የታሪክ ተመራማሪው ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦ
በኢትዮጵያ ታሪክ ስልታዊና ጊዜያዊ አብሮ መስራት ያለ ቢሆንም በዘር፣ በወገን እና በብሄር ተከፋፍሎ መስራት ግን ያልተለመደ ነው። ይህ የመጣው ከደርግ ሳይሆን ከወያኔ ነው።
ወያኔ ያመጣው አዲስ ትርክት “ኢትዮጵያ በጎሳ የተለያየች ሀገር ናት፣ አንድ ጨቋኝ ጎሳ ለብዙ ዘመናት ሌሎችን ጎሳዎች ጨቁኗል፣ አሁን ነጻ መውጣት አለባቸው” የሚል ነው።
ይህ ትርክት ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር እጅግ የሚጻረር ነው። በንጉሳዊ ዘመን የብሄርና የሀገር አንድነት በጥያቄ ውስጥ ገብቶ አያውቅም። በደርግ ዘመንም የተለያዩ ፅንሰ ሃሳቦች ቢገቡም የሀገር ቀጣይነት እና የህዝብ አንድነትን አላናጋም። ጨቋኝ እና ተጨቋኝ የሚለው ትርክት የነበረ ቢሆንም ጨቋኙ እንደ ስርዓት ነው የታየው እንጂ እንደ ጎሳ አይደለም። ፌዩዳሊዝም የባለባት ስርዓት በሁሉም ኢትዮጵያ ይነበረ እንጂ የአንድ ጎሳ ብቻ አልነበረም።
ይህ የ”አማራ ጨቋኝ ነው” የሚል ሃሳብ መጀመሪያው ከጣልያኖች እና አውሮፓውያን ነው። ኢትዮጵያን በአድዋ ስትሸንፍ፣ “እንደ ሚኒሊክ ያዋረደን የለም” ብለው ነው። ከዚያ ኢትዮጵያን እንዴት እንከፋፍላት በሚል የተለያዩ ዘዴዎችን ፈጥረዋል። አንዱ ዘዴው “ሀገሪቱ በአማራ ጨቋኝነት ስር ናት” ብሎ በማሳየት መከፋፈል ነው።
ይህንኑ ሃሳብ የ1960ዎቹ ተማሪዎች አንስተውት ነበር፣ ስልጣን መያዝ አልቻሉም። ከእነሱ አስተሳሰብ ያልወጣው ወያኔ ግን ይህንኑ ስልጣን ለመያዝ በግብር ላይ አዋለ። ወያኔ የተለያዩ ጎሳዎችን አንድ ላይ ሲያመጣ ዋና አላማው ኢትዮጵያን በጎሳ መከፋፈል ነበር። በፊት “አማራ” ነበር፣ አሁን አማራን የተካው በራሱ ትግርኛ ተናጋሪ ወያኔ ነው። ህገ መንግስቱን ያረቀቀውም ይህን ሃሳብ በህግ ለማስፈጸም ነው።
አማራን ክልል ከፍሎ ሰጥቶ፣ በሌላ ቦታ ያለውን አማራ ደግሞ በማሳደድ፣ መብት በመከልከል፣ ወደ ክልሉ እንዲመለስ በማድረግ፣ ወይም በየቦታው መግደልና መጨፍጨፍ እንደ ፈቃድ ተወስዷል።
ይህንኑ እውነት የተቀበሉት እንደ ኦነግ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የትግራይ ነጻነት ድርጅቶች እና ኤርትራውያንም ጭምር ነው።
ፋኖ ግን ለአማራ ጥቅም የቆመ እና በመጨረሻም ዋና አላማው ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተቋቋመ ነው። ይህ በታሪክ ተቀባይነት ያለው ጊዜያዊና ስልታዊ አካሄድ ቢሆንም ዋናው አላማ መርህ መዛባት የለበትም።
ዋናው አላማ ኢትዮጵያዊነት፣ የአማራ ህዝብ ነጻነት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት፣ እና በመጨረሻም በፍትህ፣ በነጻነት፣ በአንድነት እና በእኩልነት አገሩን ማስተዳደር ነው።
ፋኖ እንደዚህ ሲያደርግ ህዝቡን እስከማወዛገብ ሊደርስ ይችላል። ልዩነቱ ግን ጊዜያዊ ስኬት ቢኖረውም በመጨረሻ ወዴትም ሊያደርሰው አይችልም፣ ምክንያቱም እንደሌሎቹ ከሸፈው መቅረትነው ብዬ ነው የምገምተው።
















