አፋብንና የዲያስፖራ ፓለቲካ

ከአዳባይ

አብይ አህመድንና ህወሓትን የመሰለ ፀረ ሃገርና ህዝብ አጥፊ ተገንጣዮች እንደ ኦነግ ያሉ ብዙ ኦነጎች ባሉበት እንደ አፋብን ያለ ፊትም ኋላም ለይቶ የማያውቅ የፓለቲካ ክሱራን ሃገሬንና ወገኔን እያወደመ ባለበት “ሰላም ናችሁ “ብዬ መጀመር በሰላም መቀለድ ወይንም ሙፈሪያት ካሚልን የሆንኩ ያህል ሰለሚከብደኝ ሰላም በሌለበት የኢትዮጵያ ምድር ሰላም ናችሁ አልልም ።
ሰሞነኛው የትብብር ወይንም የጥምዶ ፓተሊካ በአየር ላይ እየተነነ ሲመጣ የአሮጌው ኢህአዴግ አብዬታውያን ለመንጋው አጫጫር ድራማ እየሰሩ ያከፋፍሉታል።ከአንድ ወር በፊት አንድ ብን ብሎ የጠፋው የአ..ብን ፓርላማ ተወካይ የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ በታክሲ ሊጋፉ ሰለሆነ ህዘብ ህዝብ እንዳይሸቱ መኪና ይገዛላቸው ሲል የኡጋንዳ ወኪላቸው ምራቁን መሰብሰብ አቅቶት ጭምር ሃዘኑን ሲገልጥ ታዝበን አለፍነው።አማራ እንኳን መኪና ለሌለው ግለሰብ አይደለም በተከታታይ አመታት በጦርነት ምክንያት ባቄላ ዘርቶ ልጆቹን መመገብ ባልቻለበት ሁኔታ ሰለ ግለሰቦች ፕሮቶኮል የሚጨነቁ አስመሳይ ሸቃዬችን ከመንገድ ላይ ዘወር ማድረግ ተገቢ ነበር።ግን ብዙ የጥቅም ተጋሪነት ሰላለበት ልክ ነህ በርታ ጀግናው ምና ምን እየተባለ በአማራ ስም ትወና ይከናወናል ።እነዚህ አስመሳይ ግለሰቦች ስለፓርላማ ተወካዩ መኪና ማጣት ሲቆጩ አብይ አህመድ በአማራነታቸው ለይቶ ለማጥፋት በየማጎሪያ መጋዘን ውስጥ ለሚሰቃዬት ወገኖቻቸው ስንት ቀን ዳቦ ገዝተውላቸው ይሆን?

እነዚህ የሚዲያ ላይ አርበኞች የእውነት ለአማራ የሚጨነቁ ከሆነ የከፊ ልጆችን የኮሎኔል ታደሰን የደምስ ይመርን የአበባውንና የእነ እሸቴ ሞገሰን ቤተሰቦች የት ናችሁ ብለው ስንት ጊዜ አስታውሰው ይሆን?.ጉራ ብቻ አለ ቴዲ አፍሮ
ሌላኛው የዚህ ሳምንት የመንጋ ፓለቲካ ጥምረቱ በአደባባይ እየፈረሰ ሲመጣ ደራሲዎቹና ዋና አዘጋጁ አንዳርጋቸው ፅጌ ያከፋፈሉት አጀንዳ ነው ።ይህ አጀንዳ በህወሃትና በአንዳርጋቸው ፅጌ መካከል የሃሳብ ልዬነት እንደተፈጠረ ተደርጎ አየሩን በክሎታል።ሽመልስ አብዲሳ የ confuse and convince ፓለቲካን የተማረው የጌታቸው ረዳን ኮት ጭምር ተውሶ በለበሰው የህወሃት ፓለቲካ መሆኑን የረሳው መንጋ ዋናውን የኢህአዴግ ሰው አንዳርጋቸው ፅጌን የህወሃትን ሚስጥር ያወጣው ሰለተጣሉ ነው ብሎ እንደመጃጃል የሚያስቅ ፓለቲካ የለም።ይልቅ የፋኖ ሰራዊትና የአርበኛ እስክንድር ነጋን ቃለ መጠይቅ መርምርና ጥምዶ በማይድን በሽታ መያዙን አውቀህ የትግል አሻጋሪ መፍተሔ ላይ ድከም።እናንተ ዲያስፖራው ግን የአፋብን አፈ ቀላጤ እንዳለው”ንቅል” ነው እንዴ? ገዱ አንዳርጋቸው የገራዥ ሃላፊ (supervisor ) ሆኖ መስራቱ ያንስበታል እና አንድ ቤት ቢጤ ኤንግዛለት የሚለው ዲያስፖራ አላስደነቃችሁም??.ገዱ በእውነት የአማራ ህዝብ ወዳጅ ወይንስ ጠላት የሚለው አጀንዳ ይቆይና በሰላሳ አመታት የስልጣን ዘመኑ በሃገር ቤትም በውጪም ያፈራውን ሃብት መንጋው ያውቃልን?በማን ገንዘብ ላለፋት ሁለት አመታት ቁጭ ብሎ ተማረ ማን ቤት ሰጠው ልጆቹ የት ነው የተማሩት?በሃገር ቤት በፀደይ ባንክ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆኑን እናውቅ ይሆን?በአማራ ባንክ በአማራ ብድርና ቁጠባ በእርሻ በሪል ሰቴትና በበርካታ ንግዶች ውስጥ በተለያዩ ሰዎች ስም ያለውን ሃብት እናውቅ ይሆን ?በአሁኑ ሰአት ከህውሃት ገንዘብ አቀባባይ ከሆነው የሞንጀሪኖ ወንድምና ሲሳይ ሳተናው ከሚባል የጎንደር ፋኖዎችን ከብልፅግና ተልዕኮ እየተቀበለ ከሚያገዳድል የደቡብ ተወላጅ ካድሬ ጋር በመመሳጠር ምን አይነት ከፋፋይ ሥራ እየሰራ እንደሆነ አማራ ያውቃልን ??ገዱ ድሃ ከሆነ ኤለን መስክም ድሃ ነውና በነካ እጃችሁ Go fund me ክፈቱለት።

ወደ ዋናው ጉዳይ እንምጣ?ይህ ሁሉ ጨዋታ አንድን ያፈጠጠ እውነት ለመሸፋፋን የተሰራ ተመልካች አልቦ ድራማ ነው ።ይህን ድራማ ቀደም ሲል ባቀረብኩት ተደጋጋሚ ማስታወሻ ላይ እንደገለፅኩት በዚህ ክረምት የአማራ ትግል ወደፊት እንዳይስፈነጠር በአፋብን በኩል አስሮ መያዝና ህወሃትን ወደ ፊት የማምጣት ሥራ ተሰርቶ ተጠናቋል ።

1.የአፋብን ውስን ግለሰቦች ጥምዶን ፈጠርን በማለት ህወሃትን አባት አድርገው በማሳየት ከአብይ አህመድ ጋር ድርድር እንድትቀመጥ በር ተከፍቶላታል።ለዚህም ኦቢሴንጎ ኦባሳንጆ ሰሞኑን መቀሌ ከርሟል ።

2.የፋኖን ትግል ለህወሓት ያከራየው የአፋብን አመራር ኦባሳንጆና ደብረጽዮን ሲነጋገሩ አራት አመራሮች እንደ ዕቃ ተቀምጠው ተሳትፈዋል ።እነሱም ዘመነ ካሴ ብሩክ ሰለሺ ሄኖክ አዲሴና አሰቻለው የሚባሉ ሲሆኑ ምሬ ወዳጆ የቋንቋ እጥረት አለበት ተብሎ ሰብሰባው ላይ አልተገኘም ።ይህ ውይይት በአፋብን ጊዜያዊ ሰብሳቢ ውሳኔ የተከናወነ ሲሆን ሌሎች የሥራ አስፈፃሚዎች አልተነገራቸውም ።ተሳታፊዎቹም የአማራን ህልውና ትግል በተመለከተ ምንም አጀንዳ በዝርዝር አቅርበው አላስረዱም ።

3.በቤተ አመሓራ ያለው አብዛኛው የራያና ሰሜን ወሎ አካባቢ የፋኖ ነፃ ቀጠና ለህወሃት እንዲሰጥ ምሬ ወዳጆ ድርሳን ብርሃኔና በለጠ ሸጋው በወሰኑት መሰረት ፋኖ ወደ ሌላ ቦታ ተሸጋሽጎ ለህወሃት የተባለውን ቀጠና የአብይ አህመድ ሚሊሻ እየሰፈረበት ይገኛል ።ይህንን የተቃወሙ የምኒልክ ዕዝ አመራሮችና አባላት ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እስከ መታሰር የሚደርስ ቅጣት እየተጣለባቸው ሲሆን አንድ ጀግና አዲግራት ተወስዶ በህወሓት ወታደሮች እየተሰቃየ ይገኛል ።ይህን ጀግና የፋኖ መሪ በአስቸኳይ የማይለቀቅ ከሆነ በፎቶግራፍና በስሙ ለህዝብ ይፋ እናደርገዋለን ።በቃልና በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ጊዜ የሚጠብቁ የምኒልክ ዕዝ ፋኖዎችም እንዳሉ አረጋግጠናል ።ይህ ሁሉ ሴራ የምኒልክ ዕዝን በመበተን የበተ አምሓራን መሬት ሙሉ በሙሉ በህወሓት ስር አሰገብቶ ወደ ወልቃይት ወረራ ለማድረግ የሚሰራ ግልጽ አሽከርነት ስለሆነ ዕዙ የአማራ በደል የገባቸውን አመራሮች ለመመደብ መፍጠን ይኖርበታል ።

4.የጎንደርን ፋኖ አንድነት ለመበታተን እና ዋና ዋና መሪዎቹን ለማስመታት ከአብይ አህመድ ሲሳይ ሳተናው የሚባል ለስለላ ፋኖ የሆነ ፀረ አማራ ካድሬ እነ ሞንጀሪኖ ከህወሃት እንዲሁም አፋብን ውስጥ የሚገኝ አንድ የበላይ ዕዝ ተወካይን በመያዝ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከዲያስፖራው ጭምር የተወከሉ ሰዎች እየበተኑ ሰለሆነ የበላይ ዕዝ መሪዎችና ታጋዬች አሁንም ያደፈጡ ባንዳዎችን በመከታተል ራሳችሁን ከተገዙ ይሁዳዎች ጠብቁ እላለሁ ።የአማራ ትግል ጊዜ ይረዝም ይሆናል እንጂ ጠላቶቹን ቀብሮ ያብባል !!!

ዝኒ ከማሁ!
ነሐሴ 20/2018

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.