ዶ/ር አበባ ፍቃደ
“ጩኸቴን ቀሙኝ ትብበሩን የሚቃወም ብልጽግና ናቸው” አሉ። ከዚህ በፊት ግንቦት 7 የሚቃወም ወያኔ ኢህአዴግ ናቸው ያሉን ተዋናዮች!’’
ፅምዶን ወይም ትብብሩን ስትቃወም የሚሰጡህ ምላሽ፦
➡️ትብብሩን የሚቃወሙ ብልጽግና ናቸው
➡️አማራ ብቻውን ማሸነፍ አይችልም
➡️ፓለቲካ አያውቁም stupid ናቸው።
➡️ከወያኔ እና ከኦነግ ጋር ከመተባበር ውጪ አማራጭ የለም
ለ30ዓመት በላይ ተመሳሳይ ተዋናይ ተመሳሳይ ቃላት እና ተመሳሳይ መልስ!
አማራጭ የለምእና አብይን ማስወገድ ብቻ ነው። ይሄ ቅድም ያልኩት የስታሚና (Stamina) መላላት የማሰብ የጥልቅ አሳቢነትና አስተዋይነትን በዚህ በዝም ብሎ obvious በሆኑ ነገሮች አሉ አይደል? እናውቃለን ይሄ አሁን መደረግ ያለበት እሱን ማስወገድ ነው። ህዝቡ ሰላም እንዲያገኝ ነው። ይሄ በሙሉ የሰው ልጅ የሚፈልገው ነው። የሚነገርም አልነበረም። ግን ይሄ ለላላው ፈርታይል ግራውንድ (Fertile Ground) ለሆነው ለመሰበከያ ምቹ ነው።
ለጓጓው ኢትዮጵያዊ ኦፍ ኮርስ (Of Course) ሰላም እንፈልጋለን። አንድም ቀን ጥይት ሳይተኮሱ በሜዳ ላይ የምናያቸው በፋኖ ስር ያሉ ወጣቶች አንጀቴን ነው የሚበሉት። ባየሁት ጊዜ ነጻነታቸውን አስከብረው የሃገራቸው ባለቤት እንዲሆኑ እንዲበቁ ነው ምኞቴ። ግን ለሌሎች እንዲገዙ ወይም ለራሳቸው ጥፋት መሳሪያ እንዲሆኑ ያለፈው ሪሳይክል (Recycle) እያረገ የመጣው ሂደት መቆም አለበት። ይሄን ለማብሰር ብቻ ነው ብሬክ (Break) መደረግ ያለበት
እኛ በህክምና ጀነሬሽን ትራማ (Generation Trauma) የምንለው አለ። ከአያት ወደ ልጅ የሚመጣ በሽታ አንዱ ጀነሬሽን ደፍሮ መስፈር አለበት። እኔ የመጣሁት ይሄን ለመስበር ጥሪ ለማድረግ እንጂ አዲስ ትንታኔ ይዤ አይደለም።
የሄድንበት በሙሉ በአዲስ ሽፋኖች፣ በአዲስ ልብሶች ነው። አዳዲስ የመጡ ሰዎች አሉ ግን ቋሚ ፕሌየር (Player)፣ ቋሚ ተዋናዮች ናቸው። ቃላት እንኳን ፍሬዝ (Phrase) እንኳን አልቀየሩም። “አብይን ለመጣል ከሰይጣን ጋር እንሰራለን” ይሉ ነበር። ግንቦት 7 ይሄን ይል ነበር።
ለምንድነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰይጣንን የሚመርጠው? አማራ የራሱ ሃይል እያለው፣ ፋኖን ያህል ሃይል እያለ፣ ህዝብ፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ ታሪካዊ ማንነት፣ ሃይማኖት ሁሉ በእጁ እያለ ለምን ባዶ ተስፋ ይከተላል? ከሰይጣን ጋር መስራት ማለት ከአብይ ጋር፣ ከወያኔ ጋር፣ ከኦነግ ጋር መስራት ማለት ነው። ስለዚህ ይሄ ሂደት መሰበር አለበት። ከእኔ ወጣት የሆናችሁ፣ የእናንተ ፊቸር (Future) ነው ፊታችሁ ላይ ያለው።
በየሚዲያው ቶኪንግ ፖይንት (Talking Point) ተብለው የሚወረወሩ አሉ። አሁን “ጽምደትን፣ ጥምረቱን የተቃወመ ብልጽግና” ይላሉ። ጩኸቴን ቀሙኝ! ይህ ምን ያህል የወደቁ እና የወዳቂ ውዳቂ መሆናቸውን ያሳያል ይላል ዶክተር ደብሩ። ለተቃዋሚነትም እንኳ፣ እንደ ጠላት እንኳን ለመቁጠር ማይመጥኑ የወደቁ ናቸው። ሲምፕሊስቲክ (Simplistic) አስተሳሰብ ነው። በዚህ እውነተኛው ኢትዮጵያዊ እየሸሸ ይኖራል።
ያ የዛሬ 30 ዓመት አድርጋችሁት ይሆናል። የዛሬ 40 ዓመት፣ 50 ዓመትም ተደርጎ ይሆናል። የዛሬ 8 ዓመትም። በአብይ ጊዜ ግን “የብልጽግና ደጋፊ ናቸው” ይላሉ። “ሌላ አማራጭ የለም” የሚለው ስቴትመንት (Statement) ከግንቦት 7 ጀምሮ ተደጋግሟል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስርዓት ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለአማራው ህዝብ በጣም ጠንቅ የሆነ ከፍተኛ ነቀርሳ ነው። መነቀል ያለበት በሽታ ነው። ያንን በሽታ ተሸክሞ ኢትዮጵያን አድናለው፣ አማራውን አድናለው ማለት አይቻልም። ሁልጊዜ የምንለው ነው፦ ባክቴሪያ ያለበት ውሃ እየጠጣህ ባዮቲክስ (Antibiotics) ብሰጥህ አትድንም። መጀመሪያ ስቶፕ ድሪንኪንግ (Stop Drinking) ማለት አለብህ አይደል?
ህሊናቸው ያልነቃ ሰዎች ፖለቲከኛ ሲሆኑ አርመኔዎች፣ ሰው በላዎች፣ ዘራፊዎች፣ ገፋፊዎች ናቸው። ህሊና ያለው ሰው ከሌላ እንስሳ የሚለየው በህሊናው ነው። የአሁኖቹ ፖለቲከኞች በደመ-ነፍሳቸው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ሊትረሊ (Literally) ማለት ነው። በደመ-ነፍስ ማለት በደምህ ውስጥ በሚዘዋወረው ሆርሞን እና ኢንስቲንክት (Instinct) ብቻ መንቀሳቀስ ማለት ነው።
ሙሉውን የ ዶር አበባ ፈቃደን ንግ ግ ር ለማድመጥ ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።






















