸው ከባድ መሳሪያ ታንክ፣ መድፍ፣ ዙ-23፣ ዲሽቃ፣ ባዙቃና መሰል የቡድን መሳሪያ Indiscriminately የሆነ ድብደባ በሁሉም አቅጣጫ ማዝነብ ጀመረ። ይህንን መጠነ ሰፊ የጠላት ኃይልና ያንተጠበቀ ዘመቻን ያዩት እነ አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ እና አርበኛ የመ/አ አበበ በብርሃን ፍጥነት ተዋጊዎቻቸውን በማሰማራት በከበባ ውስጥ አስገብቶ እንደ ገና ዳቦ በአሩር ጥይት ሊያቃጥላቸው በመጣ የጠላት ኃይል ላይ የቆረጣ ስልት በመጠቀም ብርቱ ፍልሚያ ውስጥ ገቡ።
ፍልሚያው ለተከታታይ ቀናት በመቀጠል በፋሺስቱ ሰራዊት አዛዥ ጄኔራሎች በኩል የድል እያደረግን ነው ዜና በስፋት ይሰራጭ ጀመር። ክንደ ነበልባሎቹ ፋኖዎች ግን ለፕሮፖጋንዳው የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት ፋታ የላቸውምና ፍፁሚያውን በፍጹም ቆራጥነትና በአማራዊ ጀግንነት ይህን እስከአፍንጫው ታጥቆ የመጣን የጠላት ግዙፍ ኃይል ይፋለሙ ጀመር።
ደጋ ዳሞት በምእራብ ጎጃም ዞን ስር ያለች ቀጣና ስትሆን በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ያለው የአማራ ፋኖ ቴውድሮስ እዝ ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄና መሰል በህልውና ትግሉ ውስጥ የተሳትፎ ሚና አለን የሚሉ ጋዜጠኞችና አንቂዎች ለእነ አርበኛ ዝናቡ ልንገረው የሚሆን የድጋፍ እርምጃ፣ ኃይል የማሰባሰብ፣ የማሰማራትና ብሎም የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ይከፍታሉ ተብሎ ሲገመት የታየው ዝም ጭጭ ብሎ የጠላትን ያልተጠበቀ ድንገተኛ ወረራን ውጤት ለማየት መጠባበቅ ሆነ።
በምስራቅ ጎጃም ያለው የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ ሰራዊት በእነ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ጥላሁን አበጀ፣ ማርሸት ጸሀዬ እና መሰል የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ አመራሮች የሚመራ ሰራዊት ነው። አስረስ ማረ ዳምጤ የአፋብን ቃለ አቀባይ እና የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ እንደመሆኑ መጠንና አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የአፋብን ምክትል ወታደወራዊ አዛዥና የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ እንደመሆኑ መጠን እናት ድርጅቱ አፋብን እና የዚህ ድርጅት ቃለ አቀባይ የሆነው አስረስ ማረ ዳምጤ በከበባ ላይ ላለው ባልድረባው ድምጽ በመሆን እና የሰው ኃይል በማስተባበር ወገናዊ ድጋፍ ከመስጠት ይልቅ ጸጥ እረጭ ብሎ ዛሬ ነገ አቢይ መራሹ ጨፍጫፊ ሰራዊት በሻላቃ ዝናቡ ልንገረው የሚመራውን ሰራዊት ደጋዳሞት፣ ጮቄና ፈረስ ቤት ላይ ደምስሰን አመራሩን ተቆጣጥረናል የሚልን ዜና ሲያስለፍፍ ለማዳመጥ የቋመጠ ያህል ጽጥ እረጭ ብሎ ድምጹን በማጥፋት የሚከታተል ሰው ሆነ።
እንደ ጦርነቱ ክብደት ፍልሚያው በወገን በኩል ሙሉ ትኩረት አግኝቶ ሽፋን ሲሰጠው ማየትና መስማት ባይችልም በአማራ ፋኖ ቴውድሮስ ዕዝ ደጋፊና ባለቤት ነን፣የዘመነ ካሴ፣ የአስረስ ማረና መሰል ደጋፊና ድምጽ ነን ሲሉ የሚታወቁ ጋዜጠኛ እና አንቂ ነን ተብዬዎች ልክ እንደ አለቃቸው አስረስ ማረ ፍጹም ዝምታን የመረጡ ሲሆን እጅግ ጥቂቶቹ ደግሞ ለምሳሌ በስዊዘርላንድ የምትኖረውና በተሳዳቢነት የምትታወቀው የአስረስ ማረ ጠበቃ የቅዳሜ ገበያ ለእነ ሻለቃ ዝናቡ ድምጽ ከመሆን በእነሻለቃ ዝናቡ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍታ ስትጮህና ስትሳደብ ለማየትና ለመስማት በቅተናል።
ለመሆኑ ይህ ተግባር ምን ማለት እንደሆነ ገብታችሃል??
ማለትም በአራት ጄኔራልና በሰባት ኮ/ሎኔሎች ከሚመራ ግዙፍ የጠላት ኃይል ጋር እየተፋለሙ ካሉት እነ አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ ፣ አርበኛ የመ/አ አበበና ጓደኞቻቸው በብርቱ ፍልሚያ ላይ በሆኑበት ሰዓት የአማራ ፋኖ ቴውድሮስ ዕዝ ደጋፊ ነኝ፣ ድምጽ ነኝ፣ የአስረስ ማረ ጠበቃ ነኝ፣ የማርሸት ጸሀዬ ጠበቃ ነኝ፣ የጥላሁን ድምጽና ጠበቃ ነኝ በማለት የሚታወቁ እነ ቅዳሜ ገበያና መአዛ መሀመድ አይነቱ በዚህ ወሳኝ በሆነ ሰዓት ከድጋፍ ይልቅ በአርበኞቹ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲከፍቱ ማየት ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ ተረድታችሃልን???
ከወራት በፊት አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የተመስገን ጥሩነህ እህት ልጅ የሆነውን ማርሸት ጸሀዬን በስነምግባር ጥሰት ለጥቂት ቀናት አስሮት እንደነበረ የሚታወስ ነው። በወቅቱ የተመስገን ጥሩነህ አጎት ልጅ የሆነው አስረስ ማረ ዳምጤ፣ የቅዳሜ ገበያና መሰል የሆኑ ግለሰቦች ለማርሸት ጸሀዬ ጥብቅና በመቆም በአርበኛው ላይ ዘመቻ ሲያደርጉ መታዘባችን አይዘነጋም።
ከወራት ቆይታ በኃላ አርበኛ ሻለቃ ዝናቡ፣ አርበኛ የመ/አ አበበና ባልደረቦቻቸው ይጥፉ ተብሎ የተወሰነ ይመስል ጀግኖቹ በፍልሚያ ላይ ባሉበት ወቅት ወረራውን ድምጻቸውን በማጥፋት ከመደገፍ አልፈው የጠላት ኃይል በጀግኖቻችን መመታትና መበታተን ሲጀምር ደግሞ አደባባይ ብቅ ብለው በውጊያ ላይ ያሉትን አርበኞች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲከፍቱ ማየት ከዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ጀርባ የእነዚህ ሰዎች እጅ አለበት ብሎ አንድ ሰው ቢገምት ተሳስተሀል ለማለት ይቸግረናል።
መደምደሚያ
በአራት ጄኔራልና በሰባት ኮሎኔሎች በአራት አቅጣጫ ወደ ደጋ ዳሞት፣ ጮቄ፣ ፈረስ ቤትና አከባቢው የገባው የጠላት ሰራዊት ያቀደውን እቅድ አንዱንም ሳያሳካ በቆራጥና በአይበገሬዎቹ ልጆቻችንን ክፉኛ እየተለበለበ ብርቱ ዋጋ በመክፈል የዘመቻው አላማ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ቢሆንም አይናችንን የገለጠ ድርጊቶችንም ሊያሳየን ችላል።
እነዚህ መታረም፣ መስተካከልና ምላሽ ሊሰጣቸው የሚገቡ ወሳኝ ክፍተቶችም:-
📌- 1ኛ- ድርጅቱ አፋብን የተሰጠውንም ይሁን በእጁ ያስገባውን ኃላፊነት ያልተወጣ ድርጅት መሆኑን
📌- 2ኛ- የድርጅቱ አፋብን ቃለ አቀባይ እና የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው – አስረስ ማረ ዳምጤ ኃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት ብቻ ሳይሆን ለአርበኞቹ ድጋፍ እንዳይደርስ በር ዘግቶ ጸጥ ያለ ሰው መሆኑ
📌- 3ኛ- በምስራቅ ጎጃም ያለው የአማራ ፋኖ ቴውድሮስ ዕዝ ተዋጊ ሰራዊት በመሪዎቹ ተጽእኖ ስር ወድቆ ድምጹን አጥፍቶ ዝም ማለቱ
📌-4ኛ- መላው የአማራ ፋኖ፣ መላው የአማራ ጋዜጠኛ፣ አንቂና መላው የአማራ ሕዝብ መረባረብ በሚገባው መልኩ መረባረብ ባለመቻሉ ትልቅ ክፍተት መኖሩን የደጋ ዳሞት ፍልሚያ ያሳየን ክፍተት ሲሆን በአንጻሩም ጀግኖቻችን ግን በዚህ ሁሉ ተጽእኖ ውስጥ ሆነው እስከ አፍንጫው ድረስ ታጥቆ የመጣን የጠላት ዘመቻን በታላቅ ጀግንነት ተፋልመው ድል በማድረጋቸው የአማራን ፋኖ አይበገሬነትን ዳግም ደጋ ዳሞት ላይ ያረጋገጥንበት ፍልሚያ አድርገውታል። አበቃሁ።
























