>

ብአዴን ግለሰብ እንጅ ድርጅት አይደለም!!! (ሚኪ አምሀራ)

ብአዴን (በረከት) ያጠፋቸዉ ሰወች እና ህወሃት 2008 ላይ ለሁለት ሳምንት ስዉር እስር ቤት ያሰረዉ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል፡፡ 
1. መላኩ ፈንታ፡፡ መላኩ ፈንታ በግፍ ነዉ የታሰረዉ፡፡ የዛሬ 5 አመት ገደማ የአማራ ህዝብ በደቡብ፤ በቤንሻንጉል እና ሌሎችም አካባቢ ሲፈናቀል ስብሰባ ላይ ለምን አፈናቃዮች መጠየቅ አለባቸዉ ብሎ ተከራክረዋል፡፡ ሽፈራዉ ሽጉጤ መጠየቅ አለበት ብሎ ማእከላዊ ስብሰባ ላይ አንስቷል፡፡ የበረከት ቤተዘመዶች ያለቀረጥ ያስመጡትን የ 3 ሚሊየን ካሜራ ወርሷል፡፡ የእነ ሳሞራን እና ጌታቸዉ አሰፋን ለቤት መስሪያ እያሉ ከግብር ነጻ እቃወችን አምጥተዉ ሲቸበችቡ አስቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት በእነዚህ ግለሰቦች ቂም ተቋጥሮበት እስር ቤት ነዉ፡፡ መላኩ የድርጅት ወይም የብአዴን ወይም ኢህአዴግ እስረኛ አይደለም፡፡ የበረከት፤ የሳሞራ እና ጌታቸዉ አሰፋ እስረኛ ነዉ፡፡
2.ጌትነት አማረ፡፡ ጌትነት የጎንደር ከንቲባ ሁኖ በባለፉት አመታት ሰርቷል፡፡በ 2008 ጎንደር ላይ ከተካሄደዉ የህዝብ አመጽ በኋላ በግፍ ያለፍርድ ታስሮ ይገኛል፡፡ የታሰረበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ የተነገረዉ ግን የአርማጭሆ እና ወልቃይት ህዝብ ጎንደር መቶ ሲሰፈር ዝም ብለሃል ለዚህም ነዉ እዚህ ከተማ ላይ አመጽ የተነሳዉ ተብሎ ነዉ፡፡ የአርማጭሆንና የወልቃይትን ሰዉ ግን ጎንደር አትምጡ ቤት አትስሩ ብሎ ለመከልከል የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ጌትነት ለአለቃ አይመችም በተለይ ዝማምና አለምነውን ስለሚሳደብ በተንኮል ነው ያሳሰሩት:: ጌትነት የዝማምና አለምነው እስረኛ ነው፡፡ ሀለቱንም በስብሰባ ላይ ጸረ ህዝብ ናችሁ ብሎ በገሃድ ተናግሯቸዋል፡፡ የጌትነት በደል ከድርጅት ጋር አይያያዝም የግለሰቦች የአለምነዉ እና የዝማም እስረኛ ነው፡፡
3. ኮሎኔል ናቃቸዉ፡፡ጀግና የአርማጭሆ ልጅ ነዉ፡፡ ህወሃትም ብአዴንም ከሚፈሩት ሰወች አንዱ ነበር፡፡ የእነ ዳንሻ ኁመራ ወደ ትግራይ አይካለልም ያሉ የአርማጭሆ ጠገዴ ነዋሪዎችን ሂድና አሳርፍ ተብሎ አገሬን ቤተሰቤን ሄጄ አልጨፈጭፍም አላቸዉ፡፡ ጥያቄያቸዉም ትክክል ነዉ ብሎ ይከራከር ነበር፡፡ ለስብሰባ ብለዉ መቀሌ ጠርተዉት መረዝ ካበሉት በኋላ ታሞ ወዲያዉ ሞተ፡፡
4.  ቹቹ  አለባቸዉ፡፡ ቹቹ ከድርጅቱ ጋር ግጭት የጀመረው ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ችግሩ መንስኤ አርማጭሆና ጠገዴ አስተዳደሪ እያለ( የወልቃይት ደንበር አካባቢዎች ናቸዉ) ህውሀትን መስፋፈት ለመመከት በብርቱ ስለታገለ ነበር፡፡ በተለይም አሁን ምእራብ አርማጭሆ የሚባለውን ወረዳ ( አብደራፊና አካባቢው) ከህውሀት ለማስቀረት የተቻለው በሱ ጥረት ነው፡፡ ማርዘነብ የተባለውን አከባቢም አስቀርቶታል፤ግጨዉን ግን ከ20 አመት በላይ ቢጮህም ሳይሳከላት ተቋጨ( በነገራችን ላይ ቹቹ ቅጽል ስሙ ግጨው ነው)፡፡ ቹቹ ባይኖር የትግራይ ደንበሩ ቢያንስ መተማ ይሆን ነበር፡፡  የተባረረዉ እነዚህን የ25 አመት ጥያቄዎች እንደገና አንስቶ ሌሎች ታጋዮችን እያነቃ ነዉ ተብሎ ነዉ፡፡ በስብሰባዉ ከ ሻምበል ጋር በመሆን ልዩነታቸዉን ሁለቱ ብቻ አስመዝግበዉ ወተዋል፡፡ በነበረከት ቹቹ መርዝ እረጭ ነው ሳይዉል ሳያድር መባረር አለበት ተባለና ተባረረ፡፡ ስብሰባዉ ላይ ብአዴን ከኢህአዴግ አባልነቱ ይዉጣ ከህወሃት ይላቅቅ የሚል ሃሳብ አንስቶ ነበር፡፡ ከብአዴን ተባሮ አሁን የዶክትሬት ትምህርቱን እየተማረ ይገኛል፡፡ ዲግሪዉን ከጅማ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት ሰቅሎ ነበር የተመረቀዉ፡፡ ሁለተኛ ዲግሪውንም በአለም አቀፍ የሰው ልጆች መብት ጥበቃ በህግ( International Human Rights Law) ከጎንደር ዩንቨርስቲ 4.00 በማምጣት ተመርቋል፡፡(ፎቶ 3)
5. ሻንበል ከበደ፡፡ ሻምበል አክራሪ አማራ ነው፤ የአማራ ጉዳይ አይሆነለትም፡፡ ሁሌም የአማራን ድል ያነሳል፤ ህውሀትን ክፉኛ ይተቻል፡ ህውሀትን የበላይነት  በባህርዳሩ መድረክ በመረጃ ላይ ተመስርቶ አጋልጧል፡፡ብዙወቻችን ተቀርጾ የወጣዉን ኦዲዮ ሰምተነዋል፡፡ መጨረሻም ላይ ከቹቹ ጋር ሁኖ አቋሙን በልዩነት እስመዝግቧል፡፡ ከኦዲዮዉ እንደሚሰማዉም እነ በረከት ለምን አይባረሩም የሚል ነዉ፡፡ለስራ ጉዳይ ወደ ዉጪ ሊወጣ ሲል ፓስፖርቱን ቀምተዉ ምድር ቤት ዉስጥ አስረዉት ነበር፡፡ ከስብሰባዉ በኋላ አለምነዉ ከህወሃት ጋር በመተባበር ሻምበልን ሰውረው አስረውት ከሳምንታት በኋላ በደመቀ መኮነን ጥረት ነው በፍለጋ የተገኘዉ፡፡የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ከፍተኛ አመራር የሆነ ሰዉ ሳይሰማ ለብዙ ሳምንታት የደረሰበት ሳይታወቅ ጨለማ ቤት ታስሮ ተገርፏል፡፡ ህወሃት ይሄን ያህል እብሪተኛ ነዉ የራሱን አጋር ድርጅት የማያከብር፡፡ ለነገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም የዶ/ር አብይ ምርጫ እለት ምራቅ እንደተተፋበት ሁሉ አዉርቷል፡፡ ቤተሰቦቹ በደህንነቶች እንደተዋከቡበት አዉርቷል፡፡ ህወሀት እንደዚህ ወንበዴ ነዉ፡፡ሻምበል የተባረረው በዋነኛነት በበረከት፤ አዲሱ፤ዝማምና አለምነው ግፊት ነዉ፡፡
6.  ዮኃንስ ቧ ያለው፡ መጀመሪያ ከበረከት ጋር ቀኝ እጅ ነበር፤ በኃላ ሰዉየዉን ሲያየዉ አማራን ለመቅበር የተዘጋጀ ነዉ ከዛም ይሄ ሰዉየ ክፉ ነወ ብሎ ተራራቁ፡፡ ዮኃንስ በረከት የሚያቀርበዉን ጸረ አማራ ሃሳብ አልቀበለው እያለ እንደመጣና መናቅ መጀመሩን ነው፡፡ ልጁ ተናጋሪ እና ደፋር ነበር፡፡ በረከትንም በግልጽ አንተ ሰዉ ግን ትግራይን ነዉ ወይስ አማራን ነዉ ወክለህ እዚህ ያለኸዉ ሲል ስብሰባ ላይ አፋጠጠዉ፡፡ በረከት እንደተለመደዉ ምነዉ ያኔ እንደጓደኞቼ ተሰዉቸ በሆነ የሚላትን ማሸማቀቂያ በማንሳት የአዞ እንባ አለቀሰ ሌሎች ካድሬዎች አዘኑለት፡፡ ዩሀንስንም በነገዉ ተረባርበዉ አባረሩት፡፡
7. ጄኔራል አበባዉ፡፡ አበባዉ አማራን እጅግ ያከብራል፡፡ ጊዜዉን አንኳን ባህርዳር እና ጎንደር ነዉ የሚያሳልፈዉ፡፡ ከወጣቱ ጋር እንዲሁ እንደተራ ሰዉ እየተዝናና ነዉ የሚያሳልፈዉ፡፡ ሁሌም የህወሃት የበላይነት ይከነክነዋል፡፡ ስብሰባ ላይም ይናገራቸዋል፡፡ በተለይ ለሳሞራ ያለዉ ንቀት ከፍተኛ ነዉ፡፡ ሳሞራም እንዲነሳ አጥብቆ ታግሏል፡፡ ሳሞራ እና በረከት ወጥመድ አጥምደዉ ሳሞራን ሊገለብጥ ነዉ ብለዉ አባረሩት፡፡ አሁን የቁም እስረኛ ነዉ፡፡ ወደ ዉጪ ሊወጣ ሲል ፓስፖርቱን ቀምተዉ አባረዉታል፡፡በእርግጠኝነት በ2008 ባህርዳር ላይ በአንዲት በተረገመች ቀን 120 ሰዉ ሲገደል ይህ ሰዉ ዝም አይልም ነበር፡፡
8. ጌታቸው ጀንበር መጀመሪያ ጀግና ታጋይ ነበር፤ አሁን ደንዝዟል፤ ያደነዘዙትም በረከትና አዲሱ ናቸው፡፡ ለዚህ የበቃውም ያው በግጨው ጉዳይ ነው፡፡ ሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ ነበር፡፡ ለስብሰባ ባህርዳር ይሄዳል፡፡ የዛሬ አስር አመት ገደማ ነዉ፡፡ ስብሰባዉ ላይ እንኳን ግጨዉ ወልቃይት እራሱ መመለስ አለበት የሚል ሃሳብ ያነሳል፡፡ ወዲዉ ማታ የዞን አስተዳዳሪ ሁኖ የሄደበትን መኪና ይቀማል፡፡ ይታሰር ይባል እና ያለስምምነት ይጠናቀቃል፡፡ ከዛም ከሰሜን ጎንደር አመራርነቱ በነገዉ አነሱት፡፡ መኪና እንዳይጠቀም ተብሎ በአብቶብስ ከፍሎ ጎንደር ተመለሰ፡፡ ከዛ ጠፍቶ ኑሮ ሰሞኑን እንደገና አገግሞ ብቅ ብሏል፡፡
9. ዶ/ር አንባቸው እሳት ነበር፤ አሁን እደደነዘዘ ነው፤ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ነዉ፡፡ ሁኖም ሁሌም ትምክህተኛ እያሉ ስለሚቀጠቅጡት በመደንዘዝ ጎዳና እንደገባ ነዉ፡፡ በረከት እና አምባቸዉ አይጥና ድመት ናቸዉ፡፡ ትምህክተኛ ነህ ብሎ አባሮት ነበር፡፡ ከዛም ወደ ትምህርት ሄደ፡፡ ለትህምክተኛ ከፍለን አናስተምርም ብሎ በረከት የብአዴን ስብሰባ ላይ ክስ አቅርቦ እየተማረ እያለ ገንዘብ ተቋርጦበት ነበር፡፡ ሰሞኑን ደግሞ እንደገና ተያይዘዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ብአዴን መሆን ያሳፍራል ብሎ ለበረከት እፊቱ ላይ ነግሮታል፡፡
10፡ ኮሎኔል ደሳለኝ አንዳርጌ እና ጄኔራል አሳምነዉ ለአማራ ህዝብ የሚሞቱ ናቸዉ፡፡ ትክክል አይደላችሁም ለአማራ ህዝብ ይሄ አይገባዉም ብለዉ ስብሰባ ላይ በተናገሩ ማግስት ተባረሩ፡፡
11. ሙሉ አለም አበበ፡፡ የጎንደሩ ሙሉ አለም ገና ከጅምሩ ነበር የህወሃት ሴራ በአማራ ላይ የገባዉ፡፡ ከዛም መቃወም ጀመረ፡፡ የተገደለው ማታ ስራ ላይ እያለ ቦንብ ተወርውሮበት ማርቆስ ሲሆን የሚታሙትም የኢህዴን ጓደኞቹ እነ በረከት ናቸው፤ቅንብር እንደነበር ይታወቃል ይጣራ ሲባልም እነ በረከት አለባብሰዉ አለፉት በዛም ተዳፍኖ ቀረ፡፡ ገለዉ አዳራሽ በስሙ ባህርዳር ላይ ሰየሙለት፡፡
እኔ ከዚህ በፊት አንድ ሰዉ ብቻዉን በሚሊየኖች ላይ ግፍ ሲሰራ የማዉቀዉ ሂትለርን ነዉ፡፡ ልክ እንደሱ በሚሊየኖች አንድ ብቻዉን ሁኖ ግፍ እየሰራ ያለዉ የኛዉ ሂትለር በረከት ነዉ፡፡ ብአዴን ድርጅት አይደለም፡፡ እንደምናየዉ የታሰሩት ሰወች እራሱ በድርጅት ተወስኖ አይደሉም የግለሰቦች እስረኞች ናቸዉ፡፡ አብዛኞቹ እኒህ የሚባረሩትና የሚታሰሩት ሰወች ወይ ከጎንደር አካባቢ ናቸዉ ወይ ከሰሜን ወሎ እና ዋግ አካባቢ ናቸዉ፡፡ ምክንያቱም የህወሃትን የመስፋፋት ፍላጎት ጠንቅቀዉ የሚያዉቁና የሚከራከሩ ስለሆኑ፡፡በየ አመቱ እኒህን የሚከራከሩ ሰወች እያባረሩ ነዉ መሬት እየገፉ በሰሜን በኩል ባህርዳር ሊደርሱ ምንም አልቀራቸዉም በምስራቁ በኩል ደሴ ሊደርሱ ምንም አልቀራቸዉም፡፡
ዝማም ስሟን በወጉ የማትጽፈዉ ሴትዮ (ባለፈዉ ስትጽፍ ቫወል አትጠቀምም ብያችሁ ነበር ZMMM ብላ የምትጽፈዉ ነች) ባቅሟ እንኳን የግል እስረኛ አላት፡፡ የጎንደር ከንቲባ ጌትነት አማረ የግሏ እስረኛ ነዉ ስብሰባ ላይ ስለሰደባት ብቻ ነዉ፡፡ ዝማም ማለት መጀመሪያ ሃይማኖቷን ከዛም ባሏን፤ ከዛም አካባቢዋን፤ ከዛም ድርጅቷን፤ በመጨረሻም አማራነቷን የካደች ዮዲት ጉዲት ናት፡፡ በሰሞኑ ስብሰባ ከበረከት ጎን በመቆም ለህወሃት ስታጨበጭብ ነበር፡፡ የክልተ አዉላሎ ወረዳ ተወካይ ነዉ የምትመስለዉ የደብረታቦር ሳይሆን፡፡ባሏ ከእንደዚች አይነት የህወሃት አለቅላቂ ጋር ከምኖር ብሎ ሳይናገር ጠፍቶ በፍለጋ ነበር የተገኘዉ፡፡ ከዛም አፋቱኝ ብሎ በስንት ሽማግሌ ነዉ የተፋታችዉ፡፡ ፍችኝ ሲላት ቆለጥህን አስቀጠቅጥሃለዉ አርፈህ ተቀመጥ ተብሎ ነበር የጠፋዉ፡፡
በነገራችን ላይ የትግራይ ወረዳዎችና ዞኖች ብአዴን ዉስጥ ከአማራ ክልል ወረዳወችና ዞኖች የተሻለ ዉክልና አላቸዉ፡፡ ለምሳሌ አብ ዞባ ደቡብ እነ ታደሰ ጥንቅሹ አሉ፡፡ የማእከላዊ ትግራይ ዞን ተወካይ ገነት ገ/እግዛብሄር ነች፡፡ ሃዱሽ ክልተ አዉላሎን ወረዳ ይወክላል፡፡ ህላዊ ዮሴፍ የአድዋ ተወካይ ነዉ፡፡ባህርዳር ላይ ከደሴ ይልቅ መቀሌ በደንብ ትወከላለች፡፡
CC// ANDM CC office ANRS Communication Affairs OfficeNigussu TilahunGedu Andargachew
Filed in: Amharic