ከእንግዲህ ጠብመንጃ የሚሸከም አማራ የለም!

 

ከአዳባይ

መሰንበት ደግ ነውና እንዴት ሰነበታችሁ።እኔማ በብርድና በድርቅ መካከል በሚወረወረው የሴራ ፓለቲካ ተቸንክሬ ላለመቅረት ሰል ጥግ ይዤ እየተከታተልኩ ሰነበትኩ።እነዚህ እኛ ካልመራነው አማራ ነፃ አይወጣም ብለው ከክላሽ ተኩስ ይልቅ የግል ሸሚዛቸውን ተኩስ በፎቶግራፍ ሲያስኮመኩሙን የነበሩ ግብስብሶች ከአስር ሚሊዮን በላይ ያለቀበትን የሃምሳ አመታት መሰዋእትነት ለዋናው የግድያ መፈናቀል መሰደድድና ዘር ማጥፋት ጠንሳሽ ለሆነው ወያኔ ሊሸጡን መስማማታቸውን ቆመን አደመጥን።አጃኢብ ነው ጎበዝ።በመጀመሪያ የፋኖ ትግል ሲጀመር አይሆንም እኛ የሰላማዊ ትግል ነጭ እርግቦች ነን ብለው ሲሽከረከሩ ከከረሙ በኋላ በዘመዶቻቸው የብአዴን ካድሬዎች ሃላፊነት ተመድበው የነፃነት ታጋይነት ከእኛ በላይ ጋንዲም ማንዴላም አይደርሱብንም ብለውን መንገድ እየዘጉ ጠንካራ የአማራ ታጋዬችን በመግደል የትግሉን መስመር ለማስለወጥ ሲጋጋጡ ደም እየተገበረ እሰከ አፋህድ መመስረት ተደረሰ ።በተለመደው የእኛ ሙሴነት አባዜያቸው መሪ ካልሆንን ብለው የተመሰረተውን ድርጅት ለማፍረስ ከአማራ ጠላቶች በላይ ተንቀሳቅሰው በውስጥ ሰርጎ ገብ ባንዳዎችና በዲያስፖራ ባሰባሰቧቸው መርዘኛ የመንጋ ስብስብ አፋህድን አፍርሰው አማራን ድርጅት አልባ ትግል ውስጥ በመክተት ህዝቡን ሃዘን ውስጥ ከተቱት።እነዚህ እራሳቸውን እንኳን መምራት የማይችሉ የተለጣፊነት በሸታ ያለባቸው ግለሰቦች በአደጉበት የሁለተኝነት ሥነ ልቦና ተጠልፈው ህውሃት ፈጣሪያችን እባክሽ የአራት ኪሎ መንገድን አሳይን ብለው ወደኋላ ወላጃቸው ጉያ ተወሸቁ ።ይህ ሁሉ ድራማ ሲከወን ሰባ ሚሊዮን አማራ በሚሊዮን የሚቆጠረው የፋኖ ታጋይና አሸናፊው ሲለይ ወደ መድረክ ብቅ የሚለው የአማራ ልሂቅ እጁን አገጩ ላይ ለጥፎ እንደ ኦቴሎ ቲያትር ይመለከታል ።እነዚህ እራሳቸውን በህወሃትና በእነ ሻለቃ ዳዊት አሰባሳቢነት ጠፍጥፈው አፋብን ብለው የመጡ ግራ የገባው ስብስብ አባላት እድሜ ካገኙ “አማራን የፈጠርነው እኛ ነን “ብለው መግለጫ እንደሚሰጡ ባለፉት ሰባት ወራት ከመጡበት ማንነታቸው ተነስቶ መተንበይ ይቻላል ።

በነገራችን ላይ ሻለቃ ዳዊትና ሌሎችም የአፋብንን መስራቾች አንድነት ለስኬት (UNITY FOR SUCCESS ) የሚባል የአማራን ህዝብ ወክሎ በሽግግሩ የሚወከል አዲስ ድርጅት በማቋቋም ላይ ሰለሆኑ አፋብን ላይ የተሰቀላችሁ እንዳትወድቁ ቀስ ብላችሁ ውረዱ?

የአንድነት ለስኬት ድርጅትን በተመለከተ የስልጣን ክፍፍሉ እንዳለቀ በስፋት እንመጣበታለን ።ለማንኛውም ከአፋብን አመራሮች ውስጥም በዚህ ድርጅት ውስጥ የሚካተት ስለሚኖር በውሰጠ ታዋቂነት (bY default ) አፋብን የለም ለማለት ነው ።በመሬት ያሉት አምስት እዞች የሚታገሉት በየራሳቸው መንገድ ሲሆን ህወሃት ለአፋብን በሰጠቺው መመሪያ መሰረት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ሎጂስቲክስ እንዳይደርሰው የቤተአምሐራ ፋኖ በሁለት ተከፍሎ ጥምዶን የማይደግፍ ከጠቅላይ ግዛቱ ለቆ በተለይም ራያና አካባቢዎች እንዲሁም የሰሜን ቤተአምሐራ (ወሎ) አካባቢ ለህወሃት ሰራዊት እንዲለቀቁ በተወሰነው መሰረት የሚባረሩትን አስወጥተው የሚታሰሩትን አስረዋል ።
የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ፋኖን በከፊል የጥምዶ ተገዢ ለማድረግ በአፋብን ሰብሳቢና ቃል አቀባይ በኩል የጥርነፋ ሥራው በአብዛኛው ያለቀ ሲሆን ይህንን የሚቃወም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ ተሰጥቷል ።የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ፋኖን በተመለከተ ከወልቃይት ዘብ ጋር በማጣላትና ከፋፍሎ በመምታት አቅሙን አዳክሞ ወያኔ በቀላሉ ከሰሜን ወሎ ወደ ጎንደር ፊቷን አዙራ እንድትወጋ ስምምነት የተደረሰው አፋብን በሚባለው አዲሱ የህወሃት ደሳለኝ (ዕቃ ተሸካሚ አህያ) መሆኑን አምኖ መቀበል ያስፈልጋል ።ለነገሩ ይህ ሰብስብ አማራን ለዳግም ባርነት እያስማማ ነው ።አማራ በጊዜ ተደረጅተህ እውነተኛውን ፋኖ ደግፍ ብዬ ስንት ማስታወሻ አጋራሁ።ወፍ የለም ።

እኔ የምለው የአማራ ዲያስፓራ የስደት ሃገር ውስጥ ዘላለማዊ የሆነ ጥገኝነት ይኖራል በሎ ነው ወይንስ በአመት ሁለት ጊዜ አዲስ አበባ መሄዱ እንዳይቀርበት ይሆን ጆሮ ዳባ ብሎ የሚተኛው ።ወገኔ አለም እየጠበበች ህዝብ እየበዛ የተፈጥሮ ሃብት እያለቀ ሲሄድ ሁሉም ሃገር እንደ ደቡብ አፍሪካ ቀን ቆርጦ ይጭንሃል።ካላመንክ የትራንፕን እንቅስቃሴ እየውና ወደፊት አምስት አመት ጨምረህ የሚሆነውን አስላው።በሌላ አባባል ሃገር ያስፈልግሃል እያልኩህ ነው!

ወደ ፋኖ ትግል ሰንመለስ አሁን ያለው ሁኔታ በሁለት ዘርፍ ሊታይ የሚችል ሲሆን ወደ 5% የሚሆነው ብቻ በውዴታም በግዴታም የህወሃትን መጣመር የሚደግፍ ሲሆን ሌላውና ግዙፉ ሃይል ቤተሰቡን እየገደለች ንብረቱን እየቀማች አማራ ጠላት ነው ብላ ማንፊስቶና ህገ አራዊት ይዛ ዳግም የወልቃይትና ራያን ህዝብ በመጨፍጨፍ አማራን ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከምተሰራው የአፋብን ወላጅ ህወሃት ጋር በምንም መንገድ ተጣምሮ አይታገልም ።አማራው ደግፍና ለውጤት አብቃው የምልህ ይህን ግዙፍ ሃይል ነው ።መቼም ነገርን ነገር ያነሳው የለ አፋብን ከተጣመረው የህወሓት ሃይል ውስጥ አርሚ70 የሚባለው በማይካድራ በአንድ ቀን 1600 አማራውያንን ያረደው ሳምሪ ቡድን ሲሆን የህወሃት ጦር መሪው ደግሞ የሳምሪን ጭፍጨፋ የመራው ጀነራል ነው ።ጉድበል ጎንደር አትሉም ። ሌላኛው የአፋብን ተጣማሪ ባለፋት ስምንት የሰቆቃ አመታት በመላው ኦሮሚያ በተለይም በወለጋ በአንድ ቀን 3500 የቶሌ ቀበሌ አማራውያን እንደ ዶሮ ሲታረዱ ከሽመልስ አብዲሳ ጋር በመተባበር (ኦሮሚያን ከአማራ ነፃ ማድረግ) በሚለው የውስጥ ሰምምነት መሰረት ዘግናኝ እልቂት የፈፀመው ራሱን የኦሮሞ ሰራዊት(OLA) ከቤተመንግስቱ በተቀመጠው ሰልጣንን በተዘዋዋሪ የማስጠበቅ ሰሌት መሰረት የጥምረቱ አካል ነው አልሃለሁ።እናም አፋብን የተጣመረው ከህወሃትና ከብልፅግና ጋር ነው።

ሌላው የአፋብን የውጪው ሚዲያ ዬቲዩብ ተቀላቢዎች የሚያነሱት ሙግት እናስ አማራ ከህወሓት ካልተጣመረ በጦርነት ውስጥ ልታቆዩት ነውን ይላሉ ።ቀጠል አድርገውም የአማራና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ብለው እንደ ህፃን አመክንዮ አልባ ትንተና ይነግሩናል ።በመሰረቱ ፋኖ ራሱ በውስጡ ጠንካራ አንድነት መፍጠር እንዳይችል ዋናው እንቅፋት የአፋብን አመራር ነው ።ይህም ሆን ተብሎ ከፋፍሎ የአማራን ትግል የመበታተን የህወሃትና የኦነግ(ኦህዴድ )ስሌት አካል ነው ።በሌላ መልኩ ኢትዬጲያ የ86 ዘውጋዊ ማንነት ያላቸው ህዝቦች ሃገር በመሆኗ መገንጠልን ከሚቃወሙት የአማራን ቀይ መስመር ከሚቀበሉትና በአማራ ደም እጃቸው ካልጨቀዩ ኢትዮጵያዊ ሃይሎች ጋር አብሮ መስራትን ማንም አልተቃወመም ።አይቃወምም ። የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚፈጠረው እንደ ህወሃትና ኦነግ ባሉ የአማራን ህዝብ ያረዱ ተገንጣዮች ጋር ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ነፃ የውይይት መድረክ ሲፈጠር እሱም ከትጥቅ ትግል ማግስት የሚሰራ ባለቤት ያለው ሰለሆነ የአፋብን ኮዳዎች አታደናግሩን።

የዛሬውን ለማጠቃለል አሁን በሚሊዮን የሚቆጠር የሰለጠነ የአማራ ታጋይ አለን።ሁሉም አማራ ጠላቱን ለይቶ ተረድቶ ካላሸነፈ በህይወት መኖር እንደማይችል ተረድቶ ለህልውናው ተነስቷል ።በህወሃትና አብይ አህመድ መኖሪያ ቀየውና ሃብት ንብረቱ ወድሞ የሚጠለልበት የሰላም ቀጠና እንደሌለው አምኖ ዱር ቤቴ ብሏል።ቤተክርስቲያን ወይንም መስጂድ ሄዶ ፈጣሪውን እንዳያመልክ ተቋማቶቹ ሲቃጠሉ ሲዘረፋ ገዳማቱ በድሮን ሲወድሙ ተመልክቶ ዳዊቱን በጋራ ጠብመንጃውን በቀኝ ሸክፎ ለነፃነት ቆርጧልና እንደ ትናንት ከትናንት በስተያ

ጠብመንጃ ተሸክሞ አፈ ጮሌዎችን ቤተመንግሥት አስገብቶ የሚመለስ አማራ የለምና እንደ መዥገር የተጣበቃችሁ አማራ መሳይ ባንዳዎች ከትግላችን ገለል በሉ።እንላለን ።
ዝኒ ከማሁ!
ነሐሴ 9/2018
አፋብን ዛሬ ሰባት ወር ሞላው !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.