ራሱን “ጥምዶ” እያለ ከህወሓት ጉያ ስራ ሲጥመለመል የከረመው የዘመነ ካሴና ምሬ ወዳጆ ቡድን ከአማራ ፋኖ አላማ ውጪ በሆነ መንገድ የጋራ ኮሚቴ በማዋቀር የአብይ አህመድን አገዛዝ በጋራ መጣል የሚል ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም አፈፃፀሙ ግልፅነት የጎደለው ፋኖ የማያውቀውና የአፋብን አመራር ብቻ እንዲያውቀው የተወሰነ ቢሆንም አፋብን ተቀባይነት በማጣቱ አመራሩ የህወሃት አሸከር ወደ መሆን ተቀይሯል ።
በመሆኑም
1.አሁን ጥምዶ የሚባለው ስያሜ በሙሉ ጠፍቶ የአፋብንን አመራር ጭምር የሚያዘው የህወሀት ሥራ አስፈፃሚ እንዲሆን ተደርጓል ።ለዚህም ዋናው መንስኤ እነ ዘመነ ጉዳዩን በድብቅ እንዲከናወን አድርገው ቀድመው በመሸነፋቸው ምክንያት ነው።ስለዚህ ፅምዶ ወይንም ጥምዶ በተግባር የለም
2.የህወሃትን አላማ የማይደግፉ ፋኖዎችና የፋኖ አመራሮች በሙሉ እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ትጥቅ እንዲፈቱና እንዲረሸኑ ከመቀሌ ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ።የአፋብን አመራርም ይህን ተቀብሎ ለመተግበር እየሞከረ ነው ።ለምሳሌ በቤተ አምሐራ በበለጠ ሸጋው መሪነት ወደ 20 የሚጠጉ እንቁ የፋኖ መሪዎችን ሰብስቦ ትጥቅ እንዲያስረክቡ የራያን አካባቢ በሙሉ ለህወሃት እንዲለቁና የሚረሸኑ አመራሮችንም እሱ ለሚመራው ገዳይ ቡድን እንዲያስረክቡ መመሪያ አስተላልፏል ።
3.በጎንደር ፋኖ መካከል ከፍተኛ ልዬነት እንዲፈጠር ከመቀሌ በተላለፈው መመሪያ መሰረት እነ ሳሙኤል ባለድልና ጀነራል ተዘራን ጨምሮ ከወልቃይት ዘብ ጋር የተጋጨ አላማ ያላቸው በማስመሰል እርስ በእርሰ እንዲመታቱ በከፍተኛ በጀት የሚመራ ከፋፋይ ቡድን የተመደበ ሲሆን ይኸው ቡድን በየቀኑ የጎንደር ፋኖን ልዬነት የበለጠ የሚያወሳስብ አጀንዳ በየሚዲያው ጭምር እንዲሰራጭ ትዕዛዝ የተሰጠ ሰለሆነ ጎንደር ችግርህን በጥበብ ለመፍታት ሞክር
4.የሸዋ ፋኖ ለቤተመንግስቱም ቅርብ ከመሆኑ ባሻገር የህወሃትን አላማ ለማስፈፀም አሰቸጋሪ መሆኑ ታምኖበት የሎጂስቲክስ እጥረት እንዲፈጠር ሆነ ተብሎ እየተሰራ ሲሆን ይህ ውሳኔ ሲወሰን ዘመነ ካሴ ምሬ ወዳጆና ሄኖክ አዲሴ እዛው መቀሌ አብረው መወሰናቸውን ሁሉም ፋኖ ይወቀው።
5.አሁን በህወሓት መሪነት የተጀመረው ዉጊያ በዋናነት ከአብይ አህመድ ጋር ይምሰል እንጂ ወያኔ ወደ መሐል ሃገር ይዞታዋን በማስፋፋትና ይቃወማሉ የሚባሉትን የፋኖ ሃይሎች በመበታተን ወልቃይትና ራያን ያለ አንዳች ተቀናቃኝ መቆጣጠር ከዛም ከአብይ አህመድ ጋር ወደ ፕሪቶሪያ ስምምነት መመለስ ብቻ መሆኑን አማራ በሙሉ አውቀህ ሚናህን ለይ?
ምን እናድርግ
ሀ.በአምስቱም የፋኖ እዝ ያለህ እውነተኛ የአማራ ህልውና የሚያንገበግብህ ሁሉ የውስጥ ምክክር አድርግ።አፋብን የሚባል ድርጅትም ንቅናቄም እንደሌለ አውቀህ ከየእዙ 10 ሰዎችን መርጠህ የጋራ ምክር ቤት መስርት
2.የአፋብንን መፍረስ በይፋ ለህዝቡም ለታጋዩም አሳውቆ አዲሱ የፋኖ ምክር ቤት ከታጋዮች ጋር እየመከረ መሪዎችን ይምረጥ።
3.የአፋብን መሪ ነኝ እያለ ስብሰባ ወይንም ምክክር ብሎ ሲጠራችሁ ትጥቅ ለማስፈታትና ለመግደል ወይንም ወደ መቀሌ ወስዶ ባዶ ስድስት ሊያሰቃያችሁ መሆኑን አውቃችሁ የተጠና መልስ ስጡ
5.የመቀሌው የአፋብን አመራር በዚህ ክረምት መደበኛ ሥራው የህወሃትን እቅድ ማስፈፀም ብቻ መሆኑን አምናችሁ በራሳችሁ መሥራት የምትችሉትን ለማድረግ ብቻ ታገሉ?
6.አፋብን ከመመሥረቱ በፊትም አሁንም አማራውን ለህወሀት ለማከራየትና መከራውን ለማራዘም በስልጣን ርሃብተኞች የሚመራ አቅመ ቢስ ንቅናቄ ከመሆኑም በላይ በሌሎች መመሪያ ሰጭነት የተመሰረተ ባዕድ ሰብስብ መሆኑን ሁሉም አማራ ተረድቶ ለእውነተኛ ታጋዬች ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቅ እፈልጋለሁ ።
ዝኒ ከማሁ
ከአዳባይ
ሐምሌ 29/2018





















